የይዘት ማውጫ
ይህ ጽሁፍ ሚያዝያ (April) 2 ቀን 2026 ታደሰ።
አጭር መግለጫ
ይህ ጽሁፍ፤ አስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (expedited removal) ምን እንደሆነና ማንን እንደሚመለከት የሚያስረዳ ነው። ከጥር ወር (January) 2025 ጀምሮ፤ የአሜሪካን መንግስት፤ የአስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (expedited removal) አጠቃቀምን ለማጠናከር ስላደረገው ጥረት መረጃ የሚሰጥ ነው። በመሆኑም ይህ ጽሁፍ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፤
- ስለ አስቸኳይ የመባረር ሁኔታ(expedited removal) መረጃ ይሰጣል።
- በዚህ ሁኔታ ውስጥ የሚካተቱ እነማን መሆናቸውን
- በሂደቱ ውስጥ ከገባችሁ የሚቀጥለው ነገር ምን እንደሆነና
- አሜሪካን አገር ውስጥ ለመቆየት ከዚህ ሂደት እንዴት ሰው ሊወጣ እንደሚችል ያስረዳል።
አስቸኳይ የመባረር ሁኔታ(expedited removal) ምን ማለት ነው?
ይህ አስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (Expedited removal) የአሜሪካን መንግስት በአገሩ ውስጥ ያሉትን ሰዎች በአስቸኳይ ከአገሩ ለማባረር እንዲችል የሚፈቅድ ነው። ለምሳሌ ይህ አስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (Expedited removal) ወደ አሜሪካን አገር ካለ ፍቃድ የገቡና በአሜሪካ ድንበር ላይ ወይም በአካባቢው ከአሜሪካን ኢሚግሬሽን ባለስልጣኖች ጋር የተገናኙ ሰዎችን በአስቸኳይ የማባረር ፈቃድ የሚሰጥ ከረጅም ግዜ አንስቶ ሲሰራበት የቆየ ነው።
በዚህ አስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (Expedited removal)፤ ዳኛ የማየት መብት የሎትም። ሌላ የመንግስት ባለስልጣን ግን ፍርድ ቤት፣ ዳኛ ፊት ለመቅረብ ዕድል ከማግኘትዎ በፊት፤ ከአገር እንድትባረሩ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል። አንዴ በትእዛዙ ስር ከገቡ በኋላ፤ ዜግ ነት ወደ አሎት አገር በአስቸኳይ ይባረራሉ። መንግስት ዜግነት ወደ ሌሎት ወደ ሌላ አገርም ሊያባርሮት ይችላል።
የትራምፕ አስተዳደር በአስቸኳይ መባረር (expedited removal) መመሪያዎች ላይ ለውጥ ለማድረግ የሞከረው እንዴት ነው?
በጥር (January) ወር 2025 ላይ፤ መንግስት የአስቸኳይ የመባረር (expedited removal) መመርያዎችን ለማጠናከር አዲስ መመሪያዎችን አወጣ። የትራምፕ አስተዳደር፤ ወደ አሜሪካን አገር በቪዛ ያልገቡ እና አሜሪካን አገር ውስጥ መቀመጥ ከጀመሩ ሁለት ዓመታት እንደሞላቸው ለማረጋገጥ የማይችሉ ሰዎች፤ በአስቸኳይ የመባረር (expedited removal) ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ፤ በአስቸኳይም ከአገር ይባረራሉ ሲል አውጇል። የትራምፕ አስተዳደር፤ በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ በአሜሪካን አገር መቀመጥ ከጀመሩ ከሁለት ዓመታት በላይ የሆናቸውም ሰዎች በዚህ የአስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (expedited removal) ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ይላል። ይህም ኦፊሲያላዊ በሆነ መግብያ በር በኩል ወደ አሜሪካን አገር መግባት እንዲፈቀድላቸው የጠየቁትንም ይጨምራል (ለምሳሌ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር በኩል የገቡ)።
ይህንን የአስቸኳይ የመባረር (expedited removal) መመርያ ን ለማጠናከር የተወሰደውን ድርጊት በመቃወም አንዳንድ ሰዎች ወደ በፍርድ ቤት ክስ ወይም አቤቱታ አቅርበዋል። በመሆኑም አንድ የፍርድ ቤት ፌደራላዊ ዳኛ፤ ክሱ ፍርድ ቤት ውስጥ እስካለና ውሳኔ እስካላገኘ ድረስ፤ መንግስት ያወጣቸውን መመሪያዎች በስራ ላይ እንዳይተገብር ውሳኔ በመስጠት ከልክሏል። ስለዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይመልከቱ።
በተጨማሪም መንግስት ጥር (January) 2025 ላይ፤ ምንም እንኳን አንዳንድ ሰዎች ፔሮል (parole) በሚባል በግዜያዊንት አሜሪካን አገር እንዲገቡ የሚፈቅድና የሚያስኖር ወረቀት ያላቸውንም ጭምር በዚህ በአስቸኳይ የመባረር (expedited removal) መመርያ ውስጥ ሊያስገባቸው እንደሚችል ገልጿል። ይህ ወደ አሜሪካን አገር ሲ ቢ ፒ ዋን (CBP One) በሚል ቀጠሮ ወደ አሜሪካን አገር ገብተው በግዜያዊነት እንዲኖሩ የሚፈቅደው ፔሮል (parole) ያላቸው የ ኩባ፣ ሄቲ፣ ኒካራግዋ ወይም የቬኑዜላ ዜጎችንም ይመለከታል።
ይህንንም የአስቸኳይ መባረር (expedited removal) መመርያ ን ለማጠናከር የተወሰደውን ድርጊት በመቃወም፤ አንዳንድ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤት ክስ ወይም አቤቱታ አቅርበዋል። የፌደራልዊ ዳኛም በፔሮል ማለትም በግዜያዊነት ወደ አገር ገብተው እንዲቀመጡ የሚፈቅድ ወረቀት ያላቸው ሰዎች በአስችኳይ መባረር (expedited removal) መመርያ ውስጥ ሊገቡ አይችሉም ብሎ ፈርዷል። ይህ ክስ ገና በመቀጠል ላይ ነው ያለው። ስለዚህ ጉዳይ አዲስ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይመልከቱ።
እነዚህ ለውጦች ምን አስፈላጊነት ነው ያላቸው?
እነዚህ ለውጦች ከመደረጋቸው በፊት፤ አሜሪካን አገር ውስጥ ያሉ ሰዎች፤ በአስቸኳይ የመባረር ሂደት (expedited removal) ውስጥ ይገቡ የነበሩት ከአሜሪካን ድንበር በ100 ማይልስ ርቀት ውስጥ በኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ከተያዙና አሜሪካን አገር ውስጥ ገብተው በ14 ቀናት ውስጥ ከተያዙ ብቻ ነበር።
የትራምፕ አስተዳደር የነበረውን የአስቸኳይ መባረር (expedited removal) መመርያዎችን ለመቀየር በሞከረበት ግዜ፤ የሚያዙት ሰዎች፤ ከድንበሩ ምን ያህል ማይልስ እንደራቁ አስፈላጊነት የለውም አለ። ይህም ማለት፤ በዚህ አዲስ መመርያ መሰረት፤ ከበፊቱ በርከት ያሉ ሰዎች ከአሜሪካን አገር በአስቸኳይ እንዲባረሩ በዚህ አስቸኳይ የመባረር ሂደት (expedited removal) ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ማለት ነው። በተጨማሪም፤ የስደተኛ ጉዳያቸው ፍርድ ቤት በኢሚግሬሽን ዳኛ ፊት የቀረበ ቢሆንም፤ መንግስት ጉዳያቸው በአጭሩ እንዲቋጭ በመሞከር በአስቸኳይ የመባረር ሂደት ( expedited removal) ውስጥ ሊያስገባቸው እንደሚችል ገልጿል። በመሆኑም ጉዳያቸውን ራሳቸው ሙሉ በሙሉ ለመከላከል፤ ዳኛ ፊት ከመቅረባቸው በፊት፤ የመታሰርና ከአገር የመባረር አደጋ ያጋጥማቸዋል ማለት ነው።
ምንም እንኳን እነኚህ መምሪያዎች በአሁኑ ግዜ እንዳይሰራባቸው የቆሙ ቢሆኑም፤ መንግስት ይህንን በአስቸኳይ የመባረር ሂደት ((expedited removal) ለማጠናከር፤ ሌሎች የመመርያ ለውጦችን አድርጎ በሌሎች ቡድኖች ላይም እንዲሰሩ ማድረጉ የማይቀር ይመስላል። በአሜሪካን አገር፤ ማንም ሰው ቋሚና ህጋዊ የሆነ የመኖርያ ወረቀት፤ ግሪን ካርድ (green card) ከሌለው፤ እነኚህ የሚደረጉ ለውጦች በየግዜው እንዴት እንደሚቀያየሩና ወደፊትም ምን ተጽእኖ ሊያሳድሩ እንደሚችሉ ለማወቅ ዜና መከታተል ያስፈልገዋል።
ይህንን የአስቸኳይ መባረርን መመርያ (Expedited Removal) በተመለከተ የሚቀርቡ የተለመዱ ጥያቄዎች
በዚህ በአስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (expedited removal) ውስጥ እንድገባ ከተደረኩ የስደተኛ ወረቀት ወይም በአሜሪካን አገር ውስጥ የሚያስቆዩ ሌሎች ዓይነቶች ፈቃዶችን እንዳገኝ መጠየቅ እችላለሁን?
በዚህ በአስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (expedited removal)፤ በአሜሪካን አገር እንደ ስደተኛ ለመቆየትም ሆነ ሌላ ዓይነት የመኖርያ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት ይፈቀድሎት መሆኑን ለማወቅ የማመልከቻ ሂደቱን መጀመር ብቻ ነው የሚችሉት። በዚህ በአስቸኳይ መባረር ሂደት (expedited removal) ውስጥ ካሉ፤ የአሜሪካ መንግስት ካልፈቀደ በስተቀረ፤ የስደተኛ ወረቀት ለማግኘት ማመልከት አትችሉም።
የስደተኛ ወረቀት ለማግኘት ለማመልከት እንድችል የአሜሪካን መንግስትን እንዴት ነው የምጠይቀው?
ወደ አገሮ ለመመለስ የሚፈሩ ከሆነና ይህንንም ፍራቻዎን ለአሜሪካ ባለስልጣን ከነገሩ ቃለመጠይቅ እንዲደረግሎት ያዛል። በቃለመጠይቁ ወቅት የሚሰጧቸው መልሶች እንግዲህ፤ የአሜሪካን መንግስት፤ የስደተኛ ወረቀት ወይም ሌላ በአገር ውስጥ የሚያስቆዮትን ፈቃድ ለማግኘት ለማመልከት ይፈቅድሎት መሆኑን ለመወሰን ያግዙታል ማለት ነው።
ይሁንና፤ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ወደ አገሮ መመለስ ይፈራሉን ወይም የስደተኛ ወረቀት ማግኘት ይፈልጋሉን ብለው ራሳቸው እንደማይጠይቅዎት ማስታወስ ያስፈልጋል። ይህም ማለት ምናልባትም ምንም አይጠይቅዎትም ማለት ነው። በዚህም ምክንያት፤ ወደ አገሮ መመለስ የሚያስፈራዎት ከሆነ፤ ቶሎ ብለው ፤ በአፋጣኝ ለአሜሪካን ባለስልጣናት ያስረዱ። ከአንድ ባለስልጣን በላይ ለሌሎችም ይንገሩ፤ ከአንዴም ብዙ ግዜ በተደጋጋሚ ይንገሩ።
ሌላ ማወቅ የሚያስፈልጎት፤ ቤተሰቦችዎ ከርስዎ ጋር ከሆኑ ሊለያዩዋችሁ እንደሚችሉ ነው። ስለዚህ ወደ አገርዎ መመለስ የሚያስፈራዎት ከሆነ፤ ይህ እንዴት እንደሚሰራና እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ወደ አገር ለመመለስ ልክ እንደስዎ የሚፈራ መሆኑን ለኢሚግሬሽን ባለስልጣናት፤ ለአንድ ባለስልጣን ብቻም ሳይሆን ለብዙ፤ አንዴም ብቻ ሳይሆን ብዙ ግዜ በተደጋጋሚ ተቀላጥፈው መናገር አለቦት። የዚህ እውነተኛነት ለልጆችም ጭምር ነው።
የቃለመጠይቁ ሂደት እንዴት ነው የሚከናወነው?
ወደ አገሬ መመለስ ያስፈራኛል ብለው ለአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ከተናገሩ፤ ቃለመጠይቅ እንዲደረግሎት ያዛሉ። በሁኔታዎ ላይ በመመርኮዝ፤ ሊታመን የሚችል ፍራቻ ቃለመጠይቅ (credible fear interview) ወይም ምክንያታዊ የሆነ ፍራቻ ቃለመጠይቅ (reasonable fear interview) ይደረግሎታል። እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት አስፈላጊ ነገር የኢሚግሬሽን ባለስልጣኖቹ ይህን ሁሉ ቃለመጠይቅ የሚያደርጉት አገሮ መመለስ ለምን እንደሚፈሩ በትክክል ለመረዳትና በዚህም አሜሪካን አገር እንድትቆዩ ለማመልከት ይፈቀድሎታልን ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ነው። ከአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር በሚያደርጓቸው ቃለመጠይቆች ሁሉ እውነት መናገር በጣም ያስፈልጋል።
ይህ ቃለመጠይቅ ግን የስደተኛ ወረቀት የሚያስገኞ አለመሆኑን አስታውሱ። ቃለመጠይቁን በጥሩ ሁኔታ ካለፉት የስደተኛ ወረቀት ለማግኘት የማመልከት ዕድል ያገኛሉ ማለት ብቻ ነው።
በስቃይ ላይ የሚደረግ ዘመቻ (Convention Against Torture) የተሰኘ ቃለመጠይቅም ይደረግሎት ይሆናል። ይህ ቃለመጠይቅ ከአሁን ቀደም የስቃይ ሰለባ ሆነው የሚያውቁ ከሆነ ወይም ወደ ተወሰነ አገር ብመልስ ከፍተኛ ስቃይ ይድርስብኛል ብለው ይፈሩ እንደሆነ እንዲያስረዱ የሚጠይቅ ነው።
በአስቸኳይ የመባረር ሂደት(expedited removal) ውስጥ እንድገባ ከተደረኩ እታሰራለሁን (እያዛለሁን)?
አዎን። ሊታሰሩ ይችላሉ። እንዳውም ካለመታሰር ይልቅ መታሰር ነው ሊሆን የሚችለው። የአሜሪካ ባለስልጣኖች የማባረሩን ሂደት በማሳካት ላይ እያሉ፤ አብዛኛዎቹ በዚህ የአስቸኳይ መባረር ሂደት (expedited removal) ውስጥ እንዲገቡ የተደረጉ ሰዎች ገና ቃለመጠይቅ በማድረግ ላይ ቢሆኑም በእስር ውስጥ ይገኛሉ። በእስር አሉ ማለት በባለስልጣኖቹ ቁጥጥር ስር መገኘት ማለት ነው።
በዚህ አስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (expedited removal) ጠበቃ ለማድረግ ይፈቀድልኛልን?
አዎን፤ ጠበቃ ለመያዝ ይፈቀድሎታል። ይህ አስቸኳይ የመባረር ሁኔታ በአስቸኳይ ስለሆነ የሚደረገው፤ ተቀላጥፎ ወድያውኑ ጠበቃ ማግኘት አስፈላጊ ነው።
ከተያዙ ወይም ከታሰሩ፤ ጠበቃ ማግኘት መብትዎ ነው፤ ጠበቃውንም ለመፈለግ ስልክ የመደወል መብት አሎት።(ይህም ማለት ባለስልጣኖቹ ጠበቃ እፈልጋለሁ ብለው ፍላጎትዎን ከመግለጽ ወይም ጠበቃ ለመፈለግ ስልክ ከመደውል አያስቆሞትም ማለት ነው)።
ምንም ያልገባዎትን ዶኩመንት አለመፈረም አስፈላጊ ነው። በዚህ የአስቸኳይ መባረር ሁኔታ(expedited removal) ውስጥ የመግባት አደጋ አለ የሚሉ ከሆነ፤ ከህግ አስከባሪዎች ጋር ገና ከመገናኘትዎ በፊት፤ ከጠበቃ ጋር ቢነጋገሩ ለእርሶ አጋዥ ይሆናል።
ከገባሁበት የአስቸኳይ መባረር ሁኔታ እንዴት ልወጣ እችላለሁ? የፍርድ ቤት ዳኛስ ማየት እችላለሁን?
ከእነኚህ የሚታመን ፍርሃትና ምክንያታዊ ፍርሃት ቃለመጠይቆች (credible or reasonable fear interview) ውስጥ በአንዱ ጥሩ ውጤት ካመጡ ጉዳዮ በኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት ውስጥ ይቀርባል። ይህም ማለት ጉዳዮን በኢሚግራሽን ዳኛ ፊት ፍርድ ቤት ለማቅረብ ዕድል ያገኛሉ ማለት ነው። ወደ አገሮ የመመለስ ከፍተኛ ፍርሃት እንዳሎት ለኢሚግሬሽኑ ባለስልጣኖች በደንብ ካልነገሩዋቸው ወይም የታመነ ፍርሃትና ምክንያታዊ ፍርሃት ቃለመጠይቆች (credible ወይም reasonable fear) በመባል በሚታወቁት ቃለመጠይቆች አዎንታዊ ውሳኔ ካላገኙ፤ የኢሚግሬሽን ባለስልጣኖች ገና የዳኛ ፊት ሳያዩ ነው በአስቸኳይ አጣድፈው ከአገር የሚያባርርዎት። ከዚህ የአስቸኳይ መባረር ሁኔታ ( expedited removal) ወጥተው ወደ ኢሚግሬሽን ፍርድ ቤት እንኳን ቢሻገሩ ጉዳዮ እልባት እስኪያገኝ ድረስ አሁንም ገና በእስር ውስጥ ነው የሚሆኑት።
በዚህ በአስቸኳይ የመባረር ሁኔታ(expedited removal) እጅግ የምጨነቅ ከሆነ ምን ማድረግ አለብኝ?
ማንኛውም ቋሚና ህጋዊ የሆነ የመኖርያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ green card) የሌለውና ወደ አሜሪካን አገር ከገባ ሁለት ዓመታት ያልሞላው ሰው፤ የግል ሁኔታውን በተመለከተ የሚቻል ከሆነ ከኢሚግሬሽን ጠበቃ ጋር መገናኘትና ምክር መቀበል ያስፈልገዋል።
የኢሚግሬሽን ጠበቃ፤ ጉዳዮን በተመለከተ የስደተኛ ወረቀት ለማግኘት ማመልከት ይሻላል ወይስ አሜሪካን አገር በፈቃድ የሚያስኖሩ ሌሎች ማቆያዎችን ለማግኘት ማመልከት ይሻላል በማለት ለመወሰን ይረዳዎታል። እኛ፤ የአሜሪካን መንግስት እነኚህን አዳዲስ መመሪያዎችን በእንዴት ዓይነት አኳሃን በተግባር እንደሚተረጉማቸው በትክክል የምናውቀው ነገር የለም።
ስለዚህ በአስቸኳይ የመባረር ሁኔታ (expedited removal) እጅግ የሚጨነቁ ከሆነ፤ ምናልባትም በህግ አስከባሪዎች ከተያዙ፤ ከእርሶ ጋር ሁሌም ሊይዙዋቸው የሚያስፈልጉ ነገሮች አሉ። እነኚህም የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡
-
በአሜሪካን አገር ህጋዊ የሆነ የመኖርያ ወረቀት አሎት፤
- የዚህ ህጋዊ ወረቀት ማረጋገጫ ለምሳሌ የኢሚግሬሽን ወረቀትዎ፤ የዜግነት ወረቀትዎ፤ በግዜያዊነት አሜሪካን አገር እንድትቀመጡ በሚፈቅድ ወረቀት ፔሮል (parole) ላይ ያለው መረጃ ጭምር
-
ገና በስራ ላይ ያለ የፍርድ ቤት ጉዳይ ወይም ማመልከቻ ካሎት፤
- በተለይም የስደተኛ ወረቀት ለማግኘት ያስገቡት የማመልከቻ ቅጂ፤ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ እንዳሎት የሚያሳይ ማረጋገጫ ወይም ማመልከቻ። የሚያሳዝነው ግን ይህን ሁሉ ማረጋገጫም ይዘው፤ መንግስት አሁንም በዚህ በአስቸኳይ የመባረር ሁኔታ ((expedited removal) ሊያስገባዎት ይሞክር ይሆናል።
-
አሜሪካን አገር ውስጥ ከገቡ ሁለት ዓመታት ካለፎት፤
- አሜሪካን አገር ምን ያህል ግዜ እንደተቀመጡ የሚያሳይ ዶኩመንት። ይህም የመጡበት የአየር ትኬት፣ የክፍለሃገር ወይም የስቴት መታወቅያ ወረቀት፣ የቤተመጻህፍት ካርድ፣ ስሞና የቤትዎ አድራሻ ያለበት ፖስታ፣ የትምህርት ቤት መዛግብትዎ፣ የኪራይ ውሎችና በአሜሪካን አገር ከሁለት ዓመት በላይ ማድረጎን የሚያሳዩ ሌሎች ተመሳሳይ ዶኩመንቶች።
ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ጥያቄ ሲቀርብሎ የመመለስ ግዴታ እንደሌለቦት ያስታውሱ። በኢሚግሬሽን ጥያቄ ከቀረበሎት መብቶችዎ ምን እንደሆኑ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ላይ ይመልከቱ።
ተጨማሪ መረጃና ምንጮች
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.