የይዘት ማውጫ
ይህ ጽሁፍ ግንቦት (May) 20 ቀን 2025 ታደሰ
አጭር መግለጫ
በአሜሪካን አገር ውስጥ ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች ዘመዶቻቸው አሜሪካን አገር መጥተው እንዲቀላቀሏቸው ማመልከት ይችላሉ። ይህ መመርያ ከቤተሰብ ጋር መቀላቀልን በማስመልከት የሚደረጉ ማመልከቻዎችን የሚዘረዝር ነው። ይህ ዝርዝር ግን በቤተሰብ ላይ የተመረኮዙ ፕሮግራሞችን በሙሉ አይሸፍንም።
በቤተሰብ የመቀላቀል ፕሮግራሞች ብቁ ሆኖ መገኘት፤ አብዛኛውን ግዜ፤ በእነዚህ በሚቀጥሉት ላይ የተመረኮዘ ነው፤
- በአሜሪካን አገር ውስጥ ያለው ግለሰብ ህጋዊ የሆነ ወረቀት ያለው መሆን አለበት።
- በአሜሪካን አገር ውስጥ ባለው ሰውና ከሌላ አገር በሚመጣው ሰው መካከል ያለው ዝምድና
የሚከተሉትንም በደንብ መረዳት አስፈላጊ ነው፤
- በአሜሪካን አገር ያለው ሰው፤ ከዘመዱ ጋር ለመቀላቀል ብቁ የሚያደርጉት ዶኩመንቶች ወይም ማረጋገጫዎች እንዲያቀርብ ይህንን የሚመለከቱ ፕሮግራሞች ሁሉ ይጠይቃሉ።
- አንዳንድ ፕሮግራሞች የተወሰኑ የማመልከቻ ማስገብያ የመጨረሻ ቀናት ወይም የሚከፈል ገንዘብ አላቸው። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ያንኑ አንዱን ዘመድ እንዲመጣ ለማገዝ ከአንድ ፕሮግራም በላይ ውስጥ ማመልከቻ ማስገባት አስፈላጊ የሚሆንበት ግዜ አለ። ።
- በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች፤ ራቅ ያሉ ዘመዶችን ለማስመጣት የሚያስችል ትርጉም ያለው ፕሮግራም የለም።
ለእያንዳንዱ ፕሮግራም፤ ይህ መመርያ፤ ለተጨማሪ መረጃ ወደ ሌሎች መገናኛዎች የሚመራ ነው።
የአሜሪካ ዜጎችና በአሜሪካን አገር ያሉ ህጋዊ ቋሚ ተቀማጮች
የአሜሪካ ዜጎችና በአሜሪካን አገር ህጋዊና ቋሚ ተቀማጮች፤ ዘመዳቸው ወደ አሜሪካን አገር እንዲመጣ ማመልከት ይችላሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች ምክንያት ግን እነኚህ ማመልከቻ የገባላቸው ሰዎች ወደ አሜሪካን አገር ከመምጣታቸው በፊት አያሌ ዓመታት ሊያልፉ ይችላሉ። .
