የይዘት ማውጫ
እስከ ታህሳስ 22 ድረስ የአሜሪካ መንግስት የሚከተሉትን ለውጦች አስታውቋል፡
- በሰኔ እና ታህሳስ 2025 የጉዞ እገዳዎች ውስጥ ከተዘረዘሩት አገሮች የመጡ ሰዎች የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎቶች (USCIS) ማመልከቻዎች በሙሉ ለጊዜው ተቋርጠዋል።
- ሁሉም የጥገኝነት ውሳኔዎች ተቋርጠዋል።
- የአሜሪካ የዜግነት እና የኢሚግሬሽን አገልግሎቶች (USCIS) መኮንኖች አንድ ሰው ከአገር የጉዞ እገዳ የመጣ መሆኑን ወይም አለመሆኑን እንደ አረንጓዴ ካርዶች ያሉ የጥገኝነት ማመልከቻዎችን የመወሰን አማራጭ ያላቸውን ማመልከቻዎች መወሰን ይችላሉ። ምንም እንኳን USCIS በሰኔ 2025 የጉዞ እገዳ ውስጥ ከተዘረዘሩት አገሮች የመጡ ሰዎች በዚህ ፖሊሲ ላይ ለውጦችን ብቻ ቢያሳውቅም፣ ለውጦቹ በታህሳስ 2025 የጉዞ እገዳ ውስጥ ከተዘረዘሩት አገሮች የመጡ ሰዎችም ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ።
- የአሜሪካ መንግስት ከ2021 ጀምሮ ወደ አሜሪካ የመጡት በሰኔ እና ታህሳስ 2025 የጉዞ እገዳዎች ውስጥ ከተካተቱት አገሮች የመጡ ሰዎች ቀደም ሲል የጸደቁ የኢሚግሬሽን ማመልከቻዎችን ይገመግማል።
ስለእነዚህ ዝመናዎች የበለጠ እዚህ ማወቅ ይችላሉ።
ይህ ጽሁፍ ህዳር (December) 17 ቀን 2025 ታደሰ
አጭር መግለጫ
ይህ ጽሁፍ፤ ከአሜሪካን አገር ውጪ የሚገኙና “ሙሉ በሙሉ እገዳ ከተደረገባቸው” አገሮች የሆኑ ሰዎች፤ ወደ አሜሪካን አገር እንዳይገቡ በቅርቡ ስለወጣው የጉዞ እገዳ መረጃ የሚሰጥ ነው። “ከአንድ አገር” ኖት ስንል የዝያ አገር ዜግነት አሎት ማለታችን ነው። ከተጠቀሱት አገሮች ውስጥ በአንዱ የተወለዱ ሆነው ግን የዚያ አገር ዜጋ ካልሆኑ፤ ይህ መረጃ አይመለከቶትም።
ከጥር (January) 1 ቀን 2026 ጀምሮ እነዚያ “ሙሉ በሙሉ” የታገዱ አገሮች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፤
አፍጋኒስታን (Afghanistan)፣ ቡርኪና ፋሶ (Burkina Faso)፣ በርማ (Burma)፣ ቻድ (Chad)፣ የኮንጎ ሪፑብሊክ (Republic of the Congo)፣ ኤኮቶሪያል ጊኒ (Equatorial Guinea)፣ ኤርትራ (Eritrea)፣ ሄይቲ (Haiti)፣ ኢራን (Iran)፣ ላዎስ (Laos)፣ ሊብያ (Libya)፣ ማሊ (Mali)፣ ኒጀር (Niger)፣ ሴራ ሊዮን (Sierra Leone)፣ ሶማሌ (Somalia)፣ ደቡብ ሱዳን (South Sudan)፣ ሱዳን (Sudan)፣ ሲሪያ (Syria) እና የመን (Yemen) ። ይህ ዝርዝር በፊሊስጤም ባለስልጣን የተሰጠ የጉዞ ዶኩመንት ያላቸውንም ሰዎች ያጠቃልላል።
በሰኔ (June) ወር 2025 ላይ የወጣው “ሙሉ በሙሉ የታገዱ” አገሮች ዝርዝር ከዚህ ከአሁኑ ጋር ሲወዳደር የሚከተሉትን አገሮች የሚያጠቃልል ነበር፤ አፍጋኒስታን (Afghanistan)፣ በርማ ( Burma)፣ ቻድ (Chad)፣ የኮንጎ ሪፑብሊክ (Republic of the Congo)፣ ኤኳቶሪያል ጊኒ (Equatorial Guinea)፣ ኤርትራ (Eritrea)፣ ሄይቲ (Haiti)፣ ኢራን (Iran)፣ ሊብያ (Libya)፣ ሴራ ሊዮን (Sierra Leone)፣ ሶማሌ (Somalia)፣ ሱዳን (Sudan) እና የመን(Yemen)።
