የይዘት ማውጫ
ይህ ጽሑፍ መጨረሻ የታደሰው ሓምሌ (July) 27 ቀን 2026 ነው።
አጭር መግለጫ
ይህ ጽሑፍ በወቅታዊው የአሜሪካ የመልሶ ማቋቋም ፖሊሲ እና ፕሬዚደንት ትራምፕ ጥር ( January) 20 ቀን 2025 በፈረሙት “የማስፈጸምያ ትእዛዝ“ (executive order) ጭምር ላይ ጥያቄ ላላቸው ሰዎች መልስ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው። ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ “ የአሜሪካን ስደተኞችን የመቀበያ ፕሮግራምን እንደገና ማሻሻል” በመባልም ይታወቃል። ይህም ቀደም ሲል የነበረው የአሜሪካ ስደተኞች የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም እንዲቆም አድርጓል።
ይህ ጽሑፍ፤ የማስፈጽምያ ትእዛዙ ምን እንደሚልና በወቅቱ የስደተኛ ወረቀት ለማግኘት ማመልከቻ ባስገቡ ሰዎች ላይ ለውጡ የሚያስከትለው ተጽእኖ ምን እንደሚመስል የሚያስረዳ ነው። በተጨማሪም፤ መንግስት የስደተኞች የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም እንዲቆም ማድረጉን በመቃወም ኢራፕ (IRAP) ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ በትእዛዙ ላይ ምን ተጽእኖ እንደሚያደርግ ያስረዳል።
ቀደም ሲል የነበረው የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም (ዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) ምን ሆነ ?
የአሜሪካ ስደተኞችን የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም (U.S. refugee resettlement program)፤ የአሜሪካ ስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም (United States Refugee Admissions Program) ወይም ዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) በመባል ይጠራል።
ጥር (January) 20 ቀን 2025፤ ፕሬዚደንት ትራምፕ፤ የአሜሪካንን የስደተኞች የመቀበያ ፕሮግራምን ማሻሻል “Realigning the United States Refugee Admissions Program.” የሚባል የማስፈጸምያ ትእዛዝ አወጡ። “የማስፈጸምያ ትእዛዝ” ማለት መንግስት አንድ የተወሰነ ስራ እንዲፈጸም ለማድረግ ከፕሬዚደንት የሚሰጥ ኦፊሲያላዊ ዶኩመንት ወይም ትእዛዝ ነው።
ይህ ትእዛዝ፤ የአሜሪካን መንግስት፤ ስደተኞች ወደ አሜሪካን አገር ላልታወቀ ግዜ እንዳይገቡ ይከለክላል። በተጨማሪም ይሄው ትእዛዝ በስደተኞች ማመልከቻዎች ላይ ውሳኔ እንዳይሰጥ ያግዳል።
ፕሬዚደንቱ ይህንን ትእዛዝ እንዳስተላለፉ፤ ብዙም ሳይቆዩ የመንግስት ተቋሞች የስደተኞችን አዲስ ማመልከቻዎችን መቀበል አቆሙ፤ በሂደት ላይ የነበሩ ጉዳዮችንም በሙሉ ዘጉ። ፍቃድ አግኝተው የነበሩና ተመድበው የነበሩ የስደተኞች በረራዎችንና የጉዞ ዝግጅቶችንም ሰረዙ።
የካቲት (February) 10 ቀን 2025፤ ኢራፕ (IRAP)፤ ፓሲቶ አንጻር ትራምፕ ( Pacito v. Trump) የሚባል ክስ በመንግስት ላይ መሰረተ። ይህ ክስ፤ መንግስት የማስፈጸምያ ትእዛዝ በመስጠት፤ የአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም (U.S. Refugee Admissions Program (USRAP) እንዲቆምና ለፕሮግራሙ ይሰጥ የነበረው የገንዘብ እርዳታ እንዲቋረጥ በማድረጉ ህግ ጥሷል የሚል ነው። ክሱ፤ ፕሬዚደንት ትራምፕ የሰጡት የማስፈጽማያ ትእዛዝና መንግስት ዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP)ን ለማስቆም የወሰደው እርምጃ ከህግ ውጪ መሆኑን የአሜሪካ የፍርድ ቤት ዳኛ ውሳኔውን እንዲሰጥ ጥያቄ የሚያቀርብ ነው። ይህ ጉዳይ አሁንም ገና በሂደት ላይ ያለ ነው። ይሁንና በአሁኑ ግዜ ፍርድ ቤት፤ ፕሬዚደንት ትራምፕ የስደተኞች መልሶ ማቋቋም ፕሮግራሙ እንዲቆም እንዲያደርጉ ፈቅዶላቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ስለዚሁ ጉዳይ የወሰነውንና ያሳለፈውን ውሳኔ ዝርዝር ለማወቅ የሚያስችሎትን መገናኛ መስመር እዚህ ያገኛሉ።
ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ በጉዳዬ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ምንድነው?