ህጋዊና ቋሚ ተቀማጮች (Lawful permanent residents (LPRs) አንዳንዴ የግሪን ካርድ ያዦች (green card holders) በመባል ይታወቃሉ። እነኚህ የትዳር ጓደኛቸው ወይም ያላገቡ ልጆቻቸው ወደ አሜሪካን አገር እንዲመጧላቸው ማመልከት ይችላሉ።
የአሜሪካ ዜጎች፤ ለትዳር ጓደኛቸውና በማንኛውም የዕድሜ ክልል ላሉት ያገቡም ያላገቡም ልጆቻቸው ወደ አሜሪካን አገር እንዲመጡ ሊያመለክቱ ይችላሉ። ዕድሜያቸው ከ 21 ዓመት በላይ የሆኑ የአሜሪካ ዜጎች፤ እህትና ወንደማቸው እንዲሁም ወላጆችቻቸው እንዲመጡላቸው ማመልከት ይችላሉ።
የዚህን ማመልከቻ ሂደት ለመጀመር፤ ግለሰቦች አይ-130 (I-130) የተባለ ፎርም መሙላት አለባቸው። ስለዚሁ ፎርም አይ-130 (I-130) ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።
በመጨረሻም፤ የአሜሪካ ዜጎች፤ ገና ከመጋባታቸው በፊት እጮኛቸው ወደ አሜሪካን አገር እንዲመጡም ማመልከት ይችላሉ። ይህንን ሂደት ለመጀመር የሚሞላው ፎርም I-129 ኤፍ (I-129F) ይባላል። ይህንን እጮኛን የማስመጣት ሂደት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ላይ ይገኛል።
የሶርያና የኢራቅ፟ ተወላጆች ዘመዶች ያሏቸው የአሜሪካ ዜጎችና ህጋዊ ቋሚ ተቀማጮች
ቀደም ሲል፤ ተቀባይነት ያገኘ የI-130 የኢራቅ፟ ወይም የሶርያ ዜጋ አመልካች (ከላይ እንደተጠቀሰው) በአሜሪካን አገር የስደተኛ ወረቀት እንዲሰጠው ማመልከት ይችል ነበር። ይሁንና ጥር (January) 2025 ላይ ፕሬዚደንት ትራምፕ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም (U.S. Refugee Admissions Program (ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ USRAP) ስራውን እንዲያቆም ትእዛዝ አስተላለፉ። የኢራቅና የሶርያ ቀጥታዊ የመግብያ ፕሮግራሞችም የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አካል በመሆናቸው እንዲቆሙ ተደርገዋል። ይህም ማለት በአሁኑ ግዜ ይህንን በተመለከተ የአሜሪካን መንግስት ማንኛውንም አዲስ ማማልከቻ አይቀበልም።
ስለዚሁ የስደተኞች ማቋቋምያ ፕሮግራም ስራ ማቆም ተጨማሪ መረጃ እዚህ ላይ ይገኛል።
የኮሎምቢያ፣ የኩባ፣ የኤኮዶር፣ የጓተማላ፣ የሄቲ ወይም የኤልሳልቮዶር ተወላጆች የሆኑ ዘመዶች ያሏቸው የአሜሪካ ዜጎች እና የአሜሪካ ህጋዊና ቋሚ ተቀማጮች
የኮሎምቢያ፣ የኩባ፣ የኤኮዶር፣ የጓተማላ፣ የሄቲ ወይም የኤልሳልቮዶር ተወላጆች የሆኑ ዘመዶች ያሏቸው የአሜሪካ ዜጎች እና የአሜሪካ ህጋዊና ቋሚ ተቀማጮች፤ ቀደም ሲል የቤተሰብ ቅልቅል ዋስትና ( Family Reunification Parole (ኤፍ-አር-ፒ-FRP) በተባለው ፕሮግራም ከእነዚህ ከተጠቀሱት አገሮች ቤተሰቦቻቸውን ማምጣት ይችሉ ነበር። ይሁንና የአሜሪካን መንግስት ከ ጥር (January) 2025 ጀምሮ በዚህ ኤፍ-አር-ፒ-(FRP) በኩል ማመልከቻ መቀበሉ እንዲቋረጥ አድርጓል። የአሜሪካ ዜጎች እና የአሜሪካ ህጋዊና ቋሚ ተቀማጮች በዚህ በአይ-130 ፎርም በኩል አሁንም ገና ዘመዶቻቸውን ለማስመጣት ማመልከቻ ማስገባት መቀጠል ይችላሉ። ስለዚሁ የአይ-130 ሂደት ተጫማሪ መረጃ አዚህ ላይ ማግኘት ይቻላል።
በአሜሪካን አገር ውስጥ ስለሚገኙ ስደተኞችና ጥገኞች
