የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
-
IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም.
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም.
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
ይህ "አስፈፃሚ ትእዛዝ"(Executive Order) ምንድን ነው?
ይህ የአስፈፃሚ ትዕዛዝ(Executive Order) የስደተኛ ማመልከቻ ጉዳየን እንደት ልጎዳ ይችላል?
እነዚህ ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጡ ሂደቶች ልሠሩ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል? አዲሶቹ ደንቦች የማይተገበሩባቸው አጋጣሚዎች አሉ?
አዲስ የስደተኛ ማመልከ "USRAP" መክፈት እችላለሁ?
ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጠው የስደተኛ ማመልከቻ የእንኳን ደህና መጣችሁ ኮርፕ (Welcome Corps program) ፕሮግራም ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል?
እገዳው ወይም ደሞ አዲሱ ሕግ በአፍጋኒስታን P-1/P-2 ፕሮግራም በኩል በሚያመለክቱ አፍጋኒስታን ጉዳዮች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል?
የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ መንግስት ከአፍጋኒስታን ለሚመጡ አፍጋኒስታኖች የሚሰጠውን የመልቀቂያ እርዳታ (“CARE relocation”) ለግዜው ቆሟል?
የቤተሰቤ አባል ወደ አሜሪካ መጥቼ እንድቀላቀላቸው ጠይቀዉኝ ነበር። መምጣት እችል ይሆን?
አዲሱ ህግ ተዕኖ የማያመጣባቸውና አሁንም የሚሠሩ የጉዳይ ዓይነቶች
በአዲሱ የአስፈፃሚ ትዕዛዝ እንዲቆሙ የተደረጉ የጉዳይ ዓይነቶች
እገዳው በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል?
በUSRAP በኩል ወደ አሜሪካ ከመጣው እና አሁን አሜሪካ ዉስጥ የሚገኝ ከሆነ አዲሱ የአስፈፃሚ ትዕዛዝ የነን ጉዳይ ልነካብኝ ይቺላል?
ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ድረ ገጾች ይጎብኙ
ዝርዝር መረጃ
ይህ አንቀጽ በጃኑዋሪ 20, 2025 በፕሬዚዳንት ትራምፕ የተፈረመውን “የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራምን ማስተካከል” ተብሎ ስለተፈረመው አዲሱ “አስፈፃሚ ትእዛዝ” ጥያቄ ላላቸው ሰዎች ነው ይህ ማለት በአዲሱ አስፈፃሚ ትእዛዝ (executive order) መሰረት አሜሪካ የምታደርገዉን የስደተኞች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮግራምን ባለበት እንዲቆም ያደርጋል።
ይህ ተፈፃሚ የሚሆነው ትዕዛዝ ምን እንደሚል እና በእነዚህ ለውጦች ልነኩ ስለሚችሉ ሰዎች ምን ማለት እንደሆነ ያብራራል፣ ይህ ተፈፃሚ የሚሆነው ትዕዛዝ ስደተኛ አመልካቾች እና ለስደተኝነት ለማመልከት ያሰቡትን ሰዎችም ሊነካ ይቺላላ።
ይህ አስፈፃሚ ትእዛዝ(Executive Order) ምንድን ነው?
የአሜሪካ የስደተኞች ማቋቋሚያ ፕሮግራም የአሜሪካ የስደተኞች መግቢያ ፕሮግራም ወይም “USRAP” ይባላል።
"አስፈፃሚ ትዕዛዝ" (Executive order ) መንግስት አንዳንድ ነገሮችን እንዲያደርግ የሚጠይቅ በፕሬዚዳንቱ የሚፈረም ሰነድ ነው።
በ ጃኑዋሪ 20, 2025 ፕረዚደንት ትራምፕ “የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራምን ማስተካከል” የሚል አስፈፃሚ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።” ይህ ትዕዛዝ የአሜሪካ መንግስት ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዲገቡ የሚፈቅደውን አሰራር ለጊዜዉ እንዲቆም የማድረግና እንዲሁም የተጀመሩ የስደተኛ ማመልከቻዎች ላይ ለጊዜው ውሳኔዎች እንዳይሰጡ ያዛል ።
ምንም እንኳን የአሜሪካ መንግስት እነዚህን መመሪያዎች እንዴት እንደምተገበብር ዝርዝር መረጃ ባያወጣም ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ አዲስ የስደተኛ ማመልከቻዎችን መቀበል አቁሟል። እንዲሁም መንግስት ለነባር የስደተኞች ማመልከቻ ላይ ውሳኔ እንደማይሰጥ ገልፁአል ።
ይህ የአስፈፃሚ ትዕዛዝ(Executive Order) የስደተኛ ማመልከቻ ጉዳየን እንደት ልጎዳ ይችላል?
