የይዘት ማውጫ
ይህ ጽሁፍ የታደሰው ሰኔ (June) 9 ቀን 2026 ነው።
አስፈላጊ ማስታወሻ፡
ህዳር (November) 21 ቀን 2025 ላይ የአሜሪካ መንግስት ከጥር (January) 21 ቀን 2021 እስከ የካቲት (February) 20 ቀን 2025 ድረስ ወደ አሜሪካን አገር የገቡ ስደተኞችን ጉዳይ እንደገና እንደሚያጠና አስታወቀ። በአሁኑ ወቅት ግሪን ካርድ (green card) ያላቸውንና ግሪን ካርድ ለማግኘት ማመልከቻ ያስገቡና መልስ ወይም ውሳኔ ለማግኘት በመጠባበቅ ላይ ያሉትን ሁሉ ያጠቃልላል። ስለዚሁ የስደተኞች ዳግመ - ጥናት በተመለከተ በበለጠ ዝርዝር ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።
አጭር መግለጫ
አሜሪካን አገር ውስጥ የምትኖሩ ስደተኛ ከሆኑ፤ ምን ማድረግ እንደሚፈቀድሎት፣ ያያዙት ወረቀት ምን ማለት እንደሆነና እራሶን እንዴት መጠበቅ/መከላከል እንደሚችሉ ጥያቄ ሊኖሮት ይችላል። ይህ ጽሁፍ የሚከተሉትን ያስረዳል፤
- አሜሪካን አገር ውስጥ “የስደተኛ ወረቀት” መያዝ ምን ማለት እንደሆነ
- ማንም ሰው ሲጠይቆት ማንነቶን ለማስረዳት ወይም ለማረጋገጥ እንዴት እንደሚቻሉ
- የያዙት ወረቀት ምን ያህል ግዜ እንዲሚቆይ
- ከአገር ልትባረሩ መቻሎንና አለመቻሎን
- ብቁ ሆነው የሚገኙባቸው ጠቀሜታዎች
- ቤተሰቦን ማስመጣት መቻሎንና አለመቻሎን
- ከአገር ውጭ መጓዝ መቻሎንና አለመቻሎን
- አሜሪካን አገር ውስጥ “የስደተኛ ወረቀት” መያዝ ምን ማለት እንደሆነ
አሜሪካን አገር ውስጥ የስደተኛ ወረቀት መኖር ምን ማለት ነው?
የስደተኛ ወረቀት ማለት አንድ ዓይነት የኢሚግሬሽን ሁኔታ ነው።
“የስደተኛ ወረቀት” ወይም የስደተኛ ሁኔታ(Refugee status) ሲባል በአሜሪካን አገር የተለየ የኢሚግሬሽን ሁኔታ ማለት ነው። “የስደተኛ ወረቀት” ካሎት የአሜሪካ መንግስት፤ በአሜሪካ ህግ መሰረት ስደተኛ ሊያስብሎት የሚያስችልዎትን መስፈርቶችን ያሟላሉ ብሎ ወስኗል ማለት ነው። ብህጉም መሰረት ስደተኛ ሲባል፡
- ከአገሩ ውጭ የሆነ ሰው
- በዘር፣ በሃይማኖት፣ በብሄር፣ በፖለቲካ አስተያየት፣ ወይም በአንድ የተለየ ማህበራዊ ቡድን ውስጥ አባል በመሆን ምክንያት ወደ አገሬ ከተመለስኩ በላዬ ላይ ጉዳት ሊደርስብኝ ይችላል ብሎ የሚፈራና ወደ አገሩ ለመመለስ የማይችል ወይም የማይፈልግ ግለሰብ ነው።
- ሌሎች አያሌ ህጋዊ ምክንያቶችን የሚያሟላ ነው።
የአሜሪካ የስደተኛ ሁኔታ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኛ ሁኔታ (ዩ ኤን ኤች ሲ አር UNHCR) የተለየ ነው።
በአሁኑ ወቅት በመነጋገር ላይ ያለነው በአሜሪካን አገር ውስጥ ስላለው የሰደተኛ ሁኔታ መሆኑን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ሰዎች ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም ( ከዩ ኤን ኤች ሲ አር UNHCR) ወይም ከሌላ አገር መንግስት “ የስደተኛ ወረቀት” የሚያገኙ አሉ። በዚህ ጽሁፍ ላይ ያለው መረጃ የሚመለከተው ግን በአሜሪካን መንግስት የተፈቀደ የስደተኛ ወረቀት ያላቸውን ሰዎችን ብቻ ነው። በዩ ኤን ኤች ሲ አር (UNHCR) ስለሚሰጠው የስደተኛ ወረቀት መረጃ ከፈለጉ የ ዩ ኤን ኤች ሲ አር (UNHCR) ምንጮቻችንን ይጎብኙ።
