የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
-
IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም.
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም.
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
የተፋጠነ ማስወገድ ወይም ደፖርተሽን ምንድን ነው?
ምን ተለወጠ? እነዚህ ለውጦች ለምን አስፈላጊ ናቸው?
ስለተፋጠነ ማስወገድ ወይም ዲፖርት የተለመዱ ጥያቄዎች
በፈጣን የማስወገድ ወይም ደሞ ደፖርት የመደረግ ሂደት ዉስጥ ከተካተትኩ፣ አሁንም ጥገኝነት ወይም ሌላ ዓይነት ፈቃድ በአሜሪካ ውስጥ ለመኖር መጠየቅ እችላለሁ?
እንዴት ነው የአሜሪካን መንግስት ጥገኝነት እንድጠይቅ እንዲፈቅድልኝ መጠየቅ የምችለው?
በፍጥነት እንዲወገዱ ወይም ደሞ ዲፖርት እንዲደረጉ የተባሉ ሰዎች ዉስጥ ከተመደብኩ ተይዤ (በእስር ቤት)እቆያለሁ?
በተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ በደፖርተሺን ሂደት ዉስጥ ከተመደብኩ ከጠበቃ ጋር መገናኘት እችላለሁ?
ከተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ ከደፖርተሺን እንዴት እራሴን ማትረፍ እችላለሁ? ከዳኛ ጋር መነጋገር እችላለሁ?
ስለተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ ለደፖርተሽን ካሳሰበኝ ምን ማድረግ እችላለሁ?
ዝርዝር መረጃ
በዚ አንቀጽ የተፋጠነ ማስወገድ ወይም ደፖርተሽን ምን ማለት እንደሆነ እና በማን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይገልጻል። በጃንዋሪ 2025 የተፋጠነ መወገድን በሰፊው ለማከናወን ትራምፕ ስለ ወሰዳቸው እርምጃዎች ይጋራል። በዚ አንቀጽ የምናያቸው ጠቃሚ መረጃዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል:
- ስለ ፈጣን የማስወገድ ወይም ደፖርተሽን ሂደት መረጃ ፣
- በሂደቱ ውስጥ ማን ሊካተት ይችላል ፣
- በሂደቱ ውስጥ ሲሆኑ ምን ይከሰታል, እና
- አንድ ሰው በአሜሪካ ውስጥ ለመቆየት ከሂደቱ እንዴት አድርጎ እራሱን ሊያተርፍ ይችላል።
የተፋጠነ ማስወገድ ወይም ደፖርተሽን ምንድን ነው?
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከሀገር መወገድ ወይም ድፖርት መደረግ የአሜሪካ መንግስት አንዳንድ ሰዎችን በፍጥነት እንዲያባርር የሚያስችል ሂደት ነው። ለምሳሌ፣ የተፋጠነ ማስወገድ ወይም ድፖርተሽን ለረጅም ጊዜ ስከናወን የነበረ ሂደት ሲሆን መንግስት ወደ አሜሪካ ያለፍቃድ የገቡትን አና ወደ አሜሪካ ለመግባት ስሉ ድንበር ላይ በአሜሪካ ኢሚግሬሽን መኮንኖች ተይዘው ወደመጡበን ሀርግ እንዲመለሱ ሲደረግ የነበረ ሂደት ነው።
በተፋጠነ መወገድ ወይም ድፖርተሽን ሂደት ዉስጥ ከዳኛጋ የመገናገት መብት የሎትም ። በምትኩ ሌላ የመንግስት ባለስልጣን ጉዳያችሁን በፍርድ ቤት የማቅረብ እድል ሳታገኙ ከሀገር እንድትባረሩ ሊያዝ ይችላል። ትዕዛዙ አንዴ ከገባ በኋላ ወደ ዜግነት ሀገርዎ አንደትመለሱ ሊያደርጉ ይችላሉ። ለአንዳንድ ሀገራቶች ደሞ ወደ ሌላ አገር ሊወሰዱ ይቺላሉ ለምሳሌ ወደ ሜክሲኮ።
ይህ ሂደት በትራምፕ ጊዜ ሲቀየር ሰምቻለሁ። በፈጣን ማስወገድ ወይም ደፖርተሽን ህጎች ምንድናቸው? እነሱ በእኔ ላይ ተጽዕኖ ሊኖራቸው እንደምችሉ እንዴት ማወቅ እችላለው ?