እየተከታተሉ ያሉት የስደተኛ ማመልከቻ ካልዎት ጉዳዩ ውሳኔ ሳይሰጥበት ላልተወሰነ ጊዜ ባለበት እንዲቆም ይደረጋል። የአማሪካ መንግስት የሚከተሉትን ጨምሮ ሁሉንም የስደተኞች ማመልከቻ ሂደት ባለበት እንዲቆም ውሳኔ አስተላልፏል:
- አዲስ ማመልከቻ መቀበል
- አዲስ ማመልከቻ መጀመር
- ለቃለ መጠይቅ የቀጠሮ ጊዜ መስጠት
- ለህክምና ምርመራዎች የቀጠሮ ጊዜ መስጠት ማቆም እና
- ሁሉንም ጉዳያቸውን አጠናቀው የበረራ ቀናቸዉን እየተጠባበቁ ያሉትን።
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጡ ሂደቶች ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አናውቅም። እነዚህ የቆሙት ጉዳዮች ሁሉ ስራ ሲጀምሩ አንዳንድ ሂደቶችን እንደገና መድገም ሊኖርብዎት ይችላል።
እነዚህ ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጡ ሂደቶች ልሠሩ የሚችሉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል? አዲሶቹ ደንቦች የማይተገበሩባቸው አጋጣሚዎችስ አሉ?
በአዲሱ የአስፈፃሚ ትዕዛዝ(executive order) እንደተገለፀው አንድ አንድ ከስደተኞች ጉዳይ ጋር የተያያዙት አሁንም ጉዳያቸው ሊቀጥል አንደምችል ገልጸዋል ነገር ግን የትኛው አንደሆነ አሁን ላይ አናዉቅም። በአዲሱ ትዕዛዝ(executive order)መሰረት መንግስት ከስደተኛ ጋር ተያይዞ ጉዳዮትን ማስቀጠል የምችለው ለ “ብሄራዊ ጥቅም” ይጠቅማል ቦሎ ካመነ እንዲዉም ስደተኛዉ በአሜሪካ ደህንነት ላይ ምንም አይነት ስጋት የለውም” ብሎ ካመነ በቻ ነው ብሏል። ትዕዛዙ ይህ ምን ማለት እንደሆነ አይገልጽም፣ እና የአሜሪካ መንግስት ልዩ ሁኔታን እንዴት እንደሚጠይቅ ምንም መረጃ አልሰጠም።
አዲስ የስደተኛ ማመልከ "USRAP" መክፈት እችላለሁ?
አይቻልም፣ የአሜሪካ መንግስት ሁሉንም አዲስ የስደተኛ ማመልከቻዎች በUSRAP በኩል አቁሟል።
ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጠው የስደተኛ ማመልከቻ የእንኳን ደህና መጣችሁ ኮርፕ (Welcome Corps program) ፕሮግራም ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል?
አዎ፣ የአሜሪካ መንግስት የእንኳን ደህና መጣችሁ ኮርፕ ፕሮግራምን አቁሟል። እንዲዉም አዳዲስ ማመልከቻዎችን ለስፖንሰርሺፕ ወይም ክፍት መተግበሪያዎችን ለማካሄድ እየተቀበለ አይደለም።
እኔ የአፍጋኒስታን ወይም የኢራቅ ልዩ የስደተኛ ቪዛ (SIV) አመልካች ነኝ። እገዳው ወይም ሌላ የትራምፕ አስተዳደር ለውጦች በSIV ማመልከቻዬ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ?
ምናልባት።
ማመልከቻ፣ ቃለመጠየቅ እና ሌሎች ሂደቶች፡ የአፍጋኒስታን እና የኢራቅ SIV ማመልከቻ፣ ቃለመጠይቆች አንዲሁም በኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽሕፈት በት የማመልከቻ ሂደቶች የUSRAP አካል ስላልሆኑ በእገዳው አይነኩም።
ጉዞ፡ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ለአፍጋኒስታን እና ለኢራቅ የSIV ባለቤቶች በረራዎችን አቁሟል። የSIV ባለቤቶች አሁንም የራሳቸውን የበረራ ጉዞ እንዲያመቻቹ ይፈቀድላቸዋል።
የስደተኛ ጥቅማጥቅሞች፡ በሌላ የትራምፕ አስተዳደር እርምጃ ምክንያት፣ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የSIV ባለቤቶች ለስደተኞች መልሶ ማቋቋሚያ ኤጀንሲዎች የገንዘብ ድጋፍ በቆመበት ጊዜ ሊነኩ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ፡ እባኮትን የስደተኛ ጥቅማ ጥቅሞችን በሚመለከት በዚህ መመሪያ ውስጥ ያለውን ክፍል ያንብቡ።
እገዳው ወይም ደሞ አዲሱ ሕግ በአፍጋኒስታን P-1/P-2 ፕሮግራም በኩል በሚያመለክቱ አፍጋኒስታን ጉዳዮች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል?