የጥገኛ ወረቀት ያገኙ ሰዎች ከትዳር ጓደኛቸው ጋር ለመቀላቀል እንዲችሉ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ። የልጆቻቸው ዕድሜና የትዳር ሁኔታ ግምት ውስጥ ገብቶ ከልጆቻቸው ጋርም ለመቀላልቀል ማመልከት ይችላሉ። ይህንንም ለማሳካት ፎርም አይ-730 (I-730) የተባለ ፎርም መሙላት አለባቸው። ይህ ፕሮግራም የሁለት-ዓመት የግዜ ገደብ አለው። ስለዚሁ ፎርም አይ-730 (I-730) ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይገኛል።
ልክ እንደ ጥገኞች፤ በአሜሪካን አገር ውስጥ እንደስደተኛ ተቀባይነት አግኝተው አገር ውስጥ የተቋቋሙ ስደተኞችም የትዳር ጓደኞቻቸውንና ከ21 ዓመት ዕድሜ በታች የሆኑ ያላገቡ ልጆቻቸውን በአይ-730 ( I-730) ፎርም ለማስመጣት ይችላሉ። ይሁንና ጥር (January) 2025 ላይ ፕሬዚደንት ትራምፕ ይህ የአሜሪካ ስደተኞችን የመቀበል ፕሮግራም (U.S. Refugee Admissions Program (USRAP) እንዲቆም ትእዛዝ አስተላለፉ። በዚህ የማቆም ትእዛዝም፤ በተቋቋሙ ስደተኞች ስም የገቡ የአይ-730 (I-730) ፎርም ማመልከቻዎች ሁሉ ተጎድተዋል። ስለዚሁ የአይ-730 (I-730) ፎርም ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል። እንዲሁም በወቅቱ ስለተደረገው የመልሶ መቋቋም የመቆም ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የጥገኛና የስደተኛ ወረቀት ላላቸው ሰዎች የሚያገለግል፣ ከአፍጋኒስታንና ከኢራቅ፟ ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም ልዩ የስደተኛ ቪዛ ኤስ-አይ-ቪ (SIV) ያላቸውን ሊያመጡበት የሚያስችል ፕራዮሪቲ 3 (Priority 3) የተባለ ከቤተሰብ ጋር የሚያቀላቅል ሌላ ፕሮግራምም አለ። ይሁንና ጥር (January) 2025 ላይ ፕሬዚደንት ትራምፕ ይህ የአሜሪካ ስደተኞችን የመቀበል ፕሮግራም (U.S. Refugee Admissions Program (USRAP) እንዲቆም ትእዛዝ አስተላለፉ። በአሁኑ ወቅት ይህ ፕራዮሪቲ 3 (Priority 3) የተባለ ፕሮግራም ምንም ዓይነት አዲስ ማመልከቻ አይቀበልም። ስለዚሁ ፕራዮሪቲ 3 ( Priority 3) የተባለ ፕሮግራም ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ይገኛል። በወቅቱ ስለተደረገው የፕሮግራሙ መቆምም ተጨማሪ መረጃ እዚህ አለ።
ልዩ የኢሚግሬሽን ቪዛ (SIV) ያላቸው በአሜሪካን አገር ውስጥ የሚገኙ የኢራቅና የአፍጋኒስታን ተወላጆች
ልዩ የስደተኛ ቪዛ (Special Immigrant Visa ኤስ-አይ-ቪ- SIV) ያላቸው የኢራቅና የአፍጋን ተወላጆችም የትዳር ጓደኞቻቸው እና ልጆቻቸውን ወደ አገር ለማስመጣት በአንዳንድ ሁኔታዎች ማመልከት ይችላሉ። ይህም “ልዩ የስደተኛ ቪዛ ተከትሎ መቀላቀል” ወይም “ፋሎዊንግ ቱ ጆይን” ተብሎ ይጠራል። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በዚህ የኢራፕ (IRAP) ልዩ የስደተኛ ቪዛ ያላቸው ሰዎችን ዘመዶች የማስመጣት መመርያ ውስጥ ያገኛሉ።
ከትዳር ጓደኞቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር የተለያዩ ምህረት የተደረገላቸው (parolees) የአፍጋን ተወላጆች
