የይዘት ማውጫ
ይህ ጽሁፍ በመጨረሻ የታደሰው መጋቢት (March) 12 ቀን 2025 ነው
አጭር መግለጫ
ይህ ጽሁፍ፤ አዲሱን የአሜሪካ የስደተኞች ማቋቋም ፖሊሲዎችንና በፕሬዚደንት ትራምፕ ጥር (January) 20 ቀን 2025 ላይ የተፈረመውን አዲስ “የማስፈጸምያ ትእዛዝ” በተመለከተ ጥያቄ ላላቸው ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ይህ አዲስ የማስፈጸሚያ ትእዛዝ፤ የአሜሪካ ስደተኞችን የመቀበል ፕሮግራም ማስተካከያ (Realigning the United States Refugee Admissions Program) በመባል የሚታወቅ ሲሆን የነበረውን የአሜሪካ የስደተኞች የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም (U.S. refugee resettlement program) እንዲቆም የሚያደርግ ነው።
ይህ ጽሁፍ፤ የማስፈጽሚያ ትእዛዙ ምን እንደሚልና እነኚህ የተደረጉት ለውጦች በወቅቱ የስደተኛ ማመልከቻ ባስገቡና ወደፊት ለማስገባት በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ሊኖራቸው እንደሚችል የሚገልጽ ነው። በተጨማሪም ይህ ጽሁፍ፤ ይህንን የስደተኞች የመልሶ ማቋቋምያ ፕሮግራም እንዲቆም የሚያደርገውን የመንግስት ትእዛዝ በመቃወም ዓለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮግራም (ኢራፕ-IRAP) ያቀረበው ክስ በትእዛዙ ላይ ምን ያህል ተጽእኖ እንደሚያደርግ የሚያስረዳ ነው።
ስደተኞች አሁንም ወደ አሜሪካን አገር መምጣት ይችላሉን?
ይህ ውስብስብ ያለ ጥያቄ በመሆኑ መልስ ለመስጠት አዳጋጅ ነው። የሚሰጠው መልስም ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም የሚኖረው ሊሆን ይችላል። ጥያቄውን በደንብ ለመረዳት ከስደተኞች መልሶ ማቋቋም ጋር ስለተያያዘው የማስፈጸምያ ትእዛዝ (executive order) እንነጋገር። እንዲሁም ይህ ትእዛዝ እንዴት የአገሪቱን ፖሊሲ እንደቀየረና ወደ አሜሪካ ለመመጣት ለሚፈሉጉ ሰዎች ያሉት ወቅታዊ መመርያዎች ምን እንደሆኑ እንመልከት።
የአሜሪካ ስደተኞችን መልሶ የማቋቋም ፕሮግራም፤ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም (United States Refugee Admissions Program) ወይም ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) ይባላል። የማስፈጸምያ ትእዛዝ (executive order) ሲባል ደግሞ መንግስት አንድ ነገር እንዲፈጽም የሚያደርግ በፕሬዚደንት የሚሰጥ ኦፊሳልያዊ ትእዛዝ የያዘ ዶኩመንት ነው።
ጥር (January) 20 ቀን 2025፤ ፕሬዚደንት ትራምፕ፤ የአሜሪካ ሰደተኞችን የመቀበል ፕሮግራምን የሚያሻሽል (Realigning the United States Refugee Admissions Program) በመባል የሚታወቅ የማስፈጸምያ ትእዛዝ ሰጡ። ይህ ትእዛዝ፤ የአሜሪካን መንግስት (ለግዜው) ስደተኞች ወደ አሜሪካን አገር እንዳይገቡና ገና ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ የስደተኞች ጉዳዮችም ውሳኔ እንዳይሰጥባቸው ማገዱን ያመለክታል።
ፕሬዚደንቱ ይህን ትእዛዝ ካስተላለፉ በኋላ፤ የመንግስት ተቋሞች የስደተኞችን አዲስ ማመልከቻዎች ወድያውኑ መቀበል አቆሙ፣ ገና ውሳኔ ያልተሰጣቸውን ማመልከቻዎችንም ባሉበት እንዲቆዩ አደረጉ። በተጨማሪም ተቀባይነት አግኝተው ለጉዞ በዝግጅት ላይ የነበሩ ስደተኞች ይዘዋቸው የነበሩ በረራዎችና የጉዞ ዕቅዶችንም ሰረዙ።
የአሜሪካ የስደተኞች ማቋቋምያ ፕሮግራም (ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP)) አሁንም ገና በይቆይ እንደተያዘ ነውን?
