የይዘት ማውጫ
ይህ ጽሁፍ በመጨረሻ የታደሰው ግንቦት (May) 19 ቀን 2025 ነው
አጭር መግለጫ
ይህ ጽሁፍ፤ የአሜሪካ የስደተኞች ማቋቋም ወቅታዊ ፖሊሲዎችንና በፕሬዚደንት ትራምፕ ጥር (January) 20 ቀን 2025 ላይ የተፈረመውን “የማስፈጸምያ ትእዛዝ” (executive order) በተመለከተ ጥያቄ ላላቸው ሰዎች የተዘጋጀ ነው። ይህ አዲስ የማስፈጸሚያ ትእዛዝ፤ የአሜሪካ ስደተኞችን የመቀበል ፕሮግራም ማስተካከያ (Realigning the United States Refugee Admissions Program) በመባል የሚታወቅ ሲሆን የነበረውን የአሜሪካ የስደተኞች የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም (U.S. refugee resettlement program) በይቆይ እንዲያዝ የሚያደርግ ነው።
ይህ ጽሁፍ፤ የማስፈጽሚያ ትእዛዙ ምን እንደሚልና እነኚህ የተደረጉት ለውጦች በወቅቱ የስደተኛ ማመልከቻ ባስገቡና ወደፊት ለማስገባት በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ምን ዓይነት ተጽእኖ ሊኖራቸው እንደሚችል የሚገልጽ ነው። በተጨማሪም ይህ ጽሁፍ፤ ይህንን የስደተኞች የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም በይቆይ እንዲያዝ የሚያደርገውን የመንግስት ትእዛዝ በመቃወም ዓለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮግራም (ኢራፕ-IRAP) ያቀረበው ክስ በትእዛዙ ላይ ምን ተጽእኖ እንደሚያደርግ የሚያስረዳ ነው።
ስደተኞች አሁንም ወደ አሜሪካን አገር መምጣት ይችላሉን?
ይህ ጥያቄ ውስብስብና መልስ ለመስጠት አዳጋች ነው። የሚሰጠው መልስም ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም የሚኖረው ሊሆን ይችላል። ጥያቄውን በደንብ ለመረዳት ከስደተኞች መልሶ ማቋቋም ጋር ስለተያያዘው የማስፈጸምያ ትእዛዝ እንነጋገር። እንዲሁም ይህ ትእዛዝ እንዴት የአገሪቱን ፖሊሲ እንደቀየረና ወደ አሜሪካ ለመመጣት ለሚፈሉጉ ሰዎች ያሉት ወቅታዊ መመርያዎች ምን እንደሆኑ እንመልከት።
የአሜሪካ ስደተኞችን መልሶ የማቋቋም ፕሮግራም፤ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም (United States Refugee Admissions Program) ወይም ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) ይባላል። “የማስፈጸምያ ትእዛዝ” ሲባል ደግሞ መንግስት አንድ ነገር በስራ እንዲተረጎም በፕሬዚደንት የሚሰጥ ኦፊሲያላዊ ትእዛዝ የያዘ ዶኩመንት ነው።
ጥር (January) 20 ቀን 2025፤ ፕሬዚደንት ትራምፕ፤ የአሜሪካ ሰደተኞችን የመቀበል ፕሮግራምን የሚያሻሽል (Realigning the United States Refugee Admissions Program) በመባል የሚታወቅ የማስፈጸምያ ትእዛዝ ሰጡ። ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ፤ የአሜሪካን መንግስት፤ ስደተኞች ወደ አሜሪካን አገር እንዲገቡ የመፍቀድ ፕሮግራሙ ላልተወሰነ ግዜ እንዲቆም የሚያደርግ ነው። ገና ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ የስደተኞች ጉዳዮችም ውሳኔ እንዳይሰጥባቸው ያግዳል።
ፕሬዚደንቱ ይህን ትእዛዝ ካስተላለፉ በኋላ፤ የመንግስት ተቋሞች የስደተኞችን አዲስ ማመልከቻዎች ወድያውኑ መቀበል አቆሙ፣ ገና ውሳኔ ያልተሰጠባቸውን ማመልከቻዎችንም ባሉበት እንዲቆዩ አደረጉ። በተጨማሪም ተቀባይነት አግኝተው ለጉዞ በዝግጅት ላይ የነበሩ ስደተኞች ይዘዋቸው የነበሩ በረራዎችና የጉዞ ዕቅዶችንም ሰረዙ።
የአሜሪካ የስደተኞች ማቋቋም ፕሮግራም (ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አሁንም ገና በይቆይ እንደተያዘ ነውን?