የሚከተለውን ማስታወስ አስፈላአጊ ነው፡
- እርስዎ ወይም የቤተሰቦ አባል ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት የምትችሉበት ሁኔታ በአያሌ የተለያዩ መስፈርቶች ላይ የተመረኮዘ ነው፡ ምን ዓይነት ቪዛ ለማግኘት ነው ያመለከቱት፣ ከየት አገር ናችሁ እና በአሁኑ ወቅት ያላችሁበት ቦታ የት ነው በሚሉ ጥያቄዎች መልስ ላይ የተመረኮዘ ነው።
- እያንዳንዱ ጉዳይ ከሌላው የተለየ ነው። ይህ እርሶን እንዴት እንደሚመለከትዎ ለማወቅ ከኢሚግሬሽን ጠበቃ ጋር ተነጋገሩ።
ስለ ጉዞው እገዳ ጠቅላላ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይጫኑ።
በጉዞው እገዳ ዝርዝር ላይ ከሌላ አገር ከሆኑ እዚህ ላይ ይጫኑ።
የሚገኙት አሜሪካን አገር ውስጥ ሆኖ ግን ከተጠቀሱት አገሮች ውስጥ ከሆኑ፤ እዚህ ላይ ይጫኑ።
“ሙሉ በሙሉ” ከታገዱት አገሮች ለሆኑ ሰዎች የጉዞው እገዳ ደንቦች ምንድናቸው?
“ሙሉ በሙሉ” ከታገዱት አገሮች ውስጥ ከሆኑ፤ ልዩ ለሚያስደርጎት ነጥብ ብቁ ካልሆኑ በስተቀረ፤ ማንኛውም ዓይነት ቪዛ ቢጠቀሙ በአጠቃላይ ወደ አሜሪካን አገር ፍጹም አይገቡም። ይህ ጽሁፍ፤ ሙሉ በሙሉ ከታገዱ አገሮች ውስጥ ከሆኑ፤ ጉዳዮን ልዩ የሚያደርጎትን ሁኔታዎችንና ልዩ ደንቦችን አንዳንዱን ያስረዳል።
ከተከለከሉት ቪዛዎች ውስጥ ለማግኘት ከሆነ በማመልከት ላይ የሚገኙት፤ የአሜሪካ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር (U.S. Department of ) ቃለመጠይቅ እንዲያደርጉ ቀጠሮ ሊያደርግሎት ይችላል። ይሁንና ቃለመጠይቁን የሚያደርግሎት ባለስልጣን በተደረገው የጉዞ እገዳ ምክንያት ማማልከቻዎን አልቀበለም ማለት ይችላል። ቀደም ሲሉ ይወሰዱ የነበሩ እርምጃዎች፣ በአሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት (U.S. Citizenship and Immigration Services (ዩ-ኤስ-ሲ-አይ-ኤስ-USCIS) ይደረጉ የነበሩ የስራ ቅንብሮችና የቀረቡ አቤቱታዎች ጭምር አሁንም በስራ ሊተረጎሙ ይችሉ ይሆናል።
ህጋዊ የሆነ ቪዛ ካሎት
የአሜሪካ መንግስት፤ ከአሜሪካ ውጪ የሚገኙ ግን ከተዘረዘሩት አገሮች ውስጥ ሁነው ግን ህጋዊ ቪዛ ያላቸው ሰዎች፤ በዚህ ወደ አሜሪካን አገር እንዳይገቡ የሚከለክል የጉዞ እገዳ ምክንያት ቪዛቸውን አይቀሙም። ይሁንና መንግስት በሌሎች ምክንያቶች ቪዛ የመቀማት ስልጣን አለው። ያሎትን ህጋዊ ቪዛ ተጠቅመው ወደ አሜሪካን አገር መጓዝ የሚያሳስቦት ከሆነ ምክር ለማግኘት የኢሚግሬሽን ጠበቃ አነጋግሩ።
ቀደም ሲል በስደተኞች የመልሶ መቋቋም ፕሮግራም ውስጥ ለመግባት አመልክተው ከነበር