ዓለም አቀፍ የስደተኞች የእርዳታ ፕሮግራም ኢራፕ( IRAP)፤ የአሜሪካን መንግስት ስደተኞችን የመቀበል ፕሮግራምን (ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) እንዲቆም ማድረጉ ህጋዊ አይደለም በማለት በአሜሪካ መንግስት ላይ ክስ መስርቷል። ይህ ጉዳይ አሁንም ገና በፍርድ ቤት እየታየ ነው። ግን አንድ ዳኛ፤ መንግስት ፕሮግራሙ እንዲቀጥል ማድረግ አለበት ብሎ ውሳኔ ሰጥቷል። ይሁንና መንግስት ፕሮግራሙ እንደነበረበት እንዲቀጥል አላደረግም። ይህም ስደተኞች በቀጥታ ወደ አሜሪካ እንዳይጓዙ አስቸጋሪ አድርጎታል። ከታች እንደተገለጸውም በአሁኑ ግዜ ወደ አሜሪካ ለመግባት ከሚሞክሩ ሌሎች ሰደተኞች ይልቅ፤ ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል የሚያስችል I-730 የተባለ ማመልከቻ የሞሉ አመልካቾች ናቸው (በራሳቸው ወጪ) ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚፈቀድላቸው።
ክሱ
የካቲት (February) 10 ቀን 2025፤ ኢራፕ( IRAP)-ዓለም አቀፍ የስደተኞች የእርዳታ ፕሮግራም፤ መንግስትን በመቃወም ፓቺቶ አንጻር ትራምፕ (Pacito v. Trump) በሚል ስያሜ በመንግስት ላይ ክስ አቀረበ። ይህ ክስ፤ መንግስት የአሜሪካን የሰደተኞች መቀበል ፕሮግራምን (U.S. Refugee Admissions Program (USRAP) እና ከሱ ጋር የሚተሳሰሩ የገንዘብ እርዳታ ሰጪዎችን በ ማስፈጸምያ ትእዛዝ (executive order) ማቆሙ ወይም ማገዱ ከህግ ውጭ ነው በማለት የሚከራከር ነው። ይሄው ክስ፤ በጉዳዩ የተቀመጠው ዳኛ፤ ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ( USRAP)ን ለማገድ የማስፈጸምያ ትእዛዙና መንግስት የወሰደው እርምጃ ህጋዊ አይደለም የሚል ውሳኔ እንዲበይን ይጠይቃል።
የካቲት (February) 25 ቀን 2025 ላይ፤ አንድ የማእከላይ መንግስት ዳኛ፤ ምንም እንኳን ጉዳዩ ገና ቀጣይ ቢሆንም፤ መንግስት ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ( USRAP)ን የማስቆም ወይም ይህንን ፕሮግራም ለማሳካት የሚያስችለውን ገንዘብ የመያዝ/የመከልከል ስልጣን የለውም ብሎ ውሳኔ አሳልፏል። በጹሁፍ የቀረበውን የዳኛውን ውሳኔ ለማየት እዚህ ላይ በቀረበው መገናኛ ላይ ይጫኑ። የመንግስት ተቋሞች፤ ይህ ጉዳይ እንደገና እንዲታይ ለበላይ ፍርድ ቤት አቤት ብለዋል። በአሁኑ ወቅት፤ ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ( USRAP) የስደተኞችን ጉዳይ የመመልከቱና ስደተኞችን መልሶ የማቋቋሙ ስራውን እንደገና ይጀምር ብሎ ዳኛው ያስተላለፈው ውሳኔ በስራ ላይ ይገኛል።
ወቅታዊ ሁኔታ
መጋቢት (March) 10 ቀን 2025፤ መንግስት፤ በዳኛው ለተሰጠው ትእዛዝ መልስ ለመስጠት የሁኔታ ሪፖርት አቅርቧል። በዚህ ሪፖርት መሰረትም፤ መንግስት የስደተኞችን ማመልከቻዎች በተመለከተ ውሳኔ መስጠት እንደጀመረ ተገልጿል። ግን ሌሎች የሂደት እርምጃዎች መቼ እንደሚጀምሩ ግልጽ አይደለም። መንግስት ገንዘብ እየሰጣቸው የስደተኞችን ጉዳዮች የሚመለከቱ፣ ከአመልካቾች ጋር ቀጥታዊ ግንኙነት የሚያደርጉ፣ እና የጉዳዮች ሂደቶችን የሚያስተባብሩ “የመልሶ ማቋቋም እገዛ ማእከሎች” (resettlement support centers) ግን በአሁኑ ወቅት የተከፈቱ ወይም ስራ የጀመሩ አይመስሉም።
ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ (executive order) እንዴት ነው በእኔ ጉዳይ ላይ ተጽእኖ ሊያደርግ የሚችለው?
ዳኛው፤ መንግስት በመልሶ ማቋቋምያ ፕሮግራም ላይ ያደረገውን እገዳ ማንሳት አለበት ብሎ የካቲት (February) 25 ቀን ላይ ትእዛዝ ከማስተላለፉ በፊት፤ መንግስት የስደተኞች ማመልከቻዎች ሁሉ በይቆይ እንዲያዙ አድርጎ ነበር። የስደተኛ የማመልከቻ ሂደቶች መልስ እንድያገኙ የሚያደርጉ እርምጃዎች ሁሉ እንዲቆሙ አድርጎ ነበር። የሚከተሉት ጭምር፡
- አዲስ ማጣቀሻዎችን (referrals) መቀበል
- አዲስ ጉዳዮችን መጀመር
- የቃለመጠይቅ ቀነ-ቀጠሮ መስጠት
- ለጉዳዮች ተቀባይነት መስጠት ወይም ጉዳዮችን አለመቀበል
- የህክምና ምርመራ እንዲደረግ ቀነ- ቀጠሮ መስጠትና
- እርምጃዎቹን በሙሉ ላጠናቀቁ ሰዎች የበረራ ግዜ ማጠናቀር
ዳኛው የካቲት (February) 25 ላይ ላስተላለፈው ውሳኔ መልስ በመስጠት፤ መንግስት እስከ አሁን ቃለመጠይቅ ያደረጉ አመልካቾች ጉዳይን በተመለከተ ውሳኔ የመስጠቱን ስራ እንደገና እንደጀመረ አመልክቷል። ሌሎች ስራዎች እንደገና ስለመጀመራቸው ግን የሰጠው መግለጫ የለም።
ከእገዳው ውጪ የሆኑ ጉዳዮች አሉን? ይህ አዲስ መመርያ የማይመለከታቸው ጉዳዮች አሉን?