ዓለም አቀፍ የስደተኞች የእርዳታ ፕሮግራም ኢራፕ (IRAP)፤ የአሜሪካን መንግስት ስደተኞችን የመቀበል ፕሮግራምን (ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) እንዲቆም ወይም በይቆይ እንዲያዝ ማድረጉ ህጋዊ አይደለም በማለት በአሜሪካ መንግስት ላይ ክስ መስርቷል። ይህ ጉዳይ አሁንም ገና በፍርድ ቤት እየታየ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት አንድ ዳኛ፤ መንግስት ፕሮግራሙ እንዲቀጥል ማድረግ አለበት ብሎ ውሳኔ ሰጥቷል። ይሁንና ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ፍርድ ቤት በሚሰጣቸው አንዳንድ የተለያዩ ትእዛዞች ምክንያት መንግስት በአሁኑ ግዜ በቅድመ ሁኔታ (conditionally approved) ተቀባይነት ያገኙ ስደተኞችን ጉዳይ ብቻ ተከታትሎ ወደ አሜሪካ እንዲጓዙ መፍቀድ ይጠበቅበታል። እነኚህ በቅድመ ሁኔታ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ስደተኞች፤
- ከጥር ( January) 20 ቀን 2025 በፊት ወደ አሜሪካን አገር እንዲገቡ የተፈቀደላቸው
- ፍርድ ቤቶች፡ ጠንካራ የመተማመኛ ተስፋ (strong reliance interest) ብለው በሰየሙት ጉዳይ ምክንያት እርምጃ የወሰዱ ስደተኞችን ያጠቃልላል።
ክሱ
የካቲት (February) 10 ቀን 2025፤ ኢራፕ( IRAP)-ዓለም አቀፍ የስደተኞች የእርዳታ ፕሮግራም፤ መንግስትን በመቃወም ፓቺቶ አንጻር ትራምፕ (Pacito v. Trump) በሚል ስያሜ በመንግስት ላይ ክስ አቀረበ። ይህ ክስ፤ መንግስት የአሜሪካን የሰደተኞች መቀበል ፕሮግራምን (U.S. Refugee Admissions Program (USRAP) እንዲቆም ማድረጉና በማስፈጸምያ ትእዛዙ ይደረግለት የነበረውን የገንዘብ እርዳታ ማገዱ ከህግ ውጭ ነው በማለት የሚከራከር ነው። ይሄው ክስ፤ በጉዳዩ የተቀመጠው ዳኛ፤ መንግስት በመውሰድ ላይ ያለው የማስፈጸምያ ትእዛዝና ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP)ን ለማቆም የወሰደው እርምጃ ህጋዊ አይደሉም የሚል ውሳኔ እንዲበይን የሚጠይቅ ነው።
ወቅታዊ ሁኔታ
ግንቦት (May) 15 ቀን 2025፤ አንድ ዳኛ በቅድመ ሁኔታ ወደ አሜሪካን አገር እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ስደተኞች ጉዳይና የተጀመረው የጉዞ ሁኔታቸው እንደገና እንዲጀምር አዟል። እነኚህ በቅድመ ሁኔታ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው፤
- ወደ አሜሪካን አገር እንዲገቡ ከጥር ( January) 20 ቀን 2025 በፊት የተፈቀደላቸው
- ፍርድ ቤቶች፤ ጉዳዮችን አንድ በአንድ ተመልክተው “ጠንካራ የመተማመኛ ተስፋ” ባማድረግ አንዳንድ ለውጦችን ያደረጉ ስደተኞች
የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ፤ ከየካቲት 3 ቀን 2025 በፊት እንዲጓዙ ተፈቅዶላቸው የነበሩ ስደተኞች፤ ጠንካራ የመተማመኛ ተስፋ (strong reliance interest”) ያደረጉና ለውጦችን ያደረጉ ብሎ ሰይሟቸዋል። በመሆኑም ጉዳያቸውና ጉዟቸው በተቀላጠፈ ሁኔቴ አሁኑኑ እንዲፈጸምላቸው አዟል። የዚህ ጠንካራ የመተማመኛ ተስፋ (strong reliance interest) ዓይነተኛ ምሳሌ ይከራዩት የነበሩትን መኖርያ ቤት ወይም ስራ መሄዴ ስለሆነ ብለው የለቀቁ ስደተኞችን ይመለከታል፡፡ ሌሎችም ምሳሌዎች አሉ።
በዛው ትእዛዝ ፍርድ ቤቱ፤ ከየካቲት 3 ቀን 2025 በኋላ ለመጓዝ የተፈቀደላቸው ስደተኞችን ጉዳይ የሚመለክትና ውሳኔ የመስጠት ጉዳይ የሚመራ ባለስልጣን እንደሚመድብ አስታውቋል።
የፍርድ ቤቱን ፋይሎችንና ትእዛዞችን እዚህ ላይ በመጫን መመልከት ይችላሉ።
ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ በጉዳዬ ላይ እንዴት ነው ተጽእኖ ሊያደርግ የሚችለው?