ቀደም ሲል በዚህ ዓመት፤ ይህ የጉዞ ገደብ ከመውጣቱ በፊት፤ ፕሬዚደንቱ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበል ፕሮግራምን (U.S. Refugee Admissions Program ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ-USRAP) አግደዋል። ይህም ማለት ከእንግዲህ ወዲህ በአሜሪካን አገር ውስጥ ስደተኞችን መልሰው እንዲቋቋሙ አይደረግም ማለት ነው።
ኢራፕ (IRAP)፤ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበል ፕሮግራምን (U.S. Refugee Admissions Program ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ-USRAP) በዚህ ዓይነቱ መንገድ ማገድ ህጋዊ አይደለም ብሎ በመከራከር በአሜሪካን መንግስት ላይ ክስ አቅርቧል። ክሱ አሁንም ገና በሂደት ላይ ይገኛል። በአሁኑ ግዜ አብዛኛዎቹ የመልሶ መቋቋም ማመልከቻዎች እንዳሉ በይቆይ ተይዘው ይገኛሉ። ስለዚሁ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበል ፕሮግራም (U.S. Refugee Admissions Program ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ-USRAP) እና የክሱን ሁኔታ የበለጠ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይጫኑ።
እንደተጻፈው፤ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት የሚከለክለው እገዳ ስደተኞችን የሚመለከት መሆን አይገባውም ነበር። ግን ሰኔ (June) 26 ቀን 2025 ላይ የአሜሪካን መንግስት ስደተኞችንም ይመለከታል ብሏል። ይህም ማለት እገዳ ከተደረገባቸው አገሮች ሁነው ኢራፕ (IRAP) ጉዳያቸውን ይከታተል የነበሩና ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት ይችሉ የነበሩ ስደተኞች፤ በአሁኑ ግዜ መግባት አይችሉም ማለት ነው። ኢራፕ (IRAP) በእነዚህ ስደተኞ ች ላይ የደረሰውን እገዳ አስመልክቶ ፍርድ ቤት እየተከራከረላቸው ነው። ፍርድ ቤቶቹ ግን እስከአሁን ውሳኔያቸውን ገና አልሰጡም።
ልዩ የስደተኛ ቪዛ (ኤስ-አይ-ቪ-SIV) ስለያዙ የአፍጋን ዜጋዎች
የአፍጋን ዜጋ ሆነው በልዩ የተፈቀደ የስደተኛ ቪዛ (Special Immigrant Visa (ኤስ-አይ-ቪ-SIV) የያዙ ከሆነ፤ በያዙት ህጋዊ ቪዛ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት ሊፈቀድሎት ይገባል። ስለዚህ የአፍጋን የኤስ- አይ--ቪ (SIV) ጉዞን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ እዚህ ይመልከቱ።
ምንም እንኳን ሰኔ (June) 2025 የወጣው የጉዞ እገዳ፤ የአፍጋን ኤስ- አይ--ቪ (SIV) ቪዛ የያዙትን አፍጋኖች እንደማይመለከታቸው ቢገልጽም፤ ከዚያ በኋላ የተሻሻለው ግን ይህንን ደንብ ሽሮታል። ከጥር (January) 1 ቀን 2026 ጀምሮ ልዩ የተፈቀደ የአፍጋን የስደተኛ ቪዛ (Special Immigrant Visa (ኤስ-አይ-ቪ-SIV) የሚባል ልዩ ፍቃድ በአጠቃላይ አይኖርም። ከዚህ ቀን በፊት የተፈቀዱ ልዩ የአፍጋን ቪዛ የሌላቸው ሰዎች ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት አይፈቀድላቸውም።