የአሜሪካ የአገር ውስጥ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ( Department of State) ስለ አፍጋኒስታን ተወላጆች የቤተሰብ ቅልቅል ዌብሳይት አለው። ይሄው ዌብሳይት ከአገራቸው ወደ አሜሪካን አገር እንዲሰደዱ የተደረጉ፤ የፔሮል (parole) ወረቀት ያገኙና በዛው ሂደት እንዲቆዩ የተደረጉ ወይም ግዜያዊ የጥበቃ ዋስትና የተሰጣቸው የአፍጋን ተወላጆች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ የሚያመለክቱበት ፎርም የያዘ ነው። ይህ ፎርም ዲ-ኤስ-4317 (DS-4317) ይባላል፣ እዚህም ይገኛል።
አሜሪካን አገር ውስጥ ዘመዶች ያሏቸው የኢራን የሃይማኖት አናሳዎች
ቀደም ሲል፤ የሎተንበርግ ፕሮግራም (Lautenberg Program) በሚባል ፕሮግራም አማካኝነት፤ በአሜሪካን አገር ህጋዊ ተቀማጮች የሆኑ የኢራን ዜጎች የአገራቸውን የሃይማኖት አናሳዎችን በአሜሪካ እንዲቋቋሙ መርዳት ይችሉ ነበር። ይሁንና ጥር January 2025 ፕሬዚደንት ትራምፕ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበል ፕሮግራም (U.S. Refugee Admissions Program (ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ- USRAP) ስራውን እንዲያቆም ትእዛዝ አስተላለፉ። ይሄው ፕሮግራምም የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) አካል በመሆኑ በአሁኑ ወቅት አዲስ ማመልከቻዎችን አይቀበልም። ስለዚሁ የዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ ፕሮግራም( Lautenberg Program) ተጨማሪ መረጃ ከፈልጉ እዚህ ይገኛል። እንዲሁም ስለ ወቅቱ መልሶ ማቋቋምያ ፕሮግራም መቆምም ተጨማሪ መረጃ እዚህ አለ።
በአሜሪካን አገር ውስጥ ዘመድ ያላቸው የኤልሳልቫዶር፣ የጓቴማላና የሆንዱራስ ዜጎች
የመካከለኛው አሜሪካ የልጆች ፕሮግራም (Central American Minors (ካም-CAM)፤ በኤልሳልቫዶር፣ በጓቴማላና በሆንዱራስ የሚገኙና በላያቸው ላይ ግፍ እንዳይፈጸምባቸው የሚፈሩ ወይም ግፍ የተፈጸመባቸው ልጆች ወይም ሌሎች የቤተሰብ አባሎች፤ በህጋዊ መንገድ አሜሪካን አገር ውስጥ ካሉት ወላጆቻቸው ጋር መቀላቀል የሚችሉበት ህጋዊ መንገድ አለ። ይሁንና ጥር (January) 2025 ፕሬዚደንት ትራምፕ ይህ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም (U.S. Refugee Admissions Program (ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ-USRAP) እንዲቆም ትእዛዝ አስተላለፉ። ይህ የካም (CAM) ፕሮግራም የ ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ-(USRAP) ፕሮግራም አካል ስለሆነ በአሁኑ ወቅት አዲስ ማመልከቻ መቀበሉን አቁሟል። ስለዚሁ የካም (CAM) ፕሮግራም ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ አለ። እንዲሁም ስለ ወቅታዊ የመልሶ መቋቋም ፕሮግራም ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እሱም እዚህ ይገኛል።
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.