ዳኛው፤ መንግስት በመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም ላይ ያደረገውን እገዳ ማንሳት አለበት ብሎ የካቲት (February) 25 ቀን ላይ ትእዛዝ ከማስተላለፉ በፊት፤ መንግስት የስደተኞች ማመልከቻዎች ሁሉ በይቆይ እንዲያዙ አድርጎ ነበር። የስደተኛ የማመልከቻ ሂደቶች መልስ እንድያገኙ የሚያደርጉ እርምጃዎች ሁሉ እንዲቆሙ አድርጎ ነበር። የሚከተሉት ጭምር፡
- አዲስ ማጣቀሻዎችን (referrals) መቀበል
- አዲስ ጉዳዮችን መጀመር
- የቃለመጠይቅ ቀነ-ቀጠሮ መስጠት
- ለጉዳዮች ተቀባይነት መስጠት ወይም ጉዳዮችን አለመቀበል
- የህክምና ምርመራ እንዲደረግ ቀነ- ቀጠሮ መስጠትና
- እርምጃዎቹን በሙሉ ላጠናቀቁ ሰዎች የበረራ ግዜ ማጠናቀር
ይሁንና መንግስት አዲስ የደቡብ አፍሪቃ ፕሮግራም በማውጣት የአንዳንድ የአፍሪካነርስ (Afrikaners) እና የተጎዱ አናሳዎች (disfavored minorities) ጉዳይ ተመልክቷል።
ከእገዳው ውጪ የሆኑ ጉዳዮች አሉን? ይህ አዲስ መመርያ የማይመለከታቸው ጉዳዮች አሉን?
የማስፈጸምያ ትእዛዙ በልዩ የሚመለከታቸው ጉዳዮች ሊኖሩ ይችላሉ ይላል። ይሁንና በልዩ ሊታዩ ይችላሉ የሚላቸው ጉዳዮች የትኞቹ መሆናቸውን አልገለጸም። ትእዛዙ፤ መንግስት የተወሰኑ ጉዳዮችን በልዩነት ሊያይ የሚችለው “ለአገር ጥቅም” ነው የሚል ውሳኔ ሲወስድ ብቻና የሆነ ስደተኛ በአሜሪካ የደህንነት ጥያቄ ላይ አደጋ ሊፈጥር የማይችል መሆኑን ሲያረጋግጥ ብቻ ነው ይላል። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ትእዛዙ አያብራራም። ማንኛውም ጉዳይ በልዩ መታየት ይገባዋል ብሎ የሚወስነው መንግስት ብቻ መሆኑንም ትእዛዙ ያመለክታል።
የአሜሪካ ስደተኛ እርዳታ ፕሮግራም (USRAP)ን አስመልክቼ አዲስ ጉዳይ ልከፍት እችላለሁን?
እኛ እስከምናውቀው ድረስ፤ በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙት አፍሪካነርስ (Afrikaners) እና የተጎዱ አናሳዎች (disfavored minorities) ብቻ ናቸው ወደ አሜሪካ ስደተኞች የእርዳታ ፕሮግራም፤ ለደቡብ አፍሪካውያን ስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም አዲስ ማመልከቻ ማስገባት የሚችሉት።
እገዳው በእንኳን ደህና መጡ ፕሮግራም (Welcome Corps program) ላይ ተጽእኖ ያደርጋልን?