የማስፈጸምያ ትእዛዙ (executive order) በልዩ የሚመለከታቸው ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ ይላል። ይሁንና በልዩ ሊታዩ ይችላሉ የሚላቸው ጉዳዮች የትኞቹ መሆናቸውን አልገለጸም። ትእዛዙ፤ መንግስት የተወሰኑ ጉዳዮችን በልዩነት ሊያይ የሚችለው “ለአገር ጥቅም” ነው የሚል ውሳኔ ሲወስድ ብቻና የሆነ ስደተኛ በአሜሪካ የደህንነት ጥያቄ ላይ አደጋ ሊፈጥር የማይችል መሆኑን ሲያረጋግጥ ብቻ ነው ይላል። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ትእዛዙ አያብራራም። የሆነ ጉዳይ በልዩነት እንዲታይ ለመጠየቅም ምን እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ መረጃ አይሰጥም።
የአሜሪካ ስደተኛ እርዳታ ፕሮግራም (USRAP)ን በተመለከተ አዲስ ጉዳይ ልከፍት እችላለሁን?
ግልጽ አይደለም። እንደ አንድ የፕሬዚደንቱ የማስፈጸምያ ትእዛዝ (executive order) መልስ መጠን፤ የአሜሪካ መንግስት የስደተኞች አዲስ ማመልከቻዎች ሁሉ በይቆይ እንዲያዙ አድርጓል። ይሁንና የካቲት (February) 25 ላይ አንድ ዳኛ መንግስት ይህንን ያደረገውን እንዲያነሳ አዟል። ጉዳዩን በዚህ መልኩ ስናየው፤ መንግስት አዲስ ማመልከቻዎችን መቼ እንደሚቀበል ገና የምናውቀው ነገር የለም።
እገዳው የእንኳን ደህና መጡ ፕሮግራምን (Welcome Corps program) ይመለከታልን?
አዎን። እንደ አንድ የፕሬዚደንቱ የማስፈጸምያ ትእዛዝ መልስ መጠን፤ የአሜሪካ መንግስት የእንኳን ደህና መጡ ፕሮግራምን (Welcome Corps program) በይቆይ እንዲያዝ አድርጓል። ይሁንና የካቲት (February) 25 ላይ አንድ ዳኛ መንግስት ይህንን በተመለከተ ያደረገውን እገዳ እንዲያነሳ አዟል። ጉዳዩን በዚህ አንጻር ስንመለከተው፤ መንግስት የእንኳን ደህና መጡ ፕሮግራም (Welcome Corps program) ጉዳዮችን መቼ ማስተናገድ እንደሚጀምር የምናውቀው የለም።
እኔ የአፍጋኒስታን ወይም የኢራቅ የልዩ ሰደተኛ ቪዛ (Special Immigrant Visa (ኤስ-አይ-ቪ SIV) አመልካች ነኝ። ይህ እገዳ ወይም የትራምፕ አስተዳደር ያደረጋቸው ለውጦች በዚህ ማመልከቻዬ ላይ ጫና ሊያደርጉ ይችላሉን?
ምናልባት።
ማመልከቻዎች ማስገባት፣ ቃለመጠይቆች፣ እና ሌሎች ሂደቶች፡ በኤምባሲና በቆንስሎች የሚገቡ የአፍጋኒስታንና የኢራክ ስደተኞች ማመልከቻዎች፣ ይህ እገዳ አይመለከታቸውም ምክንያቱም የ ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አካል ስላልሆኑ።
ጉዞ፡ ዓለም አቀፍ የስደተኝነት ድርጅት (International Organization for Migration (አይ-ኦ-ኤም-IOM) የኤስ-አይ-ቪ( SIV)፤ የአፍጋንና የኢራቅ ስደተኞች ሊያደርጉት የነበረውን በረራ አቁሟል። እነኚህ የኤስ-አይ-ቪ( SIV) ካርድ ተሸካሚዎች ግን በራሳቸው ወጪ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን በረራ ሊቀጥሉ ይችላሉ።
የስደተኞች ጠቀሜታዎች፡ የትራምፕ አስተዳደር በወሰደው ሌላ እርምጃ ፤ በኤስ-አይ-ቪ (SIV) ወደ አሜሪካ በ ገቡ በመልሶ ማቋቋምያ የገቡ ኤስ-አይ-ቪ (SIV) ካርድ ተሸካሚዎች፤ መንግስት ባገደው የገንዘብ እርዳታ ምክንያት ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል። ለተጨማሪ መረጃ፤ ከታች የስደተኞች ጠቀሜታዎች በሚል ርእስ የተጻፈውን ክፍል በመመርያው ላይ ያንብቡ።
ይህ እገዳ በ አፍጋን(Afghan) P-1 / P-2 ፕሮግራም በኩል ማመልከቻ ያስገቡትን የአፍጋን ስደተኞችን ይመለከታልን?