በአሁኑ ወቅት፤ መንግስት አዲስ ማመልከቻዎችን በመመልከት ላይ ያለው በደቡብ አፍሪቃ በጀመረው አዲስ ፕሮግራም አማካኝነት ብቻ ነው። መንግስት ለሌሎች አመልካቾች፤ የስደተኞች የማመልከቻ ሂደቶች በሙሉ እንዲቆሙ አድርጓል። ይህም የሚከተሉትን ይጨምራል፡
- አዲስ የተመሩ አመልካቾችን መቀበል
- አዲስ ጉዳዮችን መፍጣር
- የቃለመጠይቅ ቀነ ቀጠሮ መስጠት
- ጉዳዮችን መቀበል ወይም አለመቀበል
- የህክምና ምርመራ ቀጠሮ መስጠት እና
- አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን ላጠናቀቁ ሁሉ የበረራ ግዜ ማድረግ
በዚህ በተደረገው እገዳ ልዩ ሁኔታ አለን? እነኚህ አዲስ የወጡት መመርያዎች የማይሰሩባቸው ሁኔታዎችስ አሉን?
የማስፈጽምያ ትእዛዙ፤ ልዩ ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ ይላል። ይሁንና የማስፈጽምያ ትእዛዙ፤ እንደ ልዩ ሁኔታ ሊቆጥራቸው የሚችል ምን ዓይነት ጉዳዮች እንደሆኑ አይገልጽም። ትእዛዙ፤ መንግስት ልዩ ሁኔታ ሊፈጥር የሚችለው የሆነ ነገር ለ”ብሄራዊ ጥቅም” ያገለግላል ብሎ ሲያምን ወይም ስደተኞው በብሄራዊ ደህንነት ወይም በአሜሪካን ላይ ምንም ጉዳት አያስከትልም ብሎ ሲያምን ነው” ይላል። ትእዛዙ ይህ ምን ማለት መሆኑን በግልጽ አያስረዳም፣ በተጨማሪ አንድ ነገር ልዩ ነው፣ በልዩ ሁኔታ መታየት አለበት ብሎ መወሰንና የልዩ ሁኔታውን ሂደት መጀመር የሚችለው መንግስት ብቻ ነው ይላል።
አዲስ የዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) ጉዳይ መክፈት እችላለሁን?
እኛ እስከምናውቀው ድረስ፤ በአሁኑ ግዜ በአዲሱ የደቡብ አፍሪቃውያን የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም፤ በደቡብ አፍሪቃ አፍርካነርስ (Afrikaners) በመባል የሚታወቁትና ” የማይወደዱ አናሳዎች” (disfavored minorities) ብቻ ናቸው አዲስ የዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) ጉዳይ መክፈት የሚችሉት።
ይህ እንዲቆም የተደረገው ሁኔታ ‘እንኳን በደህና መጣችሁ ቡድን ፕሮግራምን (Welcome Corps program) ላይ ተጽእኖ ያደርጋልን?
አዎን። የአሜሪካ መንግስት፤ ለፕሬዚደንቱ የማስፈጸምያ ትእዛዝ በሰጠው ምላሽ፤ የእንኳን በደህና መጣችሁ ፕሮግራም ( Welcome Corps program) በሙሉ እንዲቆም አድርጓል።ማንኛቸውንም የመቀበያ ማመልከቻዎችን መቀበሉንና ማመልከቻዎችን ማየቱን አቁሟል።
ይህ የስደተኞች ፕሮግራም መቼ ነው እንደገና የሚከፈተው?
የአሜሪካ የስደተኞች ፕሮግራም መጪ ዕድል ምን እንደሚሆን መተንበይ አስቸጋሪ ነው። ፕሮግራሙ መቼ እንደሚከፈት አናውቅም። የፕሬዚደንት ትራምፕ ማስፈጸምያ ትእዛዝን በመቃወም ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ አሁንም በሂደት ላይ ይገኛል፤ የመጨረሻውን ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ምን ያህል ግዜ እንደሚፈጅ አናውቅም።
እኔ ልዩ የስደተኛ ቪዛ (Special Immigrant Visa (ኤስ አይ ቪ SIV) ለማግኘት በማመልከት ላይ የምገኝ የአፍጋን ወይም የኢራቅ ዜጋ ነኝ። ይህ በትራምፕ አስተዳደር የተደረገ ማንኛውም ዓይነት የማቆም ሂደት ወይም ሌሎች ለውጦች በእኔ የኤስ አይ ቪ (SIV) ማመልከቻ ላይ ተጽእኖ ሊያደርግ ይችላልን?