ከጃንዋሪ 23, 2025 ጀምሮ፣ መንግስት በምህረት ወይም በቪዛ ወደ አሜሪካ ለመግባት ፍቃድ የሌላቸው እና በአሜሪካ ውስጥ ከሁለት አመት በላይ መቆየታቸውን ማረጋገጥ የማይችሉ ሰዎች በፍጥነት የማስወገድ ሂደት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ብሏል። ወደ ኢሚግሬሽን ወይም ደሞ ወደ አሜሪካ ድንበር በመሄድ ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚጠይቁ ሰዎች አሁንም በፍጥነት እንዲወገዱ ወይም ደፖርት እንዲደረጉ ሊደረግ ይችላል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ያለ ቪዛ ወይም ሌላ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖሮት ወደ አሜሪካ ከገቡ፣ በፍጥነት እንዲወገዱ ወይም ደፖርትእንዲደረጉ ሊደረጉ ይችላሉ። ከ ጃንዋሪ 23 2025 ጀምሮ የአሜሪካ መንግስት ባስተላለፈው ውሳኔ ሰዎች በይቅርታ ወደ አሜሪካ ቢገቡም በተፋጠነ የማስወጣት ሂደት ዉስጥ እንደሚካተቱ አስታውቋል። አኛ እንደምንረዳው ከሆነ መንግስት ለአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ባስተላለፉት መልክት በምህረት መርሃ ግብር ወደ አሜሪካ የገቡትን ሰዎች የምህረት ጊዜያቸዉን እንዲገመግሙ እና በፍጥነት እንዲወገዱ ወይም ደፖርት እንዲደረጉ ማድረግ ይቻል እንደሆነ እንዲገመግሙ ነግሯቸዋል። መንግሥት ይህ በሲቢፒ (CBP) አንድ ቀጠሮ ወደ አሜሪካ የገቡትን ሰዎች እንዲሁም እንደ ኩባ፣ ሄይቲ፣ ኒካራጓን ወይም የቬንዙዌላ ዜጋ በይቅርታ የተቀበሉ ሰዎችን ይመለከታል ብሏል።ይህ ሕግ ለሌሎች ዘጎች ሰዎች ላይም ሊተገበር ይችላል ብሏል ።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች እና በኢሚግሬሽን የጥገኝነት ጉዳያቸዉን እየተከታተሉ ላሉ ሰዎች መንግስት ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ለማቆም እና በምትኩ በፍጥነት እንዲወገዱ ወይም ደሞ ወደ ዜግነት ሀገራቸው እንዲመለሱ ሊያደርግ ይችላል። መንግስት ይህንን ህግ ከአንድ አመት እና ከዚያ በላይ በይቅርታ በገቡ እና እስካሁን የጥገኝነት ጥያቄ ባላቀረቡ ሰዎች ላይም ሊጠቀሙበት እንደሚፈልጉ ተናግሯል።
ምን ተለወጠ? እነዚህ ለውጦች ለምን አስፈላጊ ናቸው?