አዎን። ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ (executive order)፤ በሁሉም የስደተኞች ማመልከቻዎች ላይ ጫና ያደርጋል እንዲሁም በአፍጋን(Afghan) P-1 / P-2 ፕሮግራም በኩል ማመልከቻ ያስገቡትንም ይጨምራል። ይሁንና የካቲት (February) 25 ላይ አንድ ዳኛ መንግስት ያደረገውን እገዳ ሁሉ እንዲያነሳ አዟል። ጉዳዩን በዚህ ት እዛዝ አኳያ ከተመለከትነው መንግስት እነኚህ ጉዳዮችን ማየት መቼ እንደሚጀምር ገና የምናውቀው ነገር የለም።
መንግስት ከአፍጋኒስታን ለሚመጡ የአፍጋን ስደተኞች ያደርገው የነበረውን የመጓጓዥያ እርዳታ (CARE relocation)፤ የትራምፕ መንግስት አግዶታልን?
ከጥር (January) 28 ቀን 2025 ጀምሮ ፤ የአሜሪካን መንግስት ከአፍጋኒስታን ለሚመጡ ስደተኞች ያደርገው የነበረውን የአይሮፕላን በረራ እርዳታ አቋርጦታል። የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP ) ማመልከቻ ለሌላቸው የአፍጋን ተወላጆች ግን ወደ አሜሪካ ለመብረር የነበራቸውን ፈቃድ እንደገና ሊቀጥለው ይችል ይሆናል። ግን መንግስት በዓመቱ መጨረሻ ላይ ፕሮግራሙን በ አጠቃላይ ይሰርዘዋል የሚል ዜና አለ።
የቤተሰቤ አባል የሆነ ሰው እኔ ወደ አሜርካን አገር እንድመጣ ማመልከቻ አስገብቶልኛል። ለመምጣት እችላለሁን?
የአንድ ግለሰብን ጉዳይ በማስመልከት እርግጠኛ መልስ ለመስጠት አንችልም። ይሁንና ይህ ትእዛዝ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንዴት ተጽ እኖ እንደሚያደርግ እናውቃለን።
ይህ ትእዛዝ ተጽእኖ የማያደርግባቸው ጉዳዮች
- ዘመድዎ ራሱ ስደተኛ ሆኖ እርሶም ወደ አሜሪካን አገር እንዲገቡ I-730 (የመቀላቀል follow-to-join asylee”) የሚባለውን ህግ ተጠቅሞ ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ ጉዳዮን አይመለከትም።
- አሲሊ“Asylee” ወይ ስደተኛ ማለት በአሜሪካን አገር ውስጥ ሆኖ የጥገኛነት መብት እንዲሰጠው የሚጠይቅ ሰው ማለት ሲሆን፤ የአሲሊ ቤተሰቦች የ I-730 ህግ ተጠቅመው ወደ አሜሪካን አገር ለመምጣት የሚሞክሩ ሰዎች ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ አይመለከታቸውም። ምክንያቱም ጉዳያቸው የ ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አካል ስላልሆነ።
- ይህንን ሲጫኑ ስለዚህ የሰደተኞች I-730 ህግ ተጨማሪ መረጃ ያገኛሉ።
- I-130: ዘመድዎ የI -130 (በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘ የስደተኛነት መጠየቅያ ፎርም) በመጠቀም ወደ አሜሪካን አገር ሊያስመጣዎት ከፈለገ፤ ጉዳዮ በማሰፈጸምያ ትእዛዙ አይነካም።
- ይህ በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘ ስደተኛን ወደ አሜሪካን አገር የማስመጣት ሂደት የሚመለከተው ብቁ የሆነ ቤተሰባቸውን ለማስመጣት የሚፈልጉ የአሜሪካ ዜጎችንና ህጋዊ የሆነ የመኖርያ ፈቃድ ( ግሪን ካርድ)ያላቸውን ሰዎች ነው። ይህ መንገድ የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) ክፍል አይደለም። እዚህ ላይ በመጫን ተጨማሪ መረጃ ስለዚህ ጉዳይ ማግኘት ይቻላል።