እንዲሁም ህዳር ( November) 2025፤ የአሜሪካን መንግስት፤ የአፍጋን ሰዎች አስገብተዋቸው የነበሩትን የ ኤስ-አይ-ቪ (SIV) ቪዛ ማመልከቻዎችን ሰርዟል፣ በቺፍ ኦፍ ሚሽን (Chief of Mission (ኮም-COM) የተደረጉ ውሳኔዎችም በይቆይ እንዲያዙ አድርጓል። ስለነዚህ ለውጦች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይመልከቱ።
እዚህ ላይ የምንናገረው ከአሜሪካ ጋር ትስስር ስላላቸውና የኤስ-አይ-ቪ (SIV) ቪዛ ስላላቸው የአፍጋን ዜጎች ነው። በአሜሪካ መንግስት ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች የሚሆን ሌላ ልዩ ዓይነት የስደተኛ ቪዛ ለማግኘት ብቁ ከሆኑ፤ ስለዚሁ ጉዳይ እዚህ ላይ ይመልከቱ፡፤
ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል (Follow-to-Join) የሚያስችል የስደተኛ ወይም የጥገኛ ፍቃድ አይ-1-730 (I-730s) ለማግኘት ያመለከቱ ከሆነ
የቤተሰብዎ አባል የስደተኛ ወረቀት ካለው፡ እንደተጻፈው፤ ይሄው የጉዞ እገዳ፤ ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል የሚያስችል ማመልከቻ ሞልተው ወደ አሜሪካን አገር የገቡትን ጨምሮ፤ ስደተኞችን ሊመለከት አይገባውም ነበር። ግን ቀደም ሲል የነበረው የ ዩ-ኤስ-አር-ኤ-ፒ (USRAP) እገዳ ሊመለከታቸው ይችል ይሆናል። ሰኔ (June) 26 ቀን 2025 በወጣው ደንብ መሰረት ግን የአሜሪካን መንግስት በእርግጥ እገዳው ስደተኞችንም ይመለከታቸዋል ብሏል።
ይህም ማለት ኢራፕ (IRAP) ክስ በማቅረቡ፤ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት ይችሉ የነበሩና እገዳ ከተደረገባቸው አገሮች ውስጥ የሆኑ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት ወደ አሜሪካን አገር መግባት አይችሉም። ይህንን እገዳ አስመልክቶ ኢራፕ (IRAP) ጉዳያቸውን ፍርድ ቤት አቅርቧል። ስለዚሁ የስደተኞች እገዳ ተጨማሪ መረጃ ከፈልጉ እዚህ ላይ ይጫኑ።
የቤተሰብዎ አባል የጥገኛነት ወረቀት ካለው፡ እንደጽሁፉ ከሆነ፤ የጉዞ እገዳው እርሶን መመልከት አይገባውም ነበር። ግን የአሜሪካ መንግስት እነኚህን ከቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል የሚያስችል ማመልከቻ የሞሉ ስደተኞችንም ይመለከታል ይላል። በጥቅምት (October) 2025፤ ኢራፕ ( IRAP) ይህንን በስደተኞች ላይ የተደረገውን እገዳ በማስመልከት ፍርድቤት ክስ አቅርቧል። ይህ ክስ ኤኤ መንግስትን በመቃወም (AA v. State) በመባል ይታወቃል። ስለዚህም ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ጭነው ይመልከቱ።
በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘና ተቀባይነትን ያገኘ የአይ-130 (I-130) አቤቱታ (Family-Based Petition (አይ-130-I-130) ተጠቃሚ ከሆኑ
