የይዘት ማውጫ
አጭር መግለጫ
የስደተኞች መልሶ ማቋቋም ፕሮግራም፤ በተለይም በአሜሪካ፤ ረጂም ግዜ የሚፈጅ ነው። በአያሌ ጉዳዮችም ላይ ብዙ ዓመታት ሊወስድ ይችላል።
በአንዳንድ ሁኔታዎች፤ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) የቀረቡት ሰዎች በእርግጥ ስደተኞች ናቸው ወይስ አይደሉም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ መጀመርያ ቃለመጠይቅ ያደርግላቸዋል። ይህም የስደተኞች ማጣርያ ውሳኔ (refugee status determination) በመባል ይታወቃል። የኢራፕ መመርያ ስለ ስደተኞች ማጣርያ ሂደት የሚከተለውን ይጫኑ።
የሚያሳዝነው ግን፤ አያሌ ስደተኞች በዚህ በመልሶ ማቋቋምያ ፕሮግራም ውስጥ እንዲገቡ አይደረግም። በመሆኑም በጣም ጥቂቶች ብቻ ናቸው በፕሮግራሙ ውስጥ ገብተው መልሰው እንዲቋቋሙ የሚደረጉት። አብዛኛውን ግዜ፤ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) አንድ ስደተኛ ወደ ሶስተኛ አገር ተልኮ እንዲቋቋም ለመወሰን የሚያስፈልገው ቢያንስ አንድ ቃለመጠይቅ ነው። ይህ የቃለመጠይቅ ሂደት ግን አያሌ ወራት ወይም ከዛ በላይ ግዜ ሊወስድ ይችላል።
ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) አንድ ስደተኛ በሶስተኛ አገር ሂዶ መልሶ እንዲቋቋም ከወሰነ፤ የስደተኛውን ፋይል ወይም መዝገብ ወደ ሶስተኛው አገር ይልካል። የስደተኛ መዝገብ፤ ከዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ወደ ሌላ አገር መንግስት መላክ አያሌ ወራት ይፈጃል።
አብዛኛውን ግዜ፤ አመልካቾች የት አገር መቋቋም እንደሚፈልጉ መምረጥ አይችሉም። ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR)፤ ስደተኛው የሚፈልገውን አገር፤ ዘመዶቹ የት እንደሚኖሩ፤ የሚሄድበት አገር የቋንቋ ችሎታ አለውን የመሳሰሉትን ግምት ውስጥ ሊያስገባ ይችላል። የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጠው ራሱ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ብቻ ነው።
አንዳንዴ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) አንድ ስደተኛን ለመልሶ መቋቋም ፕሮግራም ቃለመጠይቅ ያደርግና ለማንም መንግስት ሳያስተላልፈው ሃሳቡን ሊቀይር ይችላል። ይህም በአያሌ ምክንያቶች ሊሆን ይችላል። ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR)፤ ይህ ቃለመጠይቅ የተደረገለት ሰው ምናልባት በአስቸኳይ መልሶ መቋቋም ያስፈልጋቸዋል ከሚባሉት ውስጥ በአስቸኳይ መቋቋም የማያስፈልገው ሊሆን ይችላል፣ አንዳንዴም ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ስደተኛው ባለው አንዳንድ መስፈርቶች ምክንያት የአገሪቱ ምክንያት መንግስት አይቀበለውም የሚል ሃሳብ ሊኖረው ይችላል።
ከመንግስት ጋር የተያያዙ የመልሶ መቋቋም እርምጃዎች
ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) አንድን ስደተኛ ወደ አንድ መንግስት አንዴ ካስተላለፈው በኋላ፤ ያ መንግስት ነው ስደተኛውን መልሶ ለማቋቋም ወይም ላለማቋቋም የሚወስነው። መንግስት የሚወስደው የእርምጃ ሂደትም ብዙ ወራት ወይም ከዛ በላይ ሊወስድ ይችላል። ይህ ሂደት ለአሜሪካ አያሌ ዓመታት ሊወስድ ይችላል። አብዛኛዎቹ መንግስታትም፤ ስደተኛውን መልሶ ለማቋቋም የመጨረሻ ውሳኔአቸውን ከመውሰዳቸው በፊት ቃለመጠይቅ ለማድረግ፣ የግለሰቡ መዝገቦችን በሙሉ ለማግኘት ይፈልጋሉ። ሌሎች አያሌ መንግስታትም ተጨማሪ ቅድመ-ሁኔታዎች ይኖራቸዋል።
መንግስታት፤ ስደተኞች በመልሶ መቋቋም ፕሮግራም ውስጥ እንዲገቡ ላይቀበሉ ይችላሉ። በአሜሪካን አገር የመልሶ መቋቋምያ ፕሮግራም ውስጥ እንዲገቡ ፈቃድ ያላገኙትን ስደተኞች በሚመለከት ኢራፕ (IRAP) መረጃ አለው። እሱንም እዚህ ላይ ይጫኑ።
መልሰው የተቋቋሙ ስደተኞች ከትዳር ጓደኛቸውና ለአቅመ አዳም ካልደረሱ ልጆቻቸው ጋር አብዛኛውን ግዜ ለመጓዝ ይችላሉ። መንግስታት የቤተሰብ ቅልቅልን በተመለከተ የተለያዩ ገደቦች አሏቸው። በካናዳ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ በስዊድንና በአሜሪካ የቤተሰብ መቀላቀል ምን እንደሚመስል ኢራፕ (IRAP) መረጃ አለው።
የዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ሂደቶችንና መስፈርቶችን የያዘ መጽሄት ለማግኘት የሚከተለው ላይ ይጫኑ።
ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ወይም መንግስት በመልሶ መቋቋም ፕሮግራም ውስጥ እንዲገቡ ግምት ውስጥ ካስገባዎት በኋላ፤ ሂደቱ አያሌ ዓመታት እንደሚፈጅ ማወቅ አለቦት። በተጨማሪም የሚከተሉትን ማድረግ አለቦት፤
- በዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ውስጥ ያሉ ባለስልጣኖች ወይም የአገሪቱ መንግስት መስርያ ቤት አድራሻዎትንና እርሶን ቢያጡ ሊያገኙት የሚችሉ ሰው አድራሻ እንዳላቸው ማረጋገጥ።
- ለሚጠየቁት ጥያቄዎች ተገቢ መልስ መስጠት፣ መረጃዎችን እንዲሰጡ ሲጠየቁ መስጠት
- የተደረገሎትን ቀነ-ቀጠሮችን ሁሉ በደንብ ማክበር፤ በቀጠሮ ቀናቱ መገኘት የማይችሉ ከሆነ ለባለስልጣናቱ አስቀድሞ ማስታወቅ።
መልሶ መቋቋምያ ፕሮግራም ወደ አላቸው አገሮች ለመሄድ ሌላ ዘዴ አለን?