የስደተኛ ወረቀት ወይም የስደተኛ ሁኔታ ከጥገኛነት ወይም ፐሮል (parole) ከሚባለው የተለየ ነው።
ወደ አገራቸው መመለስ ስለሚያስፈራቸው አሜሪካን አገር ውስጥ ሆነው የኢሚግሬሽን ወረቀት ለማግኘት የሚያመለክቱ ሰዎች የጥገኝነት ወረቀት ሊሰጣቸው ይችላል። በአሜሪካን አገር የኢሚግሬሽን ስርዓት፤ እነኚህ ሰዎች “ጥገኞች” ወይም አሲሊስ (asylees) ተብለው ይጠራሉ። ይህም ከስደተኛ ሁኔታ የተለየ ነው።
አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ፔሮል (parole) በተሰኘ መንገድ ወደ አሜሪካን አገር ይገባሉ። ይህ ፔሮል ((parole)ም ከስደተኛ ሁኔታ የተለየ ነው። ፔሮል ማለት ወደ አሜሪካን አገር ለመግባትና በግዜያዊነት ለመቀመጥ ፈቃድ የሚሰጥ ሁኔታ ነው።
የስደተኛ ሁኔታ እንዳለኝ እንዴት ነው የማውቀው?
“የስደተኛ ሁኔታ” (refugee status) እንዳሎት የሚያውቁት፤ ከአሜሪካን አገር ውጪ እያሉና ወደ አሜሪካን አገር የገቡት “የስደተኞች መልሶ ማቋቋምያ ፕሮግራም” እየተባለም በሚታወቀው በአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም በ ዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) በኩል ከሆነና አንድ የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣን ስደተኛ ሊያስብሎት የሚያስችሉ ህጋዊ መስፈርቶችን ያሟላሉ ብሎ ከወሰነ ነው። በተጨማሪም ስደተኛ ልትባሉ የምትችሉት የአንድ የስደተኛ ወረቀት ያለው ግለሰብ የትዳር ጓደኛ ወይም ልጅ ከሆኑ በሱ በኩል የስደተኛ ወረቀት ሊኖሮት ይችላል።
ስደተኛ መሆኔን ለማረጋገጥ ምን ዓይነት ዶኩመንቶችን ነው መጠቀም ያለብኝ?
አንድ ግለሰብ ስደተኛ መሆኑን የሚያረጋግጡለት አያለ ዶኩመንቶች አሉ። ለምሳሌ፡
- የጉዞ መሳፈርያ ደብዳቤ (Transportation boarding letter)፡ አብዛኛውን ግዜ ስደተኞች ወደ አሜሪካ ሲገቡ” የጉዞ መሳፈርያ ደብዳቤ” የሚባል ወረቀት ይዘው ነው የሚመጡት። በስደተኛ ጉዳይ ላይ “ዋናው አመልካች” (principal applicant) እርስዎ ከሆኑ ወይም ከዋናው አመልካች ጋር አንድ ላይ ከመጡ፤ ይህንን ወረቀት አግኝተዋል ማለት ነው። ይህ ወረቀትም ፎቶዎን፣ ስምዎንና ሌላ የግል መረጃዎን የያዘ ነው።
- የቪ93 የጉዞ መሳፈርያ ፈቃድ (V93 boarding foil)፤ ከእርስዎ በፊት ወደ አሜሪካ የገባ የአንድ ስደተኛ “ተከታይ ቤተሰብ”ወይም የትዳር ጓደኛ ወይም ልጅ ከሆኑ፤ ከፓስፖርቶ ገጾች ጋር የተያያዘ ስደተኛ መሆንዎን የሚገልጽ ይህ የጉዞ መሳፈርያ ፈቃድ ይኖሮታል ማለት ነው።
- የስራ ፈቃድ ወረቀት (Employment Authorization Document (ኢ ኤ ዲ EAD)፡ የስራ ፈቃድ ካሎት፣ በካርዶ ላይ ምድብ ከሚለው ስር “(a)(3)” የሚል የማጣቀሻ ኮድ ተጽፎ ይገኛል። ይህም የሰደተኛ ወረቀት እንዳሎት የሚያረጋግጥ ነው።