ምንም እንኳን በሰኔ ወር (June) 2025 የወጣው የጉዞ እገዳ አዋጅ፤ በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘና ተቀባይነትን ያገኘ አቤቱታ አቅራቢዎችን አይመለከትም ቢልም፤ ታህሳስ (December) 2025 ላይ የወጣው የጉዞ እገዳ ይህን ደንብ ቀይሮታል። ከጥር (January) 1 ቀን 2026 ጀምሮ በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘ ማመልከቻ ያቀረቡ ሁሉ፡
- ከሙሉ በሙሉ እገዳ ከተደረግባቸው አገሮች ውስጥ ከሆኑ
- ከአሜሪካን አገር ውጪ ከሆኑ እና
- ጥር (January) 1 ቀን 2026 ላይ ህጋዊ ቪዛ ካልያዙ
ጉዳያቸው ልዩ ጉዳይ ነው ተብሎ ብቁ እስካልሆነ ድረስ፤ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት አይፈቀድላቸውም።
በዚህ ክልል ውስጥ የሚገኙ ከሆነ አሁንም አይ -130 ( I-130) የሚባለውን ማመልከቻ ሞልተው ወደ ዩ-ኤስ-ሲ-አይ-ኤስ (USCIS) ማመልከቻቸውን ማስገባት ይችሉ ይሆናል። ይሁንና ይህ የጉዞ እገዳ በስራ ላይ እስካለ ግዜ ድረስ፤ ቪዛ የማግኘቱ ጉዳይ አጠራጣሪ ነው።
ተማሪ ከሆኑ
ይህ የሚመረኮዘው ቪዛዎ ተቀባይነትን አግኝቷል ወይስ አላገኘም በሚለው ነጥብ ላይ ነው።
- ማመልከቻ በማቅረብ ላይ የሚገኙት የተማሪ ቪዛ ለማግኘት ከሆነ፤
የጉዞው እገዳ በርሶ ላይ እንዳይሰራ በሚያደርግ ልዩ መስፈርት ብቁ ሁነው ካልተገኙ በስተቀረ፤ ወደ አሜሪካን አገር
ለመግባት አይፈቀድሎትም።
- ጥር (January) 1 ቀን 2026 ላይ ህጋዊ የሆነ ቪዛ ያሎት ከሆኑ፤ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት ይፈቀድሎታል። ይሁንና ቪዛዎ ከጥር (January) 1 ቀን 2026 በፊት ተቀባይነት ያገኘም ቢሆን፤ በተማሪ ቪዛ ወደ አሜሪካን አገር መግባት አደጋ ሊያስከትል ይችላል። ህጋዊ የሆነ የተማሪ ቪዛ ካሎት፤ ጉዞዎን ከመጀመርዎ በፊት ከኢሚግሬሽን ጠበቃ ጋር መመካከር ያስፈልጎታል።
አገር-ግብኚ ወይም ቱሪስት ከሆኑ
ይህ የሚሞረኮዘው ያሎት ቪዛ ቀደም ሲል ተቀባይነትን አግኝቷል ወይስ አላገኘም በሚለው ላይ ነው።
- ማመልከቻ የሚያስገቡት የቱሪስት ቪዛ ለማግኘት ከሆነ፡ ጉዳዮ በጉዞው እገዳ ላይ በልዩነት ሊታይ የሚችል ነው ካልተባለ በስተቀረ፤ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት አይፈቀድሎትም።
- ጥር ወር (January) 1 ቀን 2026 ላይ ህጋዊ ቪዛ ያሎት ከሆነ፡ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት ሊፈቀድሎት ይችላል። ይሁንና ቪዛዎ ከጥር (January) 1 ቀን 2026 በፊት ተቀባይነት ያገኘም ቢሆን፤ በቱሪስት ቪዛ ወደ አሜሪካን አገር መግባት አደጋ ሊያስከትል ይችላል። ህጋዊ የሆነ የቱሪስት ቪዛ ካሎት፤ ጉዞዎን ከመጀመርዎ በፊት ከኢሚግሬሽን ጠበቃ ጋር መመካከር ያስፈልጎታል።