አዎ፣ ሁሉም የስደተኛ ማመልከቻዎች ታግደዋል፣ የአፍጋኒስታን P-1/P-2 ፕሮግራምን ጨምሮ።
የትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካ መንግስት ከአፍጋኒስታን ለሚመጡ አፍጋኒስታኖች የሚሰጠውን የመልቀቂያ እርዳታ (“CARE relocation”) ለግዜው ቆሟል?
ከጃንዋሪ 28፣ 2025 ጀምሮ የአሜሪካ መንግስት ከአፍጋኒስታን የመነሻ እርዳታ በረራዎችን አቁሟል። የአሜሪካ መንግስት የUSRAP መተግበሪያ ለሌላቸው አፍጋኒስታን በረራዎችን መቀጠል ይችላል።
የቤተሰቤ አባል ወደ አሜሪካ መጥቼ እንድቀላቀላቸው ጠይቀዉኝ ነበር። መምጣት እችል ይሆን?
ስለማንኛውም ሰው ጉዳይ እርግጠኛ የሆነ መልስ መስጠት አንችልም። ሆኖም፣ ይህ ትዕዛዝ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተጽኖ ሊያመጣ እንደሚችል እናውቃለን።
አዲሱ ህግ ተዕኖ የማያመጣባቸውና አሁንም የሚሠሩ የጉዳይ ዓይነቶች
-
ወዳጆ ወይም ቤተሰቦ ጥገኝነት ጠያቂ ከሆኑ እና I-730 (“follow-to-join asylee”) ሂደት በመጠቀም ወደ አሜሪካ እርስዎን ለማምጣት ካመለከቱ አዲሱ አስፈፃሚ ትዕዛዝ እሄን ጉዳይ አይነካም።
- ጥገኝነት ( Asylees) ማለት በአሜሪካ ውስጥ ጥገኝነት ጠይቃችሁ ተቀባይነት ስያገኝ ማለት ነው። የI-730 ሂደትን ተጠቅመው ወደ አሜሪካ ለመምጣት የሚያመለክቱ የጥገኝነት ጠያቂ ቤተሰቦች በአዲሱ አስፈጻሚው ትዕዛዝ አይነኩም፣ ምክንያቱም ጉዳያቸው የUSRAP አካል አይደለም።
- ስለ I-730 ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ይህንን ድረ ገጽ መጎብኘት ይችላሉ here.
-
I-130፡ ዘመድዎ በ I-130 (በቤተሰብ ላይ የተመሰረተ የኢሚግሬሽን አቤቱታ ፎርም) ወደ አሜሪካ ሊያመጣዎት ካመለከተ የእርስዎ ጉዳይ አይነካም።
- የ I-130 ቤተሰብን መሰረት ያደረገ የኢሚግሬሽን ሂደት ለአሜሪካ ዜጎች እና ህጋዊ ቋሚ ነዋሪዎች (LPRs፣ ወይም “አረንጓዴ ካርድ ያዢዎች”) ዘመዶን ወይም ወዳጆን ወደ አሜሪካ ለማምጣት የሚያመለክቱ ነው።ይህ መንገድ የUSRAP አካል አይደለም።
ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ይህንን ድረ ገጽ መጎብኘት ይችላሉ here.
በአዲሱ የአስፈፃሚ ትዕዛዝ እንዲቆሙ የተደረጉ የጉዳይ ዓይነቶች
-
ዘመድዎ ወይም ቤተሰቦ ስደተኛ ከሆኑ እና የ I-730 (“follow-to-join refugee”) ሂደት በመጠቀም እርሶን ወደ አሜሪካ ለማምጣት ካመለከቱ፡ ጉዳይዎ ሊነካ ይችላል። በእገዳው ምክንያት፣ ወደ አሜሪካ የሚደረግ ጉዞ እና በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ተዛማጅ እርምጃዎች ባሉበት ይቆማሉ። እገዳው በሌሎች የሂደት ደረጃዎች ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል ወይም አይኖረዉን የምለዉን እስካሁን አናውቅም:
- ይህ ማለት፣ “ስደተኞች” በUSRAP በኩል ወደ አሜሪካ የመጡ ሰዎች ናቸው፣ እነዚ ሰዎች ወደ አሜሪካ ከመግባታቸው በፊት ለስደተኝነት አመልክተው ተቀባይነት ያገኘ ነው ።
- ስለ I-730 ለስደተኞች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ ይህንን ድረ ገጽ መጎብኘት ይችላሉ here.