ይህ ትእዛዝ የሚመለከታቸው የጉዳዮች ዓይነት
- ዘመድዎ፤ በመከተል መቀላቀል የሚለውን የ I-730 (“follow-to-join refugee”) ማመልከቻ የሞላና በዛ ማመልከቻ ላይ ተሞርክዞ ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚሞክር ከሆነ፤ የወጣው የእገዳ ትእዛዝ ይመለከተዋል። ምክንያቱም በዚህ የእገዳ ትእዛዝ፤ የመንግስት ተቋሞች ሁሉ፤ የስደተኞች ጉዳዮችን የማየትና የጉዞ ሁኔታዎች እንዲቆሙ አድርገዋል። ይሁንና የካቲት (February) 25 ላይ አንድ ዳኛ፤ መንግስት ይህንን ያደረገውን እገዳ እንዲያነሳ አዟል። በመሆኑም መንግስት፤ ለዚህ ውሳኔ ምላሽ በመስጠት በዚህ ዓይነት ጉዳይ ላይ፤ ጉዳይ የመመልከትና ውሳኔ የመስጠት ተግባር እንደገና እንዲጀመር ማድረጉን አመልክቷል። እንዲሁም ማመልከቻቸው ተቀባይነት ያገኘ አመልካቾች ወደ አሜርካ ለመጓዝ ተፈቅዶላቸዋል ብሏል።
- በዚህ ይዘት አኳም፤ ስደተኞች (refugees) ሲባል በአሜሪካ የስደተኞች እርዳታ ፕሮግራም (ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ- USRAP) በኩል ወደ አሜሪካ ገብተው መልሶ በመቋቋም ላይ ያሉ ናቸው። ይህም ማለት አሜሪካ እንደ ስደተኛ እንድትቀበላቸው፤ ወደ አሜሪካን አገር ከመግባታቸው በፊት፤ ማመልከቻ አስገብተው ወደ አሜሪካ ለመግባት ፍቃድ ያገኙ ማለት ነው።
- በአሁኑ ወቅት መንግስት በዚህ ለ መቀላቀል መከተል የስደተኞች ፕሮግራም(follow-to-join refugee) ሂደት ውስጥ የተካተቱና ከእገዳው በፊት፤ ወደ አሜሪካን አገር ለመጓዝ ተዘጋጅተው የነበሩ ሁሉ የራሳቸውን የጉዞ ወጪ በመሸፈን ወደ አሜሪካ እንዲጓዙ ፈቅዷል።
- የአሜሪካ መንግስት፤ የህክምና ምርመራ ለማድረግ በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ለ መቀላቀል መከተል የስደተኞች ፕሮግራም(follow-to-join refugee) አመልካቾች በአሁኑ ወቅት የራሳቸውን የህክምና ወጪ መክፈል አለባቸው ይላል። ምርመራቸውን ለማድረግም ራሳቸው በቀጥታ ከሃኪሞች ቡድን ውስጥ ሃኪም መምረጥና የምርመራ ቀጠሮ መውሰድ አለባቸው። ስለዚህ የሃኪሞች ቡድን ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፤ embassy website ውስጥ ይግቡና ቃለመጠይቅ ያድርጉ።
- ስለዚህ የስደተኞች I-730 ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይጫኑ።
- ዘመዶ ፕራዮሪቲ 3 የቤተሰብ ማሰባሰብያ ፕሮግራም ( “Priority 3” (P-3) Family Reunification program) በሚባለው መሰረት ወደ አሜሪካ ሊያስመጣዎት ማመልከቻ ካስገባሎት፤ የእገዳ ትእዝዙ ጉዳዮን ይመለከታል። ይህ የፒ-3 (P-3) ፕሮግራም የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አንድ ክፍል ነው። ይሁንና የካቲት (February) 25 ላይ አንድ ዳኛ መንግስት ይህንን እገዳ እንዲያነሳ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህ የፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰረት መንግስት እነዚህ ጉዳዮችን መመልከቱን መቼ እንደገና እንደሚጀምር ገና የምናውቀው ነገር የለም።