ሙሉ በሙሉ እገዳ ከተደረገባቸው አገሮች ውስጥ ከሆኑ ግምት ውስጥ የሚገቡ ሌሎች ልዩ ምክንያቶች
የአሜሪካ ህጋዊና ቋሚ ተቀማጮች፡
ህጋዊና ቋሚ ተቀማጭ ወይንም በተጨማሪ ኤል-ፒ-አር (LPR) ተብሎ የሚጠራው ወይም የግሪን ካርድ (Green Card) ያዥ ከሆኑ እና በወቅቱ የሚገኙት ከአሜርካን አገር ውጪ ከሆነ፤ ይህ የጉዞ እገዳ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት አያግዶትም። ይሁንና የጉምሩክና የድንበር ጥበቃ ባለስልጣን ((Customs and Border Protection (ሲ-ቢ-ፒ-CBP)፤ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት እንደሚሞክሩት የአሜሪካን ዜጎች ባልሆኑ ሰዎች ላይ እንደሚያደርገው፤ በህጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካን አገር ይግቡ አይግቡ በማለት ሊወስን ይችላል።
የአፍጋን ተወላጆች ያልሆኑ የአሜሪካ ልዩ የስደተኛ ቪዛ (Special Immigrant Visa (SIV) U.S. Government Employees (Non-Afghan) ያላቸው የአሜሪካ መንግስት ሰራተኞች
የጉዞው እገዳ፤ የአሜሪካ ልዩ የስደተኛ ቪዛ (Special Immigrant Visa (SIV) U.S) ያላቸውን የአሜሪካ መንግስት ሰራተኞችን አይመለከትም፡፡ ይህ ከዛ የአፍጋን ኤስ፟አይ፟ቪ ( SIV) ከሚባለው ለየት ያለ ነው፡፡ ለዚህ አይነቱ ቪዛ ብቁ ከሆኑ በጉዞ እገዳው አይነኩም፡፡
የሁለት አገሮች ዜጋ የሆኑ ሰዎች
የሁለት አገሮች ዜጋ የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ወደ አሜሪካን አገር እንዳይገቡ ከተከለከሉት አገሮች ውስጥ ከሆኑና በዝርዝሩ ውስጥ የሌላ አገር ፓስፖርት ያላቸው፤ ይህንን ፓስፖርት እስከ ተጠቀሙ ድረስ፤ ወደ አሜሪካን አገር የመግባት ፍቃድ ለማግኘት ይችሉ ይሆናል፡፡
ለምሳሌ፤ (የተከለከሉ አገሮች ዝርዝር ውስጥ) እንደ የመን የመሰለ አገርና በተከለከሉ አገሮች ዝርዝር ውስጥ የሌለ እንደ ካናዳ የመሰለ አገር ፓስፖርት ቢኖሮት፤ እንደ ካናዳዊ ዜጋ ማመልከቻ ካስገቡ፤ ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት ይፈቀድሎት ይሆናል፡፡
ስደተኛ ላልሆኑ ሰዎች የሚሰጡ አንዳንድ የቪዛ ምድቦች
ስደተኛ ላልሆኑ ሰዎች የሚሰጥ ቪዛን ለማግኘት ከሚከተሉት A-1፣ A-2፣ C-2፣ C-3፣ G-1፣ G-2፣ G-3፣ G-4፣ ኔቶ (NATO)-1፣ ኔቶ (NATO)‑2፣ ኔቶ (NATO)-3፣ ኔቶ ( NATO)-4፣ ኔቶ (NATO)-5 ወይም ኔቶ (NATO)-6 ውስጥ አንዱን ለማግኘት ካመለከቱ ወደ አሜሪካን አገር የመግባት ሁኔታዎ በጉዞው እገዳ ላይነካ ይችላል፡፡
የስፖርተኞችና የስፖርት ቡድን ሰራተኞች
ስፖርተኛ ከሆኑ ወይም የአንድ የስፖርት ቡድን አባል ከሆኑ፤ ለምሳሌ አሰልጣኝ፤ ለስፖርተኞች አስፈላጊ እገዛ የሚያደርጉ ከሆነ ወይም የስፖርተኞች የቤተሰብ አባል ከሆኑና ለአለም ዋንጫ ውድድር፣ ለኦሎምፒክስ ወይም ለሌላ ከፍተኛ የስፖርት ጉዳይ/ጨዋታ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ከሆነ ወደ አሜሪካን አገር የመግባት ዕድል አሎት፡፡
