የይዘት ማውጫ
ይህ ጽሁፍ ሚያዝያ (April) 15 ቀን 2026 ታደሰ
አጭር መግለጫ
በአሜሪካን አገር የስደተኛ ወረቀት እያሎት በ አሜሪካ የኢሚግሬሽን ወታደሮች (U.S. immigration officers ) በ አይስ (ICE) ተይዤ ልታሰር እችላለሁ እያሉ የሚጨነቁ ከሆነ ለዚህ እንዴት መዘጋጀት እንደሚችሉ ጥያቄ ሊኖሮት ይችላል። ይህ ጽሁፍ የሚከተሉትን ያስረዳል፤
- ሊሆን ለሚችል እስራት እንዴት መዘጋጅት እንደሚቻል
- ስለ ኢሚግሬሽን እስራት ምን ማወቅ እንዳለቦት
- በእስር እያሉ ሊደረግ ስለሚችል ዳግማይ-ቃለመጠይቅ እንዴት እንደሚዘጋጁ
በሚኖሶታ ስለተፈፀመው ስደተኞችን የማሰር ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።
ሊሆን ለሚችል እስራት እንዴት መዘጋጀት እንደሚቻል
ሊሆን በሚችል እስራት የሚጨነቁ ከሆን፤ ለዚህ ሁኔታ እራሶን ለማዘጋጀት የሚጠቅሙና እርሶ ሊወስዷቸው የሚገቡ አንዳንድ እርምጃዎች ከዚህ ቀጥለው ይቀርባሉ፤
በአሜሪካን አገር ውስጥ ያሎትን ህጋዊ ወረቀቶችንና ከመልሶ መቋቋም ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ዶኩመንቶችዎን አሰባስበው ቅጂ ያድርጉ፡፡ እነኚህንም ቅጂዎች የምታምኑት ጓደኛዎ ወይም የቤተሰቦ አባል እንዲይዙሎት ይስጡ። እነኝህ ዶኩመንቶች የሚከተሉትን ሊያጠቃልሉ ይችላሉ፡
- አይ- 94 (I-94 (የገቡበትንና የወጡበትን ቀን የሚያሳይ ካርድ (Arrival/Departure record)
- የመሳፈርያ ደብዳቤ ወይም የተሳፈሩበት ካርድ
- ስራ ለመስራት የሚሰጥ ፈቃድ ወይም “ወርክ ፐርሚት” ( work permit) በመባል የሚታወቅ ካርድ
- ግሪን ካርድ (green card) ለማግኘት አመልክተው ከሆኑ፤ በሂደት ላይ ያለ ግሪን ካርድና ግሪን ካርድ ለማግኘት ያመለክቱበት ማመልከቻ ቅጂ ( ለምሳሌ የአይ 797ሲ፟ (I-797C ) ያስገቡበት “ደረሰኝ “ )
- ህጋዊ የሆነ ወኪል ካሎት፤ ወኪሉ የፈረመበት ፎርም ጂ 28 (Form G-28) (ይህ የኢሚግሬሽን ጉዳዮን በተመለከተ ወኪል እንዳሎት ለመንግስት የሚያረጋግጥ ነው፡፡
የሚያምኑት ጓደኛዎ ወይም የቤተሰቦ አባል ከዚህ የሚቀጥሉትን መረጃዎችንም ማወቁን አረጋግጡ፤
- ኤ-ናምበር (A-number)
- በዚህ ምንጭ ላይ ኤ-ናምበር (A-number) በመባል የሚታወቀውን ቁጥሮን እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ የሚያስረዱ መመሪያዎች በክፍል 3.3 ላይ ይገኛሉ።
- የተወለዱበት ቀን
- የተወለዱበት ሃገር
- ዜግነት ያሎት ሃገር
ህጋዊ ወኪል ካሎት፤
- ወኪልዎ የስራ ካርድ ካለው ይጠይቁ ወይም የስልክ ቁጥሩን ወረቀት ላይ ጽፈው ሁሌም ከእርሶ ጋር ይያዙ ።
ህጋዊ የስደተኛ ወረቀት እንዳሎት ለኢሚግሬሽኑ መኮንን ይንገሩ፣ የዚህን ወረቀት ማረጋገጫንም አሳዩት ። በተጨማሪም ገና መልስ በመጠባበቅ ላይ ያለ የግሪን ካርድ (green card) ወይም በቤተሰብ ጉዳይ ላይ የተመረኮዘ ማመልከቻ ካሎት ያሳዩ። የኢሚግሬሽን ጠበቃ ካሎት ከሱ ጋር ለመነጋገር እንደሚፈልጉም ግለጹ።
የአስቸኳይ ግዜ እቅድ (emergency notification plan) አዘጋጁ። ቀደም ሲል ከኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር ያለኝን ቀጠሮ ወይም ቃለመጠይቅ ለማክበር ስሄድ ያስሩኝ ይሆናል የሚል ስጋት ካለቦት፤ ለወዳጆችዎ ወይም ለቤተሰቦ አባሎች የት እንዳሉ ለመንገር ረዘም ያለ ግዜ ስለማይኖሮት የአስቸኳይ ግዜ ዕቅድ ያውጡ ። ተዘጋጅቻለሁ አሁን ሬዲናው (ReadyNow!) የሚል አፕ (app) ወደ ስልኮ ያውርዱ። ይህ አፕ በኢሚግሬሽን ጠበቃዎች የተዘጋጀ ነው። ምናልባት በአይስ (ICE) ወታደሮች ተይዘው ከታሰሩ፤ አስቸኳይ ዕቅዶችንና የአደጋ ጥሪ እንድታደርጉ የሚያግዝ ነው፡፡
በኢሚግሬሽን ስለሚደረግ እስራት ማወቅ ያለቦት ነገሮች
በአይስ (ICE) ወታደሮች ተይዘው የታሰሩት ከሌሎች የቤተብዎ አባሎች ጋር ከሆነ፤ ሁላችሁንም ለያይተው ወደ ተለያዩ እስር ቤቶች ሊልክዎት ይችላሉ። ከአንዱ ወደ ሌላው እስርቤት እየተሸጋገሩ፤ ከሚኖሩበት ክፍለሃገር ወደ ራቀ ቦታ ጭምር፤ ወደ አያሌ የተለያዩ ቦታዎች ልትወሰዱ ይቻላሉ።
የያዙት ንብረት እንዲሁም የመታወቅያ ዶኩመንቶችዎ ይወሰዱቦታል። አስፈላጊ የሆኑ የስልክ ቁጥሮችን በቃልዎ ይያዙ። የዶኩመንቶችዎን ቅጂዎች ደግሞ ለሚያምኑት ሰው በአደራ ይላኩ።
ጠበቃ ከሌሎት፤ በነጻ የሚያገለግሉ የጠበቃዎች የስም ዝርዝር እንዲሰጦት እዛው እስር ቤት እያሉ ይጠይቁ። ከጠበቃ ጋር መነጋገር በጣም እንደሚፈልጉ ገልጸው የስልክ መጠቀም ዕድል እንዲሰጦት አጥብቀው ይጠይቁ፡፡
የተያዙት በአይስ (ICE) ከሆነ፤ የቤተሰቦ አባላትና ጓደኞችዎ ይህንን ዌብሳይት ድረ ገጽ በመጠቀም የት እንደተያዙ ሊፈልጎት ይችላሉ። የኤ ቁጥሮን ( A-number)፣ የተወለዱበትን አገር ወይም የእርሶን የግል መረጃ በመጠቀም ሊፈልጎት ይችላሉ። ወደዚህ ዌብሳይት በየቀኑ እየገቡ ማየት አለባቸው ምክንያቱም የተያዙ ሰዎች ከአንድ እስር ቤት ወደ ሌላ ስለሚሽጋገሩ፤ መረጃቸውን ቶሎ ወደ ዌብሳይቱ በማስገባት በኩል መዘግየት ሊኖር ይችላል።
ከአይስ( ICE ) እስር ቤት የህግ አገልግሎት ለማግኘት ወይም በዛው እስር ቤት ውስጥ የሆነ ዓይነት ግፍ ሲፈጸም ሪፖርት ለማድረግ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 9233# ይደውሉ።
በአይስ (ICE) እስርቤት ስለሚደረጉ ዳግማይ ቃለመጠይቆች ምን ማወቅ እንደሚገባዎት
የተያዙት በአይስ ICE) ከሆነ፤ ምንም እንኳን አሁን ግሪን ካርድ (green card) ያሎት ቢሆኑም ወይ ደግሞ የግሪን ካርድ ማመልከቻዎን መልስ በመጠባበቅ ላይ ቢሆኑም፤ ከአሁን ቀደም የስደተኛ ወረቀት ለማግኘት ስላስገቡት ማመልከቻ እንደገና ይጠየቁ ይሆናል፤ ቃለመጠይቅም ይደረግሎት ይሆናል። የእንግሊዘኛ ቋንቋ በደምብ የማያውቁ ከሆነ የሚደረግሎት ቃለመጠይቅ በራስዎ ቋንቋ እንዲደረግሎት መብት አሎት። ጠበቃ ካሎት ለአይስ (ICE) ጠበቃ እንዳሎት ይግለጹ። የጠበቃዎ ስልክ ቁጥር ካሎት፤ ጠብቃዎ በስልክ አማካኝነት መካፈል ይችል ይሆናል። ቃለመጠይቁን ማድረግ የሚቀፎት ከሆነ፤ ፈቃዶን ላለመስጠት ይችላሉ። የሚያሳዝነው ግን በአሁኑ ግዜ ምን በመሆን ላይ እንዳለ ዝርዝር መረጃ ስለሌለ፤ ብዙ ጉዳዮች ግልጽ አይደሉም፤ ሁኔታዎችም ይቀያየራሉ። ቃለመጠይቅ ማድረግ አልፈልግም ካሉ ወደፊት ምን እንደሚያጋጥምዎ ማወቅ ወይም መተንበይ አስቸጋሪ ነው።
በሚደረግሎት ዳግማይ ቃለመጠይቅ፤ ከአገሮ ለምን እንደወጡ ወይም ወደ አገሮ መመለስ ለምን እንደሚፈሩ የመሳሰሉ ጥያቄዎች ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ እነኚህ ጥያቄዎች ና ውጭ አገር እያሉ ከተጠየቋቸውና መልስ ከስጡባቸው ጥያቄዎች ጋር ተመሳሳይ ሊሆኑ ይችላሉ። መልስ ሲሰጡ ልክ እንደ በፊቱ እንድ አደረጓቸው ቃለመጠይቆች በጣም መጠንቀቅና እውነተኛ መሆን ያስፈልጎታል።
የአካል ጉዳት ካለብዎት፣ ማመቻቸትን የመጠየቅ መብት አለዎት። ስለ መብቶችዎ የበለጠ እዚህ ማወቅ ይችላሉ።
እኔ በሚኖሶታ የምገኝ ስደተኛ ነኝ፤ ማወቅ የሚያስፈልገኝ ምን ሌላ ነገር አለ?
ጥር (January) 2026 ላይ አይስ (ICE) በሚኖሶታ ውስጥ ግሪን ካርድ (green card) የሌላቸውን ስደተኞች ማሰር ጀመረ። ለዚህ ምላሽ በመስጠት አንድ የሚኖሶታ ፍርድ ቤት፤ አይስ (ICE፤ ግሪን ካርድ ((green card) የላቸውም ብሎ ስደተኞችን ማሰር አይችልም የሚሉ ሁለት ትእዛዞችን አስተላለፈ። ከዛ በኋላ የአሜሪካ መንግስት፤ ግሪን ካርድ ስለሌላቸው በመላው ሃገር የሚገኙ ስደተኞችን ለማሰር እሞክራለሁ ሲል አወጀ። በማሳሹሴትስ የሚገኝ ሌላ ፍርድቤት፤ የአሜሪካ መንግስት ይህንን የሰደተኞችን ማሰር የሚመለከት መመርያውን በየትም ቦታ በስራ ሊተረጉም አይችልም ሲል ትእዛዝ አወጣ።
በአሁኑ ወቅት በሚኖሶታ የነበረው ጉዳይ ተሰርዟል። ይህም ማለት ከእንግዲህ ወዲህ የስደተኞችን ማስር ጉዳይ የሚመለከት ምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ በሚኖሶታ የለም ማለት ነው። በደንብ መታወቅ ያለበት ነገር በማሳሹሴትስ የተደረገው የፍርድ ቤት ትእዛዝ በመላው ሃገር፤ በሚኖሶታም ጭምር፤ ግሪን ካርዳቸውን ያላገኙ ቢሆኑም መመርያው እንዲቆም ማድረጉ ነው። ስለሆነም በሚኖሶታ የሚገኙ ስደተኞች አሁንም ከመታሰር የተጠበቁ ናቸው።
እዚህ ጽሁፍ ላይ የተገለጹትንም ጨምሮ፤ መብቶችዎን በደንብ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። እዚህ አገር መጀመርያ ሲገቡ በመልሶ ማቋቋምያ ድርጅቶች ታግዘው ከነበር፤ አሁንም የአካባቢዎን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከእነሱ ጋር መገናኘት አጋዥ ሊሆን ይችላል።
የአገር ውስጥ ደህንነት ጽህፈት ቤት (Department of Homeland Security ዲ ኤች ኤስ DHS) በሚኖሶታ ለሚገኙ አያሌ ስደተኞች የፓሪስ ቃለመጠይቅ (PARRIS Interview) እና እንደ ስደተኛ ተቀባይነት ካገኙ በኋላ የሚደረግ የማጣርያ ቃለመጠይቅ (Post-Admission Refugee Reverification) እና የ I-485 ቃለመጠይቅ እንዲያደርጉ ወደ ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) ህንጻ እንዲመጡ ትእዛዝ እየሰጠ ነው። ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) ግሪን ካርድ (ህጋዊና ቋሚ የሆነ የመኖርያ ፈቃድ) ለማግኘት ያመለከቱ ስደተኞችን ቃለመጠየቅ እንዲያደርጉ የመጥራት ስልጣን አለው። በእነዚህ ቃለመጠይቆች ካልተገኙ፤ ግሪን ካርድ ( green card) ለማግኘት ያስገቡት ማመልከቻ ተቀባይነት ላያገኝ ይችላል፤ መንግስትም የስደተኛ መብቶን ለመሰረዝ ዕቅድ እንዳለው የሚያስረዳ ጽሑፍ ሊደርሶት ይችላል። በዚህ ቃለመጠይቅ ላይ ስደተኛ ለመሆን ያበቃዎትን ምክንያቶች በዝርዝር እንዲያስረዱና ስለ ግሪን ካርድ
(green card) ማመልከቻዎ እንዲያስረዱ ይጠየቃሉ የሚል እምነት አለን።
ከእነዚህ ማስታወሻዎች አንዱ እንኳን ቢደርሶ፤ ተቀላጥፈው የጠበቃ ምክር ማግኘትና ወደ ቃለመጠይቁም ጠበቃዎን ይዞ መግባት እጅግ ጠቃሚ ነው። ጠበቃ ማግኘት ግን ግዜ ስለሚፈጅ፤ ቀደም ሲል እርዳታ ያደረጉሎትን የመልሶ መቋቋም ድርጅቶችን በአፋጣኝ ማግኘት ጠቃሚ ነው ብለን ምክራችንን እንለግሳለን።
ተጨማሪ መረጃና ምንጮች
- መብቶን ይወቁ (Know Your Rights)፤ በኢሚግሬሽን ከተያዙ ወይንም ከታሰሩ ምን ማደረግ አለቦት (What to Do if You Are Arrested or Detained by Immigration (National Immigration Law Center)
- መብቶን ይወቁ (Know Your Rights)፤ እርስዎ ወይም ወዳጆ ከታሰረ ምን ማድረግ አለቦት (What to Do If You or a Loved One Is Detained National Immigrant Justice Center)
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.