የኤስ አይ ቪ (SIV) ፕሮግራም የአሜሪካ የስደተኛ ሂደት አካል አይደለም። ይሁንና ፕሬዚደንት ትራምፕ፤ የአንዳንድ አገሮች ዜጋዎች፤ አፍጋኒስታንም ጭምር፤ ወደ አሜሪካን አገር እንዳይገቡ የሚከለክል ሌላ የጉዞ ማዕቀብ ወይም እገዳ አድርገዋል። ስለዚሁ የጉዞ ማዕቀብ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ላይ ያንብቡ። ስለዚህ ምንም እንኳን ይህ የኤ አይ ቪ (SIV ) ፕሮግራም በስደተኞች ፕሮግራም መቆም ተጽእኖ የማይደርስበት ቢሆንም፤ በተደረገው የጉዞ ማዕቀብ ተጽእኖ ይደርስበታል። ለኢራቃውያን የ ኤስ አይ ቪ (SIV) አመልካቾች የተደረገ የጉዞ እገዳ ግን የለም።
በተጨማሪም ማወቅ ያለቦት የኤስ አይ ቪ ( SIV) አመልካቾች በሚያደርጉት የ ኮም (COM) ማማልከቻዎችም ላይ ለውጦች መደረጋቸውን ነው። በሂደት ላይ ባሉ ጉዳዮች ላይ መንግስት ማንኛውንም አዲስ የኮም (COM) ማመልከቻዎችንም ሆነ ዶኩመንቶችን አይቀበልም። በኮም (COM) ማመልከቻዎች ላይ ስለተደረጉ ለውጦች በበለጠ ለመረዳት ከፈልጉ እዚህ ላይ ያንብቡ።
ይህ የመቆም ሁኔታ በአፍጋን ፒ-1/ፒ-2 (Afghan P-1 / P-2) ፕሮግራም በኩል በሚያመለክቱ የአፍጋን ተወላጆች ጉዳይ ላይ ጫና ሊያደርግ ይችላልን?
አዎን። የስደተኞች ማመልከቻዎች በሙሉ፤ በአፍጋን ፒ-1/ፒ-2 (Afghan P-1 / P-2) ፕሮግራምም ጭምር የገቡ ጉዳዮች፤ ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ ጫና የሚያደርግባቸው ናቸው።
የትራምፕ አስተዳደር፤ የአሜሪካን መንግስት ከአፍጋኒስታን ለሚጓዙ አፍጋኖች ያደርገው የነበረውን “የቦታ መቀየር እርዳታ” (CARE relocation) አቋርጦታልን?
የአሜሪካን መንግስት፤ ቀደም ሲል ከአፍጋኒስታን ወደ አሜሪካ ለሚመጡ የተወሰኑ አፍጋኖች ያደርግ የነበረውን የቦታ መቀየር እርዳታ አስተባባሪ መስርያ ቤትን (Afghan Relocation Efforts (CARE) ዘግቷል።
የቤተሰቤ አባል የሆነ ሰው ወደ አሜሪካን አገር መጥቼ ከእርሱ ጋር እንድቀላቀል አመልክቶልኝ ነበር። አሁንም መምጣት እችላለሁን?
በዚህ በተደረገው የስደተኞች ፕሮግራም መቆም ምክንያት፤ አንዳንድ በቤተሰብ ላይ የተመረኮዙ የኢሚግሬሽን ማመልከቻዎች አልተነኩም። ይሁንና ፕሬዚደንት ትራምፕ የአንዳንድ የተወሰኑ አገሮች ዜጎች ወደ አሜሪካን አገር ፍጹም እንዳይገቡ የጉዞ እገዳ አድርገዋል እንዲሁም የኢሚግሬሽን ቪዛ እንደከለከሉ አድርገዋል። ምናልባት የተደረገው የጉዞ እገዳ እና/ ወይም የስደተኞች ቪዛ መከልከል የሚመለከቶት እንዳይሆን ለማረጋገጥ እዚህ ይመልከቱ።
ይህ የቆመው የስደተኞች ፕሮግራም የማይመለከታቸው ጉዳዮች ምን ዓይነቶች ናቸው?