- አይ-94 (I-94)፡ አሜሪካን አገር የሚገቡ አብዛኛዎቹ ሰዎች አይ-94 (I-94) የተባለ ጽሁፍ ይቀበላሉ። ይህም “የመግባት/ የመውጣት ሰነድ” (Arrival/Departure Record ) በመባል ይታወቃል። ይህም ሰነድ ወደ አሜሪካን አገር በህጋዊ መንገድ እንደገቡ የሚያረጋግጥ ነው። አብዛኛዎቹ ወደ አሜሪካን አገር የሚመጡ ሰዎች የዚህን ፎርም የወረቀት ቅጂ አያገኙም። አብዛኛውን ግዜ ይህንን የእርስዎን አይ-94 (I-94) ቅጂ በ ሲ ቢ ፒ ድረ ገጽ (the CBP website) ያገኙታል። የስደተኛ ወረቀት ካሎት በአይ-94 (I-94) ወረቀትዎ ላይ ያለው “የመግብያ ምድቦ” (Class of Admission ) “RE” የሚል ኮድ እና ምናልባትም ከጎኑ ቁጥር እንደ “RE1” የመሰለ ተጽፎበት ይገኛል።
በኤሌክትሪካዊ መንገድ አይ -94 ( I-94)ን ለማግኘት ችግር ካጋጠሞት የአስተዳደር ስህተት ወይም የመረጃ አሰባሰብ ችግር ሊሆን ይችላል። እዚህ ከተዘረዘሩት ሰነዶች ውስጥ አንዱንም ማግኘት ካቃትዎት ወይም ምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ወይም ሁኔታዎን እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ማወቅ ከፈለጉ፤ የኢሚግሬሽን ጠበቃ ለማግኘት ከወደታች የቀረቡትን ምንጮች መጠቀም ይችላሉ።
የአይስ (ICE) አባሎች ያለኝን የስደተኛ ወረቀት ከተጠራጠሩት ምን ማድረግ አለብኝ?
የኢሚግሬሽን አባሎች (ICE) ወደ ቤትዎ ከመጡ፤ የፍርድ ቤት ወረቀት ከሌላቸው በስተቀረ፤ በሩን አትክፈቱላቸው። የፍርድ ቤት ወረቀት ማለት በፍርድ ቤት የተሰጠና በክፍለሃገር ወይም በፌደራል ዳኛ ( በኢሚግሬሽን ዳኛ ሳይሆን) የተፈረመ ህጋዊ ዶኩመንት ሁኖ የህግ አስከባሪዎች ቤትዎ ውስጥ እንዲገቡ፣ እንዲያስሮት ወይም ቤትዎን ለመፈተሽ ፈቃድ የሚሰጥ ወረቀት ነው።
ህግ አስከባሪዎች ቤትዎ ውስጥ ለመግባት የፍርድ ቤት ትእዛዝ ሊያሳዩዎት ይገባል። ከወደታች አስፈላጊውን የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንደምሳሌ የሚያሳይ ሰእል ቀርቧል፤ ወደ ቤትዎ የመጣው መኮንን የፍርድ ቤት ትእዛዝ አለኝ ብሎ ሲናገር፤ የትእዛዝ ወረቀቱን ከበሩ ስር ባለው ቀዳዳ እስገብቶ ወይም በመስኮት እንዲያሳዮት ይጠይቁ። የፍርድ ቤት ትእዛዝ ወረቀት ካላሳይዎት በስተቀር ግን በሮን ፍጹም አትክፈቱ። መኮንኖቹ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ቢኖራቸውም እንኳን፤ እርሶ ዝም የማለት፣ ለሚጠይቅዎት ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ላለመስጠትና ጠበቃ የመጥራት መብት አሎት ።
እንደምሳሌ የቀረበ የፍርድ ቤት ትእዛዝ
የሰእሉ ባለቤት: ብሄራዊ የስደተኞች ፍትህ ማእከል (National Immigrant Justice Center)
መኮንኖቹ፤ በኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ማጠናከርያ ( Immigration and Customs Enforcement (አይስ ICE) ባለስልጣናት የተፈረመ “የአይስ ማዘዣ” (ICE warrant) ወይም “ የአስተዳደር ማዘዣ ወረቀት” (administrative warrant) ሊያሳይዎት ይችላሉ።