- የኢራቅ ወይም የሶርያ ተውላጅ ሁነው ዘመድዎ በዚህ ልዩ የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ I-130 (USRAP I-130) ፕሮግራም መሰረት ወደ አሜሪካ እንዲመጡ ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ በዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) በኩል ያደረጉት የስደተኛ ጉዳዮ በእገዳው ሊካተት ይችላል። ይሁንና የካቲት (February) 25 ላይ አንድ ዳኛ መንግስት እገዳ ውን እንዲያነሳ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህ የዳኛ ትእዛዝ መሰረት መንግስት መቼ እነዚህ ጉዳዮችን መመልከቱን እንደገና እንደሚጀምር ገና የምናውቀው ነገር የለም። በተጨማሪ ከላይ በተጠቀሰው በመደበኛው የ I-130 ሂደት መሰረት ለስደተኞች የሚሰጠው የቪዛ ማውጣት ሂደት በዚህ እገዳ አይጠቃለልም።
- እንኳን በደህና መጡ በሚል ፕሮግራም (Welcome Corps) ዘመድዎ ወይም ሌላ ሰው እርሶንወደ አሜሪካ ለማስመጣት ስፖንሰር (sponsor)ወይም የእርሶን ጉዳይ በሙሉ ሃላፊነቱን እሸከማለሁ በሚል ማመልከቻ ቢያስገባ እገዳው ጉዳዮን ይመለከታል። ይህ ፕሮግራም የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አንድ ክፍል ነው። ይሁንና የካቲት (February) 25 ላይ አንድ ዳኛ መንግስት ይህንን እገዳ ማንሳት አለበት የሚል ውሳኔ አሳልፏል። በዚህ የዳኛ ትእዛዝ መሰረት መንግስት እነዚህ ጉዳዮችን መመልከቱን እንደገና መቼ እንደሚጀምር ገና የምናውቀው ነገር የለም።
- እርሶን ወደ አሜሪካን አገር ለማስመጣት ዘመድዎ በመካከለኛው የአሜሪካ ልጆች ፕሮግራም (Central American Minors (ካም CAM) Program) በኩል ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ የስደተኛ ጉዳዮን እገዳው ሊመለከተው ይችላል። ምክንያቱም የካም (CAM) ፕሮግራም የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አካል በመሆኑ። ይሁንና የካቲት (February) 25 ላይ አንድ ዳኛ መንግስት ይህንን እገዳ ማንሳት አለበት የሚል ውሳኔ አሳልፏል። በዚህ የዳኛ ትእዛዝ መሰረት፤ መንግስት እነዚህ ጉዳዮችን መመልከቱን እንደገና መቼ እንደሚጀምር ገና የምናውቀው ነገር የለም። ኢራፕ፣ የዓለም አቀፍ ስደተኞች የእርዳታ ፕሮግራም (IRAP)፤ የካም (CAM) የደሞዝ ክፍያም እንደቆመ ተረድቷል። መንግስት ግን ስለዚህ ጉዳይ የሰጠው ኦፊሲያላዊ መግለጫ የለም። በመሆኑም እኛም በአሁኑ ግዜ ስለዚህ ጉዳይ ዝርዝር መግለጫ የለንም።
ይህ እገዳ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ የበላይ ኮሚሽነር ( ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር UNHCR) ስር ያሉትን ጉዳዮች ይመለከታልን?