ጉደፈቻዎች (Adoptions)
ምንም እንኳን በሰኔ ወር (June) 2025 የወጣው የጉዞ እገዳ አዋጅ፤ ከሌላ አገር በጉደፈቻነት የተገኙ ልጆች ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት አይታገዱም ያለ ቢሆንም ታህሳስ (December) 2025 የወጣው አዋጅ ያንን የመጀመርያውን አዋጅ ሽሮታል፡፡ ከሚመጣው ጥር (January) 1 ቀን 2026 ጀምሮ የጉደፈቻነት ቪዛ ለማግኘት የሚያመለክቱ ሁሉ፤
- “ሙሉ በሙሉ ከታገዱ” አገሮች ውስጥ ከሆኑ
- የሚገኙት ከአሜሪካን አገር ውጪ ከሆነ እና
- በጥር ወር (January) 1 ቀን 2026 ላይ ህጋዊ ቪዛ የሌላቸው ሰዎች፤ ጉዳያቸው አንድ በአንድ ወይም በተናጠል እየታየ ልዩ መሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀረ፤ ወደ አሜሪካን አገር ሊገቡ አይችሉም፡፡
በኢራን የሚገኙ አንዳንድ የብሄረሰቦችና የሃይማኖት አናሳዎች
አዋጁ፤ በኢራን ውስጥ በስቃይ ላይ የሚገኙት ብሄረሰቦችና የሃይማኖት አናሳዎች የስደተኛ ቪዛ ለማግኘት ማመልከትና ቪዛውንም ማግኘት እንደሚችሉ ይገልጻል። ይህም ወደ አሜሪካ ህጋዊና ቋሚ ወደ ሆነው የመኖርያ ቪዛ ወደ ማግኘት ያመራቸዋል ማለት ነው።. ኢራፕ (IRAP) እንደሚረዳው ከሆነ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቡድኖችን ነው አዋጁ ከሌላው ልዩ ናቸው የሚላቸው ብሎ ያምናል። እነሱም፡ አህዋዚ አረቦች (Ahwazi Arabs)፣ አዘርባጃን ቱርኮች (Azerbaijani Turks -Azeris)፤ ባሃይ ( Baha'i)፣ ባሉች (Balouch)፣ ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች (Jews)፣ ከርዶች (Kurds)፣ ሳቢያን-ማንዲያኖች (Sabean-Mandaeans)፣ የሱፊ እስላሞች (Sufi Muslims)፣ የሱኒ እስላሞች (Sunni Muslims)፣ ያርሳኖች (Yarsans)፣ ዞሮስትሪያኖች (Zoroastrians)፣ እና ምናልባትም ሌሎች ቡድኖች ጭምር። ባለስልጣናት፤ የየአንዳንዱን ሰው ጉዳይ በተናጠል ወይም አንድ በአንድ በማየት ነው ጉዳያቸው ከሌላው ልዩ ነው ብለው ውሳኔያቸውን የሚሰጡት። ይህ ልዩ የመሆን ሁኔታ እኔን ይመለከታል የሚል እምነት ካሎት፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ያሎትን መረጃና ማመሳከርያ በቪዛው ቃለመጠይቅ ወቅት ይዘው በመጣት ያስረዱ።
ወደ አሜሪካን አገር እንደገና ለመግባት የሚጠይቁ ጥገኞችና ስደተኞች
የጉዞው እገዳ፤ ህጋዊ የሆነ የስደተኞች የጉዞ ዶኩመንት (Refugee Travel Document) ይዘው ወደ አሜሪካን አገር ለመግባት ሊከለክሎት አይገባም።
ሙሉ በሙሉ ከታገዱ አገሮች ውስጥ ለሆኑ ሰዎች የተሰጠ የጉዞ እገዳው አጭር መግለጫ
ጉዳዮች አንድ በአንድ ወይም በተናጠል እንዲታዩና ልዩ መሆናቸው እንዲታወቅ የመጠየቅ መንገዶች አሉ ሲባል ሰምቻለሁ። ይህ እውነት ነውን? እውነት ከሆነ እንዴት ነው ማድረግ ያለብኝ?