-
የቤተሰቦ አባል ራሱ ጥገኛ (asylee) ከሆነ፣ ጥገኛ የሆነን ቤተሰብን ለመቀላቀል I-730 (ለመቀላቀል ተከተል follow-to-join asylee”) የተባለ ፕሮግራም ማመልከቻ በመሙላት ወደ አሜሪካን አገር እንዲመጡ ያመለከቱ ከሆነ ይህ የስደተኞች ፕሮግራም መቆም አይመለከቶትም።
- “ ጥገኞች” (Asylees) የሚባሉት፤ በአሜሪካን አገር ውስጥ እያሉ የጥገኝነት ወረቀት ያገኙ ናቸው። የ I-730 ሂደትን በመጠቀም ወደ አሜሪካን አገር እንዲገቡ የሚያመለክቱ የጥገኞች የቤተሰብ አባላት፤ ጉዳያቸው የዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) አካል ስላልሆነ፤ ይህ የማስፈጸምያ ትእዛዝ አይመለከታቸውም።
- ይሁንና በሚመጡበት አገር ላይ በመመርኮዝ ይህ የ I-730 ሂደት በተደረገው የጉዞ ገደብ (travel ban) እና የስደተኞች ቪዛ የመስጠት ጉዳይ መቆም ሊነካ ይችላል።
- ለጥገኞች ስለሚደረገው የ I-730 ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ይመልከቱ።
-
I-130: ዘመድዎ ወደ አሜሪካን አገር ሊያስመጣዎት በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘ የኢሚግሬሽን የI-130 ፎርም ወይም ማመልከቻ ያስገባሎት ከሆነ፤ ጉዳዮ በዚህ በስደተኞች ፕሮግራም መቆም አይነካም።
- ይህ በቤተሰብ ላይ የተመረኮዘ ቤተሰብን የማስመጣት I-130 የተባለ ፕሮግራም የሚያገለግለው ብቁ የሆነ የቤተሰባቸውን አባል ወደ አሜሪካን አገር ለማምጣት የሚፈልጉ የአሜሪካ ዜጎችንና ህጋዊና ቋሚ የመኖርያ ወረቀት ግሪን ካርድ (green card) ያላቸውን ሰዎች ነው። ይህ የአመጣጥ ዘይቤ የዩ ኤስ አር ኤ ፒ ( USRAP) አካል አይደለም። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።
- ይሁንና ይህ የ I-130 ማመልከቻ፤ የቤተሰቡ አባል ከየትኛው አገር በመምጣት ላይ መሆኑ ላይ የሚመርኮዝ በመሆኑ አሁንም ቢሆን በተደረገው የጉዞ እገዳና የኢሚግሬሽን ቪዛ መከለከል ሁኔታ ሊነካ ይችላል።
በዚህ የስደተኞች ፕሮግራም መቆም ጉዳይ የሚነኩ ጉዳዮች
- የቤተሰቦ አባል ራሱ ስደተኛ (refugee) ከሆነና ቤተሰብን ለመቀላቀል I-730 (follow-to-join asylee”) የተባለ ፕሮግራም ማመልከቻ በመሙላት ወደ አሜሪካን አገር እንዲመጣ ያመለከተ ስደተኛ ከሆነ: ጉዳዩ ይቆማል። የስደተኞች ጉዳይ በሙሉ እንዲቆም በመታዘዙና የመንግስት ተቋማት የጉዳዮቹን ሂደትና የጉዞ ሁኔታን በሙሉ እንዲቆሙ በማድረጋቸው ጉዳዮም በዛው ልክ ይቆማል። ስለዚህ I-730 የበለጠ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ያገኛሉ።.
- ዘመዶ ወደ አሜሪካን አገር እንዲገቡ ያስገባሎት ማመልከቻ ፕራዮሪቲ 3 (ፒ 3) ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ፕሮግራም በተባለ ፕሮግራም “Priority 3” (P-3) Family Reunification program) በኩል ከሆነ ጉዳዮ እንዲቆም ተደርጓል።
- ዜግ ነትዎ ኢራቃዊ ወይም ሶርያዊ ከሆነና ዘመድዎ ወደ አሜሪካን አገር እንዲመጡ ያስገባሎት ማመልከቻ በ ዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) የI-130 ልዩ ፕሮግራም በኩል ከሆነ፤ በዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) በኩል የገባው ጉዳዮ እንዲቆም ተደርጓል። የI-130 ጉዳዮም በተደረገው የጉዞ እገዳና የስደተኞች ቪዛ መቆም ጫና ሊደረግበት ይችላል።
- ዘመድዎ ወይም ሌላ ሰው በ’እንኳን በደህና መጡ ‘ዌልካም ኮር ( Welcome Corps) ፕሮግራም በኩል ከሆነ ወደ አሜሪካ እንድትመጡ ማመልከቻ ያስገባሎት ጉዳዮ ቆሟል።
- ዘመድዎ ወደ አሜሪካ እንድትመጡ በሴንትራል ኣሜሪካውያን የህጻናት ፕሮግራም (Central American Minors (ካም CAM) Program) በኩል ከሆነ ማመልከቻ ያስገባሎት፤ ጉዳዮ ቆሟል።
ይህ የመቆም ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች የበላይ ኮሚሽነር (United Nations High Commissioner for Refugees (ዩ ኤን ኤች ሲ አር UNHCR) ስር የሚገኙ ጉዳዮችን ይመለከታልን?