አይመለከትም። እገዳው በ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር-(UNHCR) ስር ያሉትን የስደተኞችን ጉዳዮች ወይም ስደተኞችን መልሶ የማቋቋም ስራን በተመለከተ የዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር-(UNHCR) ውሳኔዎችን አይመለከትም። ይሁንና ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር-(UNHCR) ጉዳዮን ወደ አሜሪካ የመልሶ መቋቋምያ ፕሮግራም (USRAP) ካስተላለፈና አሁን እርሶ ያሎት ጉዳይ የ ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) ጉዳዮች አካል ከሆነ፤ እገዳው ጉዳዮን ይመለከታል ማለት ነው።
አሜሪካን አገር ውስጥ በዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP)እንድቋቋም ከተደረኩና በአሁኑ ወቅት አሜሪካን አገር ውስጥ ካለሁ፤ የተደረገው እገዳ በሁኔታዬ ላይ ጫና አለውን?
እገዳው፤ ከአሜሪካን አገር ውጪ ያሉትንና በዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) በኩል ወደ አገር ውስጥ ለመግባት የሚፈልጉትን ነው የሚመለከተው። ያሉት አሜሪካን አገር ውስጥ ከሆነ፤ እገዳው የእርሶን ሁኔታ አይመለከትም። እስኪ ከላይ ያለውን የጽሁፉን ክፍል ይመልከቱና እገዳው ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል በሚል ያስገቡት ማመልከቻ ላይ ጫና ያደርግ መሆኑንና አለመሆኑን ያረጋግጡ።
በዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) በኩል በአሜሪካን አገር እንድቋቋም ከተደረገ ወይም በኤስ-አይ-ቪ (SIV ) በኩል ወደ አሜሪካን አገር ገብቼ የስደተኞች የገንዘብ እርዳታ የማገኝ ከሆነ፤ የትራምፕ አስተዳደር፤ መንግስት ለስደተኞች መልሶ ማቋቋምያ ተቋሞች ይሰጥ የነበረው ገንዘብ እንዲቋረጥ ካደረገ፤ በእኔ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል?
ምናልባት። ከዚህ ከዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) እገዳ ውጪ፤ የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካን አገር ላሉ የመልሶ ማቋቋምያ ተቋሞች፤ መንግስት ለስደተኞች አገልግሎት ይሰጣቸው የነበረውን ገንዘብ እንዳይጠቀሙበት አዟል። አንዳንድ የመልሶ ማቋቋም ተቋሞች ለስደተኞች የሚያደርጉትን አገልግሎት ቀጥለዋል፣ አንዳንድ አገልግሎቶችም ይቋረጡ ወይም በሌላ ይተኩ ይሆናል። ዓለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮግራም ኢራፕ (IRAP) ይህንን የአገልግሎት መስጠት እገዳ ይቃወማል፤ ይህም ያቀረበው ክስ አካል ነው።
ተጨማሪ መረጃና ምንጮች
የአሜሪካ የስደተኞች መልሶ የማቋቋም ሂደት ምንድነው?
ያስገባሁት የሰደተኛ ማመልከቻ ሁኔታ ምን ላይ እንደደረሰ ማወቅ እችላለሁን እንዴት ነው ማወቅ የምችለው?
የዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር ( UNHCR) የመልሶ ማቋቋምያ ሂደት ምንድነው?
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም. ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም. መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ። በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን። |
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.