አዎን፤ በጉዞው እገዳ ላይ አንድ በአንድ ወይም በተናጠል ሊታዩ የሚችሉ ሁለት ልዩ ነገሮች አሉ፡ አንድ በአንድ ወ
- የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቢ ህግ፤ ይህ ሰው ከአሜሪካ መንግስት የፍርድ ሚኒስቴር (Department of Justice) ጋር በተያያዘ መልኩ ወደ አገር ቢገባ ለአሜሪካ ጥቅም ሊያገለግል ይችላል (ለምሳሌ ፍርድ ቤት ለቀረበ ወንጄል የምስክር ቃል ሊሰጥ ይችላል) ብሎ ከወሰነ፤ ግለሰቡ በልዩ ታይቶ ከጉዞው እገዳ ነጻ በመሆን ወደ አሜሪካን አገር መግባት ይችላል።
- በተጨማሪም፤ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር (Secretary of State) የእርሶ አገር ውስጥ መግባት ለ “ብሄራዊ ጥቅም” እንደሚያገለግል ከተረዳ ጉዳዮ በልዩነት ታይቶ ከጉዞው እገዳ ነጻ ሁነው ወደ አገር መግባት ይችላሉ።
ኢራፕ (IRAP)፤ መንግስት፤ ለአገር ጥቅም ለማገልግል ይህ ሰው ብቁ ነው ብሎ እንዴት እንደሚወስን ዝርዝር መረጃ የለውም። . መንግስት፤ ጉዳዩ ልዩ ነው ተብሎ በልዩነት ለመግባት ከአንድ የአሜሪካ ዜጋ ወይም ድርጅት ጋር ግንኙነት መኖር ወይም የገንዘብ ችግር ውስጥ መሆን፣ የግል ችግር፤ (የ ጭንቀት ስሜት)፣ የትምህርት ችግር፣ ወይም በራስ ጤንነት ላይ ወሳኝ ያልሆነ ጉዳት በማድረስ ላይ መሆን፤ ልዩ ለመባል በቂ አይደለም ሲል ተናግሯል። በተጨማሪም መንግስት ይህ ዓይነቱ በልዩ የመታየት ጉዳይ፤ “አልፎ አልፎ” የሚደረግ እንጂ የሚዘወተር አይደለም ይላል።
ይህ የጉዞ እገዳ ቋሚ ነውን? አዋጅ ሲባል ስንት ግዜ ነው የሚቆየው?
ይህ የጉዞ እገዳ ምን ያህል ግዜ እንደሚቆይ ግልጽ አይደለም፡፡ በዚህ ታህሳስ ( December) 2025 በወጣው የፕሬዚደንቱ አዋጅ መሰረት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር (Secretary of State)፣ አዋጁ ታህሳስ (December)16 ቀን 2025 ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ 180 ቀናት ውስጥ ከጉዞ እገዳው ውስጥ የትኛው ክፍል ነው መቀየር ወይም መሰረዝ የሚያስፈልገው በማለት ሪፖርት ማቅረብ አለበት፡፡ ከዛም በኋላ፤ በየ180 ቀናት፤ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር (Secretary of State) ተመሳሳይ ሪፖርት ማቅረብ አለበት፡፡
ግምገማ በተደረገበት በእያንዳንዱ የግዜ ገደብ፤ የጉዞ እገዳው ሁኔታ እንደገና ሊቀያየር ይችል ይሆናል፡፡ በአሁኑ ባለንበት ወቅት ግን የጉዞው እገዳ ምን ያህል ግዜ እንደሚቆይ ወይም ወደፊት ምን ለውጥ እንደሚደረግበት አናውቅም፡፡ በዚህ የጉዞ እገዳ ላይ ማናቸውም ለውጥ ቢደረግ፤ ይህ ጽሁፍ እንደገና ይታደሳል፡፡
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.