የይዘት ማውጫ
ይህ ጽሑፍ ለመጨረሻ ጊዜ የተዘመነው ሐምሌ 8፣ 2026 ነው።
አጭር መግለጫ
የተጠበቀ ግዜያዊ የመኖርያ ሁኔታ (Temporary Protected Status (ቲ ፒ ኤስ TPS)፤ የአንዳንድ አገሮች ሰዎች ወደ አገራቸው የመመለስ ሁኔታ አደጋ የሚያስከትልባቸው በመሆኑ፤ አሜሪካን አገር ውስጥ መቆየት እንዲችሉ ለመርዳት የአሜሪካን መንግስት ያወጣው ፕሮግራም ነው። ግዜው ያልተቃጠለ የቲ ፒ ኤስ (TPS) ወረቀት ካሎት ለተወሰነ ግዜ በአሜሪካን አገር የመኖርና የመስራት መብት አሎት።
የአሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቲ ፒ ኤስ (TPS)ን በተመለከተ ሚያዝያ (April) 29 ቀን 2026፤ ሁለት ጉዳዮችን- አንዱ የሶርያ ማሊን አንጻር ዳህሊያ ዶ (Mullin v. Dahlia) ፣ ሁለተኛው ደግሞ የሄቲ ትራምፕ አንጻር ሚዮት (Trump v. Miot) የተባሉ ጉዳዮችን ሰምቷል። ሰኔ (June) 25 ቀን 2026 ከፍተኛው ፍርድ ቤት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የሰጠውን ውሳኔ ይፋ አደረገ፤
- የትራምፕ አስተዳደር፤ ለሶርያና ለሄቲ ይሰጥ የነበረው ቲ ፒ ኤስ ( TPS) እንዲቋረጥ ፈቀደ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት፤ ለሶርያና ለሄቲ ተፈቅዶ የነበረው ቲ ፒ ኤስ (TPS) መንግስት እንዲያቋርጠው ሲወስን፤ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔውን ከወሰደበት ዕለት ጀምሮ የሚታሰብ ከ 32 ቀናት (ሓምሌ 27 ቀን) በኋላ ቲ ፒ ኤስ (TPS) ይቋረጣል ማለት ነው። ይህ የሚሆነው ግን በመካከል የዲስትሪክቱ ፍርድቤቶች ሌላ ልዩ የሆነ ውሳኔ እስካልወሰዱ ድረስ ነው።
- የማእከላይ መንግስት ወይም የፌደራል መንግስት ፍርድ ቤቶች፤ የቲ ፒ ኤስ (TPS) ሕግን ምርኩዝ በማድረግ ይህንን ውሳኔ እንደገና ሊያጤኑ ወይም ይህ የመንግስት ውሳኔ ሕጋዊ አይደለም ብለው ሊከራከሩ አይፈቀድላቸውም።
- የፌደራሉ ፍርድ ቤቶች፤ ይህንን የመንግስት ውሳኔን መቃወምና ሕገ መንግስቱን የሚጥስ ነው ብለው መከራከር የሚፈቀድላቸው ሕገ መንግስቱን እንደሚጥስ ጭብጥ ሲያቀርቡ ነው። የዚህን ጭብጥ ማግኘት ግን አስቸጋሪ ነው።
ይህ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ፤ የትራምፕ አስተዳደር ለሌሎች አብዛኛዎቹ አገሮች የተሰጠው ቲ ፒ ኤስ (TPS) ም እንዲቋረጥ ለማድረግ የሚፈቅድለት ነው። ይህ ቲ ፒ ኤስ (TPS)ን ለማስቆም የተደረገ ውሳኔ ሕገ መንግስታዊ አይደለም በሚል በዝቅተኞቹ ፍርድ ቤቶች ክሶች መቅረባቸው ሊቀጥል ይችላል። ይሁንና ይህን በሕጋዊ መንገድ ማረጋገጥ ከባድ ነው።
ለአንዳንድ አገሮች የተሰጠው ቲ ፒ ኤስ (TPS) አሁንም ገና በስራ ላይ ነው።
በዚህ ውሳኔ መሰረት የእያንዳንዱ ዝርዝር አገር ቲ ፒ ኤስ (TPS) ምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እዚህ ላይ ይመልከቱ።
የተጠበቀ ግዜያዊ የመኖርያ ሁኔታ (Temporary Protected Status) ምን ማለት ነው?