መንግስታት፤ ስደተኞች በህጋዊ መንገድ ወደ ሌሎች አገሮች መሄድ የሚችሉባቸው ሌሎች የተወሰኑ አማራጮችን ይሰጣሉ። በአንዳንድ ጉዳዮች፤ ስደተኞች ከቤተስብ ጋር ለመቀላቀል ብቁ ከሆኑና የሚሄዱበት አገር ውስጥ ስራ ካገኙ፤ ለመሄድ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለእነዚህ ዘዴዎች ኢራፕ (IRAP) ህጋዊ የሆነ መረጃ አለው፡ የሚከተሉትን ይጨምራል፡
- ለአሜሪካ ሰራዊት የሰሩ የአፍጋንና የኢራቅ ተወላጆች ስለሚሰጣቸው ቪዛ ለማወቅ ከፈለጉ የሚከተለውን ይጫኑ፡ ለአሜሪካ ሰራዊት የሰሩ የአፍጋንና የኢራቅ ተወላጆች ስለሚሰጣቸው ቪዛ።
- ከቤተሰብ ጋር ስለመቀላቀል ኢራፕ ስላለው መረጃ እዚህ ላይ ይጫኑ፤ የኢራፕ (IRAP) መረጃ ስለከቤተሰብ ጋር መቀላቀል ይህ እንደ ካናዳ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን፣ ስዊድንና አሜሪካ በመሳሰሉት አገሮች የቅርብ ቤተሰብ ያላቸው አንዳንድ ስደተኞች ወደ እነዚህ አገሮች እንዲሄዱ የሚፈቅድ ነው።
እንዴት ነው ኢራፕ ( IRAP) በዚህ የመልሶ መቋቋም ፕሮግራም ሂደት ሊረዳኝ የሚችለው?
ኢራፕ (IRAP) የማንኛውም መንግስት ወይም የዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) አካል አይደለም። ኢራፕ (IRAP)፤ የመልሶ መቋቋም ጉዳዮን ለመንግስት እንዲያቀርቡ መወስን አይችልም። ኢራፕ (IRAP)፤ ማንኛውም መንግስት የመልሶ መቋቋም ጉዳዮን እንዲቀበል ሊወስን አይችልም። ቪዛ በማግኘትና በሌሎች መንገዶች ላይ ውሳኔ ሊያደርግ አይችልም። ኢራፕ (IRAP) የገንዘብ እርዳታ አይሰጥም። መኖርያ ቤት እንዲያገኙ አይረዳም፣ የቤት ኪራይ የሚከፍሉበት ገንዘብ አይሰጥም፣ ስራ እንድታገኙም እርዳታ አያደርግም።
ኢራፕ (IRAP) በሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሰዎችን ሊረዳ ይችላል፡
- ኢራፕ (IRAP)፤ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር ( UNHCR) በአንዳንድ አገሮች፤ አንዳንድ ስደተኞችን እንዲረዳ ሊጠይቅ ይችላል። ስደተኞቹ፤
- የግላቸው የሆነ በህይወታቸው ወይም በአካላቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል የሚል ስጋት ካለ
- ህይወታቸውን ወይም የአካል እንቅስቃሴያቸውን የሚፈታተን የጤና እክል ያጋጠማቸውና የሕክምና እንክብካቤ የማያገኙ ከሆነ
ኢራፕ (IRAP) የሚከተሉትን በተመለከተ ምክር ወይም እርዳታ ሊያደርግ ይችላል፡
- አንድ ጥገኝነት ለማግኘት የሚሞክር ሰው፤ በዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) እንደ ስደተኛ እንዲታወቅ ሲፈልግ
- ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ወይም አንድ መንግስት አንድን ስደተኛ በመልሶ መቋቋምያ ፕሮግራም ውስጥ እንዲገባ ግምት ውስጥ ሲያስገቡት
- አንድ ስደተኛ፤ ወደ ሌሎች አገሮች ሂዶ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀያ ቪዛ የመሰለ ሌላ ዓይነት ቪዛ ለማግኘት ብቁ ሲሆን
የኢራፕ (IRAP)ን እርዳታ ስለመጠይቅ እዚህ ላይ መረጃ አለ።
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.