አዎን። የአሜሪካ መንግስት፤ እንደ አንድ የፕሬዚደንቱ የማስፈጸምያ ትእዛዝ መልስ መጠን፤ የእንኳን ደህና መጡ ፕሮግራም (Welcome Corps program) በይቆይ እንዲያዝ አድርጓል። አዲስ የስፖንሰርሺፕ ማመልከቻዎችን የመቀበልና የገቡ ማመልከቻዎችን የመመልከት ሂደት እንዲቆም አድርጓል፤ ይሁንና ከጥር (January) 20 ቀን 2025 በፊት ጉዳያቸው ተቀባይነት ያገኘና የጉዞ ቀናቸው የተመደበ በ እንኳን ደህና መጡ (Welcome Corps) የሚታወቁ ስደተኞች እና ጠንካራ እምነት አሳድረው ከአንዳንድ ሁኔታዎች የተቆጠቡ ስደተኞች ጉዳይና ጉዞአቸው በተግባር ሊተረጎም ይችላል ይላል።
እኔ የአፍጋኒስታን ወይም የኢራቅ ተወላጅ ሆኜ የልዩ ሰደተኛ ቪዛ (Special Immigrant Visa (ኤስ-አይ-ቪ SIV) አመልካች ነኝ። ይህ እገዳ ወይም የትራምፕ አስተዳደር ያደረጋቸው ለውጦች በዚህ ማመልከቻዬ ላይ ተጽእኖ አላቸውን?
ምናልባት።
ማመልከቻዎች ማስገባት፣ ቃለመጠይቆች፣ እና ሌሎች ሂደቶች፡ በኤምባሲና በቆንስሎች የሚገቡ የአፍጋኒስታንና የኢራቅ ስደተኞች ማመልከቻዎች፣ ይህ እገዳ አይመለከታቸውም ምክንያቱም የ ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አካል ስላልሆኑ።
ጉዞ፡ ዓለም አቀፍ የስደተኝነት ድርጅት (International Organization for Migration (አይ-ኦ-ኤም-IOM) የኤስ-አይ-ቪ( SIV)፤ የአፍጋንና የኢራቅ ስደተኞች ሊያደርጉት የነበረውን በረራ አቁሟል። እነኚህ የኤስ-አይ-ቪ( SIV) ካርድ ተሸካሚዎች ግን በራሳቸው ወጪ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን በረራ ሊቀጥሉ ይችላሉ።
የስደተኞች ጠቀሜታዎች፡ የትራምፕ አስተዳደር በወሰደው ሌላ እርምጃ ፤ በኤስ-አይ-ቪ (SIV) በመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም ወደ አሜሪካ የገቡ የኤስ-አይ-ቪ (SIV) ካርድ ተሸካሚዎች፤ መንግስት ባገደው የገንዘብ እርዳታ ምክንያት ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል። ለተጨማሪ መረጃ፤ ከታች የስደተኞች ጠቀሜታዎች በሚል ርእስ የተጻፈውን ክፍል በመመርያው ላይ ያንብቡ።
ይህ እገዳ በ አፍጋን(Afghan) P-1 / P-2 ፕሮግራም በኩል ማመልከቻ ያስገቡትን የአፍጋኒስታን ስደተኞችን ይመለከታልን?
አዎን። ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ፤ በሁሉም የስደተኞች ማመልከቻዎች ላይና በአፍጋን(Afghan) P-1 / P-2 ፕሮግራም በኩል ማመልከቻ ያስገቡትንም ስደተኞች በመጨመር ጫና ያደርጋል።
የአሜሪካ መንግስት፤ ከአፍጋኒስታን ለሚመጡ የአፍጋን ስደተኞች ያደርገው የነበረውን የመጓጓዥያ እርዳታ (CARE relocation)፤ የትራምፕ መንግስት በይቆይ እንዲያዝ አድርጓልን?
ከጥር (January) 28 ቀን 2025 ጀምሮ ፤ የአሜሪካን መንግስት ከአፍጋኒስታን ለሚመጡ ስደተኞች ያደርገው የነበረውን የአይሮፕላን በረራ እርዳታ በይቆይ እንዲያዝ አድርጓል። ምንም እንኳን መንግስት የሰጠው ኦፊሲያላዊ መግለጫ ባይኖርም፤ በዓመቱ መጨረሻ ላይ ፕሮግራሙን በአጠቃላይ ይሰርዘዋል የሚል አንዳንድ ዜና አለ።
የቤተሰቤ አባል የሆነ ሰው እኔ ወደ አሜርካን አገር እንድመጣ ማመልከቻ አስገብቶልኛል። ለመምጣት እችላለሁን?
