የአሜሪካን መንግስት፤ ከጥር (January) 20 ቀን 2025 ጀምሮ፤ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር በሚገኙት ሰዎች ላይ ተጽእኖ የሚያደርጉ አያሌ የፖሊሲ ለውጦችን አድርጓል። ከእነዚህ ለውጦች ውስጥ አያሌዎቹ ጠበቃዎችንም ሆነ በዚህ ድንበር በኩል ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚፈልጉትን ሰዎች ገና የሚያደናግሩ ናቸው። እስከአሁን የምናወቀው ነገር እንደሚከተለው ነው፡
ሲ-ቢ-ፒ ዋን (CBP One) ከእንግዲህ በስራ ላይ የለም
በድንበሩ የሚገኙትን የስደተኞችን ቀጠሮ መውሰድ ያስችል የነበረው ይሄው ሲ-ቢ-ፒ ዋን (CBP One) የተባለው ተንቀሳቃሽ መተግበርያ (Mobile App) ከእንግዲህ ስራ ላይ የለም። የአሜሪካን መንግስት ተደርገው የነበሩትን ቀጠሮዎች ሁሉ ሰርዟል። አዲስ ቀጠሮዎችን ማድረግ አይቻልም። በአሁኑ ወቅት ወደ አሜሪካን ድንበር ለመሄድ የሚያስችል ቀጠሮ የመውሰድ ሌላ መንገድ የለም።
ኤም-ፒ-ፒ (MPP) ወይም “ሜክሲኮ ውስጥ ይቆዩ” “Remain in Mexico” ፖሊሲ
የአሜሪካን መንግስት ይህ ኤም-ፒ-ፒ ((MPP) ወይም “ሜክሲኮ ውስጥ ይቆዩ” የተባለው ፖሊሲ እንደገና ተመልሶ በመምጣት ላይ ነው ይላል። ይህ ኤም-ፒ-ፒ ((MPP) ወይም “ሜክሲኮ ውስጥ ይቆዩ” የተባለው ፖሊሲ፤ ሰዎች ጉዳያቸው በአሜሪካ የስደተኞች ፍርድ ቤቶች እንዲሰማላቸው የተሰጣቸው ቀነ-ቀጠሮ እስኪደርስ ድረስ በሜክሲኮ ውስጥ እንዲቆዩ የሚያዝ ፖሊሲ ነው የነበረው። በአሁኑ ወቅት ማን በዚህ ፕሮግራም ውስጥ እንደተጠቃለለ ወይም እንደሚጠቃለል የምናቀው ነገር የለም። የፕሮግራሙ ዝርዝር ሁኔታዎች በአሁኑ ወቅት እንዴት በስራ ላይ ሊውሉ እንደሚችሉም አናውቅም። በበለጠ ስናውቅ ይህንን ገጽ እናድሳለን።
የአሜሪካና የሜክሲኮ ድንበርን የሚነኩ ሌሎች እርምጃዎች
የአሜሪካ መንግስት፤ የአሜሪካና የሜክሲኮ ድንበር ተዘግቷል ብሏል። ይህ በትክክል ምን ማለት እንደሆነ አናውቅም። የአሜሪካ መንግስት ከእንግዲህ ህጋዊ የሆነ መንገድ ያልተጠቀሙ በድንበሩ ያሉ ሰዎችን የማባረር ወይም ወደ አገራቸው የመመለስ መብት አለኝ የሚል ነው የሚመስለው።
የአሜሪካ መንግስት ስደተኞችን በተቀላጠፈ መንገድ ከአገር ለማባረር በመስራት ላይ መሆኑን እናውቃለን። ይህም አብዛኛውን ግዜ ሰዎች መብታቸውን፤ የስደተኛነት ጥያቄ የማቅረብ መብታቸውንም ጭምር፤ ለመጠቀም እንዳይችሉ በጣም ከባድ እክል ይፈጥርባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ሜክሲኮ ድንበር የሚገኙ ሰዎች እንዴት የስደተኛ መብት ለማግኘት መጠየቅ እንደሚችሉ የምናውቀው ነገር የለም።
በበለጠ እያወቅን ስንሄድ እናሳውቃችኋለን
እንደገና፤ በአሁኑ ግዜ፤ ነገሮች ያልተረጋገጡና በፍጥነት የሚቀያየሩ ሆነዋል። ይሁንና ኢራፕ (IRAP) ያገኘውን አዲስ መረጃ ሁሉ ለእናንተ ለማካፈል የበኩሉን ሁሉ ያደርጋል።
ተጨማሪ መረጃ ስናገኝ እናሳውቃችኋለን።