ከነዚህ ለውጦች በፊት፣ በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ሰዎች በአሜሪካ ድንበር በ100 ማይል ርቀት ላይ እና ወደ ሀገር በገቡ በ14 ቀናት ውስጥ በአሜሪካ መንግስት ከተያዙ ብቻ በተፋጣኝ ልወገዱ ወይም ደፖርት ሊደረጉ ይችላሉ።
አሁን፣ ያለ ቪዛ ወይም በሌላ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ወደ አሜሪካ ከገቡ፣ በፍጥነት እንዲወገዱ ወይም ደፖርት እንዲደረጉ ሊደረጉ ይችላሉ። ከአሜሪካ ድንበር የቱንም ያህል ርቀት ላይ ብትሆኑ ምንም ለውጥ አያመጣም። ይህ ማለት በአሜሪካ ውስጥ ብዙ ተጨማሪ ሰዎች አሁን በተፋጠነ መወገድ ወይም ወደ ትዉልድ ሀገራቸው የመመለስ ፕሮግራም ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ እንደ ማለት ነው።
ስለተፋጠነ ማስወገድ ወይም ዲፖርት የተለመዱ ጥያቄዎች
በፈጣን የማስወገድ ወይም ደሞ ደፖርት የመደረግ ሂደት ዉስጥ ከተካተትኩ፣ አሁንም ጥገኝነት ወይም ሌላ ዓይነት ፈቃድ በአሜሪካ ውስጥ ለመኖር መጠየቅ እችላለሁ?
በተፋጠነ የማስወገድ ወይም ዲፖርት ሂደት ዉስጥ ለጥገኝነት ወይም ሌላ በዩኤስ ውስጥ የመቆየት ፍቃድ ለማመልከት ይፈቀድልዎ እንደሆነ ለማየት ሂደት መጀመር ይችላሉ። በፍጥነት የማስወገድ ወይም ደሞ ደፖርት ሂደት ላይ ከሆኑ፣ የአማሪካ መንግስት እርስዎ ለጥገኝነት መጠየቅ አንደምትችሉ እስክፈቅድ ድረስ ጥገኝነት መጠየቅ አይችሉም።
እንዴት ነው የአሜሪካን መንግስት ጥገኝነት እንድጠይቅ እንዲፈቅድልኝ መጠየቅ የምችለው?
ወደ ትውልድ ሀገርዎ መመለስን ከፈሩ እና ለአሜሪካ መንግስት ባለስልጣን እንደፈሩ ከነገሯቸው ቃለ መጠይቅ ሊደረግልዎ ይገባል። በዚያ ቃለ መጠየቅ ላይ የምትናገሩት ነገር የአሜሪካን መንግስት ለጥገኝነት ወይም ሌላ አይነት በአሜሪካ ውስጥ ለመቆየት ፍቃድ እንዲያመለክቱ ይፈቀድልዎ እንደሆነ ለመወሰን ይረዳል።
ሆኖም፣ የኢሚግሬሽን ባለስልጣኖች ፈርታቺው እንደሆነ ወይም ጥገኝነት ማመልከት እንደምፈልጉ ሊጠይቅዎ እንደማይችሉ ማስታወሱ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ማለት ምናልባት እርስዎን አይጠይቁዎትም ማለት ነው. ስለዚህ እርስዎ ወደ ትዉልድ ሀገርዎ መመለስ ከፈሩ ለአሜሪካ ባለስልጣናት በተቻለ ፍጥነት ማስረዳት አለቦት። ጉዳዮትን ለአንድ ሰው በላይ መንገር ይችላሉ እንዲሁም ከአንድ ጊዜ በላይ ሊነግሩዋቸው ይችላሉ።
ሌላ ማወቅ ያለቦት ነገር ከቤተሰብ ጋር እራሱ የሚኖሩ ከሆነ ሊለያዩ እንደሚችሉ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። ስለዚህ፣ ወደ ትውልድ ሀገርዎ ለመመለስ ከፈሩ፣ ሁሉም የቤተሰብዎ አባል እሄን ጉዳይ እንዴት ማረግ እንዳለባቸው የምመለከተዉን አካል ማናገር አንዳለባቸው እርግጠኛ ይሁኑ እና ለአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ለምን ወደ ትውልድ ሀገርዎ ለመመለስ እንደሚፈሩ በተቻለ ፍጥነት እና በተቻለ መጠን ማሳወቅ አለባችሁ ። ይህ ህግ ልጆች ላይም ሊተገበር ይቺላል።
የቃለ መጠይቁ ሂደት እንዴት ነው የሚሰራው?
ለአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለስልጣን ወደ ትውልድ ሀገርዎ መመለስ እንደሚፈሩ ከነገሯቸው ቃለ መጠይቅ ሊደረግልዎ ይገባል። እንደ ሁኔታዎ ይህ ቃለ መጠይቅ “ተአማኒ የሆነ የፍርሃት ቃለ መጠይቅ” ወይም “ምክንያታዊ የፍርሃት ቃለ መጠይቅ” ተብሎ ሊጠራ ይችላል። ስለዚህ ቃለ መጠይቅ ማወቅ ያለብዎት ያለባችሁ ትልቁ ነገር የኢሚግሬሽን ባለስልናት ለምን ወደ ትውልድ ሀገርዎ መመለስ እንደሚፈሩ ለማሳወቅ እና እርስዎ በአሜሪካ ውስጥ ለመቆየት እንዲያመለክቱ ሊፈቀድልዎ እንደሚገባ ለማሳወቅ ነው።
ይህ ቃለ መጠይቅ ጥገኝነት የሚያሰጥ ሳይሆን፣ጥገኝነት ለመጠየቅ አንደምትችሉ ለማወቅ የሚረዳ ቃለመጠየቅ ነው።
ስለ እነዚህ ቃለ መጠይቅ የበለጠ መረጃ እዚህ ድረ ገጽ ላይ ያገኛሉ here.
በፍጥነት እንዲወገዱ ወይም ደሞ ዲፖርት እንዲደረጉ የተባሉ ሰዎች ዉስጥ ከተመደብኩ ተይዤ (በእስር ቤት)እቆያለሁ?
አዎ፣ ሊታሰሩ ይችላሉ ። በአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ ትውልድ ሀገራቸው እንዲመለሱ የታዘዙ ወይም በቃለ መጠይቅ ሂደታቸው ወቅት ወደ ትውልድ ሀገራቸው እንዲመለሱ የታዘዙ አብዛኛዎቹ ሰዎች ይታሰራሉ። መታሰር ማለት ተይዞዉ በእስር ላይ እንደመሆን ማለት ነው።
በተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ በደፖርተሺን ሂደት ዉስጥ ከተመደብኩ ከጠበቃ ጋር መገናኘት እችላለሁ?
አዎ፣ የግሎ ጠበቃ ከፈለጉ መቅጠር ይችላሉ። የተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ በደፖርተሺን ሂደት በአጭር ጊዜ ዉስጥ ስለምጠናቀቅ ቶሎ ብሎ ጠበቃን ማነጋገር አስፈላጊ ነው።
ከታሰሩ፣ ጠበቃ እንዲኖሮት የመጠየቅ መብት እና ጠበቃ ለማግኘት ስልክ የመደወል መብት አልዎት። (ይህ ማለት ባለሥልጣኖች ጠበቃ ለማግኘት ከመጠየቅ ሊያግዱዎት አይችሉም እና ለማግኘት ለመሞከር ስልክ ከመደወል ሊያግዱዎት አይችሉም።)
ያልተረዱትን ሰነዶች አለመፈረም አስፈላጊ ነው. የተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ ለደፖርተሺን የመጋለጥ አደጋ ላይ ያላችው ሰው ከሆናችዉ ከህግ አስከባሪዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ከማድረጋችው በፊት ጠበቃን ማነጋገር ጠቃሚ ነገር ነው።
ከተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ ከደፖርተሺን እንዴት እራሴን ማትረፍ እችላለሁ? ከዳኛ ጋር መነጋገር እችላለሁ?
ወደ ትውልድ ሀገሮ ለመመለስ እንደሚፈሩ በቃለ መጠይቅ ጊዜ ለአሜሪካን መንግስት ካሳመኗቸው ጉዳዮ በኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት ሂደት ውስጥ እንዲካተት ይደረጋል ። ይህም ማለት ጉዳይዎን ለኢሚግሬሽን ዳኛ የማቅረብ እድል ይኖርዎታል ማለት ነው።ስለዚህ ወደ ትውልድ ሀገርዎ የመመለስ ፍራቻዎትን ለአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ተአማኒነት ያለው ምክናእት በቃለመጠየቅ ጊዜ ካልገሯቸው የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ዳኛ ሳያዩ ሊያስወግዶ ወይም ደሞ ድፖርት ሊያረግዎ ይችላሉ። ከተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ ለደፖርተሺን ወደ ኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት የመቅረብ እድል ካገኙ፣ አሁንም ቀሪው ጉዳዩን በእስር ሆነው መከታተል ሊኖርቦ ይችላል ።
ስለተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ ለደፖርተሽን ካሳሰበኝ ምን ማድረግ እችላለሁ?
በአሜሪካ ውስጥ ቋሚ ህጋዊ ፍቃድ የሌለው እና ከሁለት አመት በፊት ወደ አሜሪካ የገባ ማንኛውም ሰው ከተቻለ ስለግል ሁኔታችው ከኢሚግሬሽን ጠበቃ ጋር መማከር አለበት። የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት እነዚህን አዳዲስ ደንቦች እንዴት እንደሚተገብሩ በትክክል አናውቅም።
ስለ ተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ ለደፖርተሽን ከተጨነቁ፣ የህግ አስከባሪ አካላት መንገድ ላይ አስቆመዎት አንዳንድ ጥያቄዎችን ሊጠይቅዎት ስለሚችሉ ከታች የተዘረዘሩትን አስፈላጊ ዶኩመንቶች በእጆ መያዝ እንዳይረሱ:
-
በአሜሪካ ውስጥ ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ካሎት:
- የእርስዎን የኢሚግሬሽን ሁኔታ ውይም ደሞ በአሜረካ ውስጥ የመኖሪያ ፍቃድ እንዳላችሁ የሚያሳይ ወረቀት መያዝ አለባችዉ
-
እየተከታተሉ ያሉት የፍርድ ቤት ጉዳይ ወይም ማመልከቻ ካለዎት:
- እየተከታተሉት ያለው ጉዳይ ካለ እሱን የሚያሳይ ወረቀት
- ሆኖም፣ መንግስት አሁንም እርስዎን በተፋጠነ የማስወገድ ሂደት ወይም ደሞ ደፖርተሽን ውስጥ ሊያስገባዎት ይችላል።
-
ወደ አሜሪካ የገቡት ከሁለት ዓመት በፊት ከሆነ:
- በአሜሪካ ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ እንደኖሩ የሚያሳዩ ሰነዶች። እነዚህም የአውሮፕላን ትኬቶችን፣ የሚኖሩበት እስተት መታወቂያ ካርድ፣ የቤተ መፃህፍት ካርዶችን፣የቤት አድራሻዎ ያለበት ፖስታ ቤት፣ የትምህርት ቤት መዛግብት፣ የኪራይ ውል እና ሌሎች ተመሳሳይ ሰነዶች በአሜሪካ ውስጥ ከሁለት አመት በላይ እንደኖሩ የሚያሳዩ ሊሆኑ ይችላሉ።
የኢሚግሬሽን ሁኔታዎን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን መመለስ እንደሌለብዎት ያስታውሱ - በኢሚግሬሽን ሰዎች አንድ አንድ ጥያቄዎችን ከተጠየቁ ስለመብቶት የበለጠ መረጃ ለማወቅ እዚህ here ድህረ ገጾች ይመልከቱ።
ተጨማሪ መርጃዎች
NILC Know Your Rights Expedited Removal Expansion
National Immigrant Justice Center: Know Your Rights if You Encounter ICE