የይዘት ማውጫ
ይህ ጽሑፍ ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው ኦገስት 20፣ 2026 ዓ.ም.
መመርያው፤ በሃሰት ከኢራፕ ( IRAP) ጋር እሰራለሁ ወይም ኢራፕን (IRAP) እወክላለሁ ከሚል ሰው ጋር በሚገናኙበት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለቦ መረጃ የሚሰጥ ነው።
ኢራፕ የሚሰጠው እርዳታ በሙሉ ነጻ ነው፤
- ህግን በተመለከተ ለምንሰጠው እርዳታ መቼም ግዜ ቢሆን ገንዘብ እንዲከፍሉ ወይም ሌላ አገልግሎት እንዲያደርጉ ፍጹም አንጠይቅም።
- ማንም ከኢራፕ (IRAP) ጋር የተሳሰረ፤ ገንዘብ እንዲከፍሉ ወይም አገልግሎት እንዲያደርጉ የመጠየቅ መብት የለውም።
- የስራ ማመልከቻ ለማስገባት ክፍያ አንጠይቅም።
- ሎተሪ አናደርግም፣ ሽልማት ወይም ገንዘብ አናበረክትም።
- የተጠቃሚ ስሞን (username) ወይም የይለፍ ቃሎን ፓስወርዶን (password.) አንጠይቆትም።
ለሚከተሉት ጉዳዮች ለማንም ገንዘብ መክፈል የለቦትም፡
- ከኢራፕ (IRAP) ጋር ለመገናኘት
- ከኢራፕ (IRAP) የሆነ እገዛ ለማግኘት
- ከዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ማንኛውንም ዓይነት እርዳታ ለማግኘት
- በኢራፕ (IRAP) ውስጥ ስራ ለመፈለግ
ኢራፕ (IRAP) ግኑኝነት የሚያደርገው ኦፊሲያላዊ በሆኑ ስርጦች/ መንገዶች (channels) ብቻ ነው።
- ኢሜል ስንልክሎት መጨረሻቸው @refugeerights.org ከሆኑ የኢሜል አድራሻዎች ብቻ ነው።
- ኢራፕ (IRAP) ሁለት ድህረ-ገጾች (websites) አሉት። እነኚህ ሁለቱ ብቻ ናቸው በኢራፕ IRAP) የሚተዳደሩት፡
- ኢራፕሊጋልኢንፎ.ኦርግ (iraplegalinfo.org)
- ሬፉጂራይትስ.ኦርግ (refugeerights.org)
- የኢራፕ (IRAP) ኦፊሲያላዊ የማህበራዊ ሚድያ መለያዎች (social media accounts) የሚከተሉት ናቸው፡
- ፌስቡክ Facebook
- ቻትቦት ፌስቡክ Facebook Chatbot
- ትዊተር X/Twitter: @IRAP
- ብሉስኪ Bluesky: @irap.bsky.social
- የኢራፕ (IRA) ኦፊሲያላዊ ኢንስታግራም Instagram: @RefugeeAssistance
የማጭበርበር ድርጊት ካጋጠሞት ሪፖርት ማድረግ አለቦት።
የኢራፕ (IRAP) ሰራተኛ ያልሆነ ሰው፤ የኢራፕ (IRAP) ሰራተኛ ነኝ ብሎ በሃሰት የሚናገር ሰው ካጋጠሞት፤ እባኮን ወደ fraudalert@refugeerights.org. ኢሜል ያድርጉ። ይህ የኢሜል አድራሻ የማጭበርበርያ ሪፖርት ብቻ የሚቀበል ኢሜል ነው። ኢራፕ ( IRAP) ይህንን ኢሜል የህግ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን ጥያቄ ለመመለስ አይጠቀምበትም።
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.