አይመለከትም። ይህ የመቆም ሁኔታ በዩ ኤን ኤች ሲ አር (UNHCR ) ስር ባሉ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ የስደተኞችና የመልሶ መቋቋም ውሳኔን አይመለከትም። ይሁንና ዩ ኤን ኤች ሲ አር (UNHCR ) በአሜሪካን አገር ውስጥ እንድትቋቋሙ ከመራዎትና በወቅቱ ያሎት ጉዳይ የ ዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) ጉዳይ ከሆነ በአሜሪካን አገር ያሎት የመልሶ መቋቋም ጉዳይ በተደረገው የማስፈጸምያ ትእዛዝ ቆሟል ማለት ነው።
በዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) በኩል በአሜሪካን አገር ውስጥ እንድቋቋም ከተደረኩና በአሁኑ ግዜም ያለሁት አሜሪካን አገር ውስጥ ከሆነ፤ ይህ የስደተኞች ጉዳይ እገዳ በሁኔታዬ ላይ ጫና ያደርጋልን?
እገዳው ጫና የሚኖረው ከአሜሪካን አገር ውጪ ባሉና ወደ አሜሪካን አገር በዩ ኤስ አር ኤ ፒ ( USRAP) በኩል ለመግባት በሚፈልጉ ስደተኞች ላይ ብቻ ነው። አሜሪካን አገር ውስጥ ካሉ ግን እገዳው በኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ላይ ጫና አያደርግም።
ይሁንና በአሜሪካን አገር ውስጥ ያሉ ስደተኞችን የሚመለከቱ ሌሎች አዲስ ፖሊሲዎች አሉ። ለምሳሌ፤ መንግስት “ወደኋላ ዞሮ” በአሜሪካ ውስጥ ያሉ የስደተኞችን ጉዳይ እንደገና እየተመለከተ ነው። ስላለፈው የስደተኛ ጉዳዮ፤ ከመንግስት የሆነ ዓይነት ደብዳቤ ካገኙ ወደነዚህ ምንጮች ይመልከቱ።
በአሜሪካ ውስጥ ያሉ ስደተኞች ምን ማወቅ እንደሚያስፈልጋቸው በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ከፈልጉ እዚህ ይመልከቱ።
በአሜሪካን አገር ውስጥ እንድቋቋም የተደረኩት በዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) በኩል ከሆነ ወይም ወደ አሜሪካ የገባሁት በ ኤስ አይ ቪ ( SIV) ከሆነና ለስደተኞች የሚሰጥ ጠቀሜታ የምቀበል ከሆነ፤ የትራምፕ አስተዳደር ለስደተኛ ተቋሞች የሚሰጥ የገንዘብ እርዳታ ላይ የሚያደረገው እገዳ በእኔ ላይ ተጽእኖ ሊያደርግ ይችላልን?
ይህንን የስደተኞች ፕሮግራም እገዳ በመቃወም ፍርድ ቤት ለቀረበው ክስ በቅርቡ ምላሽ የሰጠው የፍርድ ቤት ትእዛዝ፤ መንግስት ለስደተኞች አገልግሎትና አሜሪካን አገር ውስጥ ላሉ ኤስ አይ ቪ ( SIV) የሚያደረገውን የገንዘብ እርዳታ እንዲቀጥል የሚል ውሳኔ የሚሰጥ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችና ምንጮች
የአሜሪካ የስደተኞች የመልሶ ማቋቋም ሂደት ምንድነው?
የአሜሪካ የስደተኛ ወረቀት ለማግኘት ያስገባሁት ማመልከቻ ምን ላይ እንደደረሰ እንዴት ነው ማወቅ የምችለው?
የዩ ኤን ኤች ሲ አር (UNHCR) የመልሶ ማቋቋም ሂደት ምንድነው?
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.