የአስተዳደር ማዛዣ ምሳሌ፤ ( Administrative Warrant) - የኢሚግሬሽንና የጉምሩክ ማጠናከርያ መስርያ ቤት አይስ (Immigration and Customs Enforcement (“ICE”) ይህ ማዘዣ በዳኛ አልተፈረመም ፣ በመሆኑም መኮንኖች ካለርስዎ ፈቃድ ቤትዎ ውስጥ እንዲገቡ ፍቃድ አይሰጥም፡
የሰእሉ ባለቤት: ብሄራዊ የስደተኞች ፍትህ ማእከል (National Immigrant Justice Center)
የሰእሉ ባለቤት: ብሄራዊ የስደተኞች ፍትህ ማእከል (National Immigrant Justice Center)
የአይስ (ICE) መኮንኖች በአደባባይ ስለ ሁኔታዎ ቢጠይቅዎት፤ ስለስደተኛ ሁኔታዎ ከላይ የተጠቀስውን እንደማረጋገጫ ይስጧቸው፤ ዕድሜዎ ከ18 ዓመት በላይ ከሆነ እነኚህን ከታች የተጠቀሱትን ሰነዶች ሁሌም ከእርስዎ ጋር ይያዙ፡
- አይ-94 (I-94) የመግብያ/የመውጭያ ወረቀት (Arrival/Departure record)
- የጉዞ መሳፈርያ ደብዳቤ (Transportation Boarding Letter (ወይም መሳፈርያ መዝገብ boarding foil)
- የስራ ፈቃድ ዶኩመንት (Employment Authorization Document) ወይም የስራ ፈቃድ ካርድ (work permit card)
- ግሪን ካርድ ( green card) ለማግኘት አመልክተው ከሆነ ያመለከቱበትን ወረቀት ቅጂ የሚያሳይ ( እንደ አይ-797C (I-797C) የመስለ የደረሰኝ ወረቀት (Receipt Notice)
ማስታወስ ያለቦት ሁሌም ቢሆን የአስፈላጊ ዶኩመንቶች ቅጂ መያዝ እንጂ ኦሪጂናል መያዝ ጥሩ እንዳልሆነ ነው ምክንያቱም ሊጠፉ ወይም ሊሰረቁ ይችላሉና። በወታደሮች እንዲቆሙ ቢደረጉም፤ አጠገብዎ ጠበቃ ከሌለ በስተቀረ፤ ለሚጠየቁት ጥያቄዎች መልስ አልሰጥም ማለት ወይም አልፈተሽም ማለት መብትዎ ነው።
የኢሚግሬሽን ሁኔታዎን የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ቢጠራጠሩም እርሶ ተረጋጉ። ማስታወስ ያለቦት አሜሪካን አገር ውስጥ ያሉት በህግ በተሰጦት ፈቃድ መሰረት መሆኑን ነው። ይህ ፈቃድ ደግሞ መቼም ቀን ቢሆን የሚቃጠል አይደለም።
የኢሚግሬሽን ጠበቃ ካሎት የጠበቃውን መረጃ በእጅዎ ከእርሶ ጋር በቅርብ መያዝ አለቦት ።
ከኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር መገናኘት የሚያሳስቦት ከሆነ፤ ሬዲናው (ReadyNow) የተባለውን አፕ (app) ወደ ስልኮ ማውረድን ግምት ውስጥ ያስገቡ። ይህ አፕ (app) የተጀመረው ወይም የተመሰረተው ለኢሚግሬሽን ደህንነት በቆሙ ተቆርቋሪዎች ነው። በአይስ ( ICE) ከተያዙ ወድያውኑ አስቸኳይ ዕቅድ እንዲያወጡና የማስጠንቀቅያ ወይም የማንቅያ ስርዓት እንድትመሰረቱ የሚያግዞትና አስቀደመው የመረጡዋቸው ሰዎች የመያዞን ዜና ተቀላጥፈው እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው።
አንዳች ስንክልና ያለቦት ስደተኛ ከሆኑ ደግሞ ከአይስ (ICE ) ጋር ሲገናኙ መብቶችዎን በተመለከተ የሚያስረዱ ተጨማሪ መረጃዎች እዚህ ያገኛሉ።
በአያሌ ቋንቋዎች የተዘጋጁና ከኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር ሲገናኙ በደንብ መዘጋጀቶን የሚያሳዮት መጻህፍቶችን ማንበብም ይፈልጉ ይሆናል፡
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights: ከአይስ