የአንድ ግለሰብን ጉዳይ በማስመልከት እርግጠኛ መልስ ለመስጠት አንችልም። ይሁንና ይህ ትእዛዝ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንዴት ተጽ እኖ እንደሚያደርግ እናውቃለን።
በዚህ ትእዛዝ የማይነኩ ጉዳዮች
- ዘመድዎ ራሱ ስደተኛ ሆኖ የ I-730 (ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል follow-to-join asylee”) ፕሮግራም ተከትሎ እርሶም ወደ አሜሪካን አገር እንዲገቡ ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ ጉዳዮ በዚህ ትእዛዝ ተጽእኖ አይኖረውም።
- - አሲሊስ (Asylees) ወይም ጥገኞች የሚባሉት በአሜሪካን አገር ውስጥ ያሉና የስደተኛ እውቅና ወረቀት እንዲሰጣቸው አመልክተው ወረቀቱን ያገኙ ሰዎች ናቸው። ይህ ትእዛዝ፤ የቤተሰብ አባል የሆኑና የ I-730 ፎርም ተጠቅመው ወደ አሜሪካን አገር ለመምጣት ማመልከቻ ያስገቡ ሰዎችን አይመለከታቸውም። ምክንያቱም ጉዳያቸው የUSRAP አካል አይደለምና።
- ስለዚሁ የስደተኞች 1-730 ሀግ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይጫኑ።
- I-130: ዘመድዎ የ I -130 (በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘ የስደተኛነት መጠየቅያ ፎርም) በመጠቀም ወደ አሜሪካን አገር ሊያስመጣዎት ከፈለገ፤ ጉዳዮ በማሰፈጸምያ ትእዛዙ አይነካም።
- ይህ I -130 በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘ ስደተኛን ወደ አሜሪካን አገር የማስመጣት ሂደት የሚመለከተው ቤተሰባቸውን ለማስመጣት የሚፈልጉ የአሜሪካ ዜጎችንና ህጋዊ የሆነ የመኖርያ ፈቃድ ( ግሪን ካርድ)ያላቸውን ህጋዊ ሰዎች ነው። ይህ መንገድ የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አካል አይደለም። እዚህ ላይ በመጫን ተጨ ማሪ መረጃ ስለዚህ ጉዳይ ማግኘት ይቻላል።
በዚህ ትእዛዝ የሚነኩ ጉዳዮች
- ዘመድዎ ራሱ ስደተኛ ሆኖ እርሶን ወደ አሜሪካን አገር ለማስመጣት የ I-730 (ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል “follow-to-join asylee”) ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ ጉዳዮ በዚህ ትእዛዝ ተጽእኖ ይኖረዋል። ምክንያቱም በተደረገው እገዳ ምክንያት አያሌ የመንግስት ተቋሞች የጉዳዮን ሂደትና ጉዞዎን በይቆይ እንዲያዙ በማድረጋቸው። ስለዚሁ I-730 ጉዳይ በበለጠ ለመረዳት እዚህ ላይ ይጫኑ።
- “ፕራዮሪቲ 3” (ፒ-3 ) ቤተሰብ እንደገና የማገናኘት ፕሮግራም (“Priority 3” (P-3) Family Reunification program) በመጠቀም ወደ አሜሪካን አገር እንድትገቡ ዘመድዎ ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ የማስፈጸምያ ትእዛዙ በጉዳዮ ላይ ተጽእኖ ያደርጋል።
- የኢራቅ ወይም የሶርያ ተውላጅ ሁነው ዘመድዎ በዚህ ልዩ የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ I-130 (USRAP I-130) ፕሮግራም መሰረት ወደ አሜሪካ እንዲመጡ ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ በዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) በኩል ያደረጉት የስደተኛ ጉዳዮ በእገዳው ተጽእኖ ሊደረግበት ይችላል። ይሁንና ከላይ በተዘረዘረው ሂደት መሰረት፤ በመደበኛው የ1-130 በኩል በሂደት ላይ ያለ የስደተኞች ቪዛ ሂደት ላይ ተጽእኖ የለም።
- በእንኳን ደህና መጡ ፕሮግራም (Welcome Corps) በኩል ዘመድዎ ወይም ማንም ሰው ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ ጉዳዮ በትእዛዙ ተጽእኖ ሊደረስበት ይችላል።
- እርሶን ወደ አሜሪካን አገር ለማስመጣት ዘመድዎ በመካከለኛው የአሜሪካ ልጆች ፕሮግራም (Central American Minors (ካም CAM) Program) በኩል ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ ትእዛዙ የስደተኛ ጉዳዮን ሊመለከት ይችላል። ምክንያቱም የካም (CAM) ፕሮግራም የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አካል በመሆኑ። ኢራፕ (IRAP) ወይም ዓለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮግራም የካም (CAM) ሂደት በይቆይ እንዲያዝ መደረጉን ይረዳል። ይሁንና መንግስት ስለዚህ ጉዳይ ኦፊሲያላዊ የሆነ መግለጫ አልሰጠም። እኛም በአሁኑ ወቅት ዝርዝር መረጃ የለንም።
ይህ በይቆይ ይያዝ የሚለው ትእዛዝ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ የበላይ ኮሚሽነር ( ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር UNHCR) ስር ያሉትን ጉዳዮች ይመለከታልን?
አይመለከትም። እገዳው በ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር-(UNHCR) ስር ያሉትን የስደተኞችን ጉዳዮች ወይም ስደተኞችን መልሶ የማቋቋም ስራን በተመለከተ የሚደረጉ የዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር-(UNHCR) ውሳኔዎችን አይመለከትም። ይሁንና ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር-(UNHCR) ጉዳዮን ወደ አሜሪካ የመልሶ መቋቋምያ ፕሮግራም (USRAP) ካስተላለፈና አሁን እርሶ ያሎት ጉዳይ የ ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) ጉዳዮች አካል ከሆነ፤ እገዳው ጉዳዮን ይመለከታል ማለት ነው።
አሜሪካን አገር ውስጥ በዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) እንድቋቋም ከተደረኩና በአሁኑ ወቅት አሜሪካን አገር ውስጥ ካለሁ፤ የተደረገው የይቆይ ትእዛዝ በሁኔታዬ ላይ ጫና አለውን?
እገዳው፤ ከአሜሪካን አገር ውጪ ያሉትንና በዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) በኩል ወደ አገር ውስጥ ለመግባት የሚፈልጉትን ነው የሚመለከተው። አሁን እርሶ ያሉት አሜሪካን አገር ውስጥ ከሆነ፤ እገዳው የእርሶን ሁኔታ አይመለከትም። እስኪ ከላይ ያለውን የጽሁፉን ክፍል ይመልከቱና እገዳው ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል በሚል ያስገቡት ማመልከቻ ላይ ጫና ያደርግ መሆኑንና አለመሆኑን ያረጋግጡ።
በዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) በኩል በአሜሪካን አገር እንድቋቋም ከተደረገ ወይም በኤስ-አይ-ቪ (SIV ) በኩል ወደ አሜሪካን አገር ገብቼ የስደተኞች የገንዘብ እርዳታ የማገኝ ከሆነ፤ የትራምፕ አስተዳደር፤ መንግስት ለስደተኞች መልሶ ማቋቋምያ ተቋሞች ይሰጥ የነበረው ገንዘብ እንዲቋረጥ ካደረገ፤ በእኔ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል?
ምናልባት። ከዚህ ከዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) እገዳ ውጪ፤ የትራምፕ አስተዳደር በአሜሪካን አገር ላሉ የመልሶ ማቋቋምያ ተቋሞች፤ መንግስት ለስደተኞች አገልግሎት ይሰጣቸው የነበረውን ገንዘብ እንዳይጠቀሙበት አዟል። አንዳንድ የመልሶ ማቋቋም ተቋሞች ለስደተኞች የሚያደርጉትን አገልግሎት ቀጥለዋል፣ አንዳንድ አገልግሎቶችም ይቋረጡ ወይም በሌላ ይተኩ ይሆናል። ዓለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮግራም ኢራፕ (IRAP) ይህንን የአገልግሎት መስጠት እገዳ ይቃወማል፤ ይህም ያቀረበው ክስ አካል ነው።
ተጨማሪ መረጃና ምንጮች
የአሜሪካ የስደተኞች መልሶ የማቋቋም ሂደት ምንድነው?
ያስገባሁት የሰደተኛ ማመልከቻ ሁኔታ ምን ላይ እንደደረሰ እንዴት ነው ማወቅ የምችለው?
የዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር ( UNHCR) የመልሶ ማቋቋም ሂደት ምንድነው?
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.