- ዘመድዎ በ“ቅድሚያ 3” (P-3) በተሰብ የማገናኘት ፕሮግራም ወደ አሜሪካ እርስዎን ለማምጣት ካመለከቱ፡ ጉዳይዎ ይነካል። ምክንያቱም የP-3 ፕሮግራም የUSRAP አካል ነው።
-
እርሶ ኢራቃዊ ወይም ሶሪያዊ ከሆኑ እና ዘመድዎ በልዩ የUSRAP I-130 ፕሮግራም እርስዎን ለማምጣት ካመለከቱ ፡ በUSRAP በኩል ያለህ የስደተኛ ጉዳይ ባለበት ይቆማል። ነገር ግን፣ ከላይ በተዘረዘረው መደበኛ የI-130 ሂደት የስደተኛ ቪዛ ሂደት ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም።
- ዘመድዎ ወይም ሌላ ሰው በደህና መጡ ኮርፕስ በኩል እርስዎን ስፖንሰር ለማድረግ ካመለከቱ፡ ጉዳይዎ ባለበት ይቆማል። የእንኳን ደህና መጣችሁ ኮርፕ ፕሮግራም በአሁኑ ጊዜ ባለበት እንዲቆም ተደርጓል።
- ዘመድዎ በማዕከላዊ አሜሪካ አናሳ (CAM) ፕሮግራም በኩል እርስዎን ወደ አሜሪካ ለማምጣት ካመለከቱ፡ የጉዳይ ባለበት ይቆማል፣ ምክንያቱም የCAM የስደተኛ ጉዳዮች የUSRAP አካል ስለሆነ። የCAM የይቅርታ ጉዳዮች እንዴት እንደሚነኩ እስካሁን አናውቅም።
እገዳው በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ጉዳዮች ላይ ተጽእኖ ያሳድራል?
አይ፣ እገዳው የUNHCR ሂደቶችን ወይም የስደተኛ ሁኔታን ወይም የመልሶ ማቋቋምን በሚመለከት የUNHCR ውሳኔን አይነካም። ነገር ግን፣ UNHCR ወደ ዩኤስ ለመልሶ ማስፈር ከላከህ እና አሁን የUSRAP ጉዳይ ካለህ፣ የዩኤስ የመልሶ ማቋቋም ጉዳይ ባለበት ይቆማል።
በUSRAP በኩል ወደ አሜሪካ ከመጣው እና አሁን አሜሪካ ዉስጥ የሚገኝ ከሆነ አዲሱ የአስፈፃሚ ትዕዛዝ የነን ጉዳይ ልነካብኝ ይቺላል?
እገዳው የሚነካው ከአሜሪካ ውጭ ያሉትን እና በUSRAP በኩል ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚፈልጉ ስደተኞችን ብቻ ነው። አሜሪካ ውስጥ ከሆኑ፣ እገዳው የእርሶን ጉዳይ አይነካምእባኮትን ቤተሰቦን ወደ አሜሪካ ለማምጣት ፎርም እየሞሉ ከሆነ ከላይ ያለውን ክፍል ያንብቡ።
በUSRAP ወይም በSIV በኩል ወደ አሜሪካ ከገባሁ እና የስደተኛ ጥቅማጥቅሞችን እያገኘው ከሆነ ፣ የትራምፕ አስተዳደር ለስደተኞች ማቋቋሚያ ኤጀንሲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ልያቋርጥ ይችላል?
ምናልባት። ከUSRAP እገዳ በተለየ የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካ ለሚገኙ የስደተኞችን የምያቋቅሙ ኤጀንሲዎችን ከአሜሪካ መንግስት የሚገኘውን የተወሰነ ገንዘብ ለስደተኞች አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ ትእዛዝ ሠቷቸዋል። የገንዘብ ድጎማው መቆሙ የሚያስከትለውን ትክክለኛ ተጽእኖ እስካሁን አናውቅም፣ ነገር ግን አንዳንድ የስደተኛ መቋቋሚያ ኤጀንሲዎች አገልግሎት መስጠታቸውን ቀጥለዋል እና አንዳንድ አገልግሎቶች ሊቆሙ ወይም ሊለወጡ ይችላሉ።
ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ድረ ገጾች ይጎብኙ
What is the U.S. refugee resettlement process? (የአሜሪካ የስደተኞች መልሶ ማቋቋም ሂደት ምንድነው?)
How can I check the status of my U.S. refugee application? (የአሜሪካ ስደተኛ ማመልከቻዬን ሁኔታ እንዴት ማየት እችላለሁ?)
What is the UNHCR resettlement process? (UNHCR የመልሶ ማቋቋም ሂደት ምንድ ነው?)