የተጠበቀ ግዜያዊ የመኖርያ ሁኔታ (Temporary Protected Status (ቲ ፒ ኤስ TPS) ግዜያዊ የሆነ የኢሚግሬሽን ዓይነት ነው። የአሜሪካን መንግስት፤ ከተወሰኑ አገሮች መጥተው በአገራቸው ውስጥ በሚካሄድ ጦርነት ወይም በአገራቸው ውስጥ ባጋጠመ የተፈጥሮ አደጋ ወይም በሌላ ምክንያት ወደ አገራቸው መመለስ ጉዳት ለሚያስከትልባቸው የአንዳንድ አገሮች ዜጎች ይህንን የተጠበቀ ግዜያዊ የመኖርያ ሁኔታ (Temporary Protected Status (ቲ ፒ ኤስ TPS) በመባል የሚታወቅ ፈቃድ ይሰጣል።
በእነዚህ ባላፉት ቅርብ ዓመታት ውስጥ ቲ ፒ ኤስ (TPS) ያገኙ አገሮች፤ አፍጋኒስታን (Afghanistan)፣ በርማ (Burma) ማይናማር (Myanmar)፣ ካሜሮን (Cameroon)፣ ኤልሳልቫዶር (El Salvador)፣ ኢትዮጵያ (Ethiopia)፣ ሄቲ (Haiti)፣ ሆንዱራስ (Honduras)፣ ሊባኖስ (Lebanon)፣ ኔፓል (Nepal)፣ ኒካራጉዋ (Nicaragua)፣ ሶማሌ (Somalia)፣ ደቡብ ሱዳን (South Sudan)፣ ሱዳን (Sudan)፣ ሶርያ (Syria)፣ ዩክሬን (Ukraine)፣ ቬኑዙዌላ (Venezuela) እና የመን (Yemen) ናቸው።
ያልተቃጠለ ቲ ፒ ኤስ (TPS) ካሎት የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፤
- በሕጋዊ መንገድ አሜሪካን አገር ውስጥ መቀመጥ
- የስራ ወረቀት ለማግኘት ማመልከት
- ያልተቃጠለ ቲ ፒ ኤስ (TPS) ካሎት ከመያዝና ከመታሰር መዳን
ግን ቲ ፒ ኤስ (TPS) የሚከተሉትን አያደርግሎትም፣
- ዘላቂ የሆነ የኢሚግሬሽን ፈቃድ አያሰጥዎትም።
- በራሱ ብቻ ግሪን ካርድ ( green card) እንድታገኙ አያደርግም።
በየአንዳንዱ አገር በኩል ብናየው የወቅቱ የቲ ፒ ኤስ (TPS) ሁኔታ ምን ይመስላል?
የትራምፕ አስተዳደር የአያሌ አገሮች ቲ ፒ ኤስ (TPS) እንዲቆም አድርጓል። በአንዳንድ አገሮች ግን ቲ ፒ ኤስ (TPS) ገና በስራ ላይ ይገኛል። ይሁንና የትራምፕ መንግስት የተሰጣቸው ቲ ፒ ኤስ (TPS) ገና በመስራት ላይ የሚገኙ አገሮችን ቲ ፒ ኤስ አያሳድስም የሚል ግምት አለ። ይህ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ በተጨማሪ ጉዳያቸው ፍርድ ቤት በመቅረቡ ምክንያት በግዜያዊነት እንዲቆሙ በተደረጉ ቲ ፒ ኤሶች (TPS) ላይም ጫና ያደርጋል።
የእያንዳንዱ አገር ቲ ፒ ኤስ (TPS) በምን ሁኔታ ላይ እንዲሚገኝ ከወደ ታች ቀርቧል፤
አፍጋኒስታን (Afghanistan)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡ ተቋርጧል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል
በርማ Burma (ሚያንማር Myanmar)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡ መቋረጥ ለግዜው ቆሟል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ካሜሩን (Cameroon)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡ ቲ ፒ ኤስ (TPS) ተቋርጧል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ኤል ሳልቫዶር (El Salvador)
ቲ ፕ ኤስ (TPS) እስከ መስከረም (September) 9 ቀን 2026 ይሰራል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ኢትዮጵያ (Ethiopia)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡ የቲ ፒ ኤስ (TPS) መቋረጥ ለግዜው ቆሟል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ሄቲ (Haiti)
ቲ ፒ ኤስ (TPS) ሓምሌ ( July) 27 ቀን 2026 ይቋረጥ ይሆናል
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ሆንዱራስ (Honduras)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡ ተቋርጧል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ሊባኖስ (Lebanon)
ቲ ፒ ኤስ (TPS) እስከ ህዳር (November) 27 ቀን 2026 ይሰራል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ here ይመልከቱ።
ኔፓል (Nepal)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡ ተቋርጧል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ኒካራግዋ (Nicaragua)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡ ተቋርጧል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ሶማሌ (Somalia)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡ የቲ ፒ ኤስ (TPS) መቋረጥ ለግዜው ቆሟል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ደቡብ ሱዳን (South Sudan)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡: የቲ ፒ ኤስ (TPS) መቋረጥ ለግዜው ቆሟል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ሱዳን (Sudan)
ቲ ፒ ኤስ (TPS) እስከ ጥቅምት (October)19 ቀን 2026 ይሰራል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ሶርያ (Syria)
ቲ ፒ ኤስ (TPS) ህዳር (July) 27 ቀን 2026 ይቋረጥ ይሆናል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ here ይመልከቱ።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ዩክሬን (Ukraine)
ቲ ፒ ኤስ (TPS) እስከ ጥቅምት (October)19 ቀን 2026 ይሰራል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ቬኑዝዌላ (Venezuela (2021)
እየተከናወነ ያለ ክስ፡ ተቋረጠ
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ቬኑዝዌላ (Venezuela) (2023)
በመካሄድ ላይ ያለ ክስ፤ የተደረገው የቲ ፒ ኤስ (TPS) መቋረጥ ለግዜው ቆሟል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
የመን (Yemen)
በመካሄድ ላይ ያለ ክስ፤ የተደረገው የቲ ፒ ኤስ (TPS) መቋረጥ ለግዜው ቆሟል።
ስለክሱ አዲስ መረጃ እዚህ ይገኛል።
የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የምንጭ ገጽ እዚህ ይገኛል።
ይሄ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በአሜሪካን አገር ስራ እንድሰራ በተፈቀደልኝ ሁኔታ ላይ ጫና ያደርጋልን?
አዎን። ለአገሮ የተሰጠው ቲ ፒ ኤስ (TPS) እንዲቋረጥ ከተደረገ አሜሪካን አገር ውስጥ እንዲሰሩ አይፈቀድሎትም። ይህ እንዳይሆን የሚያደርግ ግን ምናልባት አሜሪካን አገር እንድትሰሩ የሚፈቅድ ሌላ ልዩ ሕጋዊ ወረቀት ካሎት ብቻ ነው።
ከሐምሌ 1፣ 2026 ጀምሮ፣ USCIS ለሶሪያ፣ ለሄይቲ፣ በርማ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና የመን የሥራ ፈቃድ ሐምሌ 10 ላይ አብቅቷል። USCIS እነዚህን ቀናት ለእነዚያ አገሮች TPS እስከ ሐምሌ 10፣ 2026 ድረስ እንደሚጠናቀቅ በመጠባበቅ አሳትሟል። ግልጽ ለመሆን፣ እነዚህ ቀናት የመጨረሻ አይደሉም እና በፍርድ ቤት ውሳኔዎች ላይ በመመስረት ሊለወጡ ይችላሉ።
የሥራ ፈቃድ የTPS ሁኔታዎ ከማብቃቱ በፊት አያበቃም። ትክክለኛ የTPS ሁኔታ ካለዎት፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የመሥራት ፈቃድ አለዎት።
መረጃው በፍጥነት ስለሚለዋወጥ፣ እዚህ የተዘረዘረውን አገርዎን የUSCIS ምንጭ ገጽ በየጊዜው መመልከት አለብዎት።
ተሰጥቶኝ የነበረ የቲ ፒ ኤስ (TPS) ወረቀቴን የማጣ ከሆነ እንዴት ነው ለዚህ መዘጋጀት የምችለው?
ለአገሮ ይሰጥ የነበረው ቲ ፒ ኤስ (TPS) እንዲያበቃ ከተደረገ፤ ሌላ ሕጋዊ የስራ ፈቃድ ከሌሎት፤ የመታሰር እንዲሁም ከአገር የመባረር አደጋ ሊያጋጥሞት ይችላል። አሜሪካን አገር እንዲቆዩ የሚያደርግ ሌላ ምርጫ እንዳሎት ለማወቅ የስራ ፈቃድ ያለው ብቁ የሆነ ጠበቃን ማነጋገር ያስፈልጎታል። በነጻ ማለትም ገንዘብ ሳይከፍሉ ወይም በጣም አነስተኛ በሆነ ክፍያ የሚሰሩ የጠበቃዎች ዝርዝር እዚህ ይመልከቱ፤ እንዲሁም በግል የሚሰሩ ጠበቃዎችን ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።
ማስታወሻ፤ ኢራፕ (IRAP) ስማቸው በሊስቱ ውስጥ የተዘረዘሩት ጠበቃዎች ብቁ ስለመሆናቸው የሚሰጠው ዋስትና የለም።
ከአሜሪካን የኢሚግሬሽንና የጉምሩክ ማጠናከርያ ጽህፈት ቤት (U.S. Immigration and Customs Enforcement (አይስ ICE) ባለስልጣናት ጋር ስትገናኙ፤ መብቶች እንዳሎትም ማስታወስ አስፈላጊ ነው። መብቶቹም እንደሚከተሉት ናቸው፤
- ዝም የማለትና ለተጠየቁት ጥያቄዎች መልስ ያለመስጠት
- የዳኛ ፊርማ ያለበት ወረቀት ከሌላቸው በስተቀረ አይስ (ICE) እርሶንም ሆነ ቤትዎን እንዳይፈትሽ የመከልከል መብት
- ከታሰሩ ከጠበቃ ጋር የመነጋገር መብት
የኮንግሬስ አባል ወኪሎን እርዳታ ስለመጠየቅ
በአይስ (ICE) ከታሰሩ፤ በኮንግሬስ ያለው ወኪሎ (Member of Congress) ሊረዳዎት ይችል ይሆናል። የኮንግሬስ አባሎች መስርያ ቤቶች፤ ሲያዙ ያሉበት ቦታ የት እንደሆነ፣ የሚያስፈልጎት መድሃኒት ካለ እንዲደርሶት ወይም ወደ ሌላ ቦታ የተዛወሩበትና ሲያዙ ስለነበረው ሁኔታ አይስ (ICE) ን መጠየቅ ይችላሉ።
በአይስ (ICE) ተይዘው እንዳይታሰሩ ስጋት ያለቦት ከሆነ፤ በኮንግሬስ ያለው አባል ወኪልዎ፤ እርስዎ በእስር ላይ እያሉ ስለጉዳዮ እንዲጠይቅና እርዳታ እንዲያደርግሎ ይህንን ፎርም (አይስ ፎርም 60-001- ICE Form 60-001) ሞልተው ማስገባትን ግምት ውስጥ አስገቡ። እርሶን ለመርዳት ይሄው የኮንግሬስ አባል ሙሉ በሙሉ የተሞላና በርስዎ የተፈረመ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፈ ፎርም ያስፈልገዋል። አይስ (ICE) የተተረጎመ ፎርም አይቀበልም።
በአይስ (ICE) ተይዘው ከታሰሩ፤ ይህንን የተሞላ ፎርም ወደ ሚያምኑት የቤተሰቦ አባል፣ ጓደኛዎ ወይም ጠበቃ ዘንድ በመላክ ወደ ኮንግሬስ አባል ወኪሎ እንዲሰጥ ያድርጉ።
ይህ ፎርም ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ90 ቀናት ብቻ ሕጋዊ ሁኖ የሚቀጥል ነው።
ተጨማሪ ምንጮች
ምናልባትም ከኢሚግሬሽን ባለሰልጣኖች ጋር ከተገናኙ በበለጠ ተዘጋጅተው እንዲቆዩ የሚያደረግዎትን በአያሌ ቋንቋዎች የተዘጋጁ እነኚህን የሚከተሉትን ጽሑፎች ማንበብም ይፈልጉ ይሆናል፤
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights): የአይስ (ICE) አባሎች ጋር ስትገናኙ (If you encounter ICE) | National Immigrant Justice Center
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights)፤ በኢሚግሬሽን ስትያዙ ወይም ስትታሰሩ ምን ማደረግ እንዳለቦት |What to do if You Are Arrested or Detained by Immigration| National Immigration Law Center
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights)፤ ሕጋዊ ምንጭ የሚገኝበት አፕ |Legal Resource app | National Korean American Service and Education Consortium
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights: ከሕግ አስከባሪዎች ጋር ስትገናኙ ምን ማድረግ እንዳለቦት | What to Do in Interactions with Law Enforcement | CLEAR
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights) የስደተኞች መብቶች (Immigrants’ Rights | ACLU
በመጨረሻም፤ ናሽናል ቲ ፒ ኤስ ትብብር/አላያንስ (National TPS Alliance)፤ ቲ ፒ ኤስ (TPS) ላላቸው ሰዎች ተጨማሪ ምንጮችንና እገዛዎችን ሊያደርግ ይችል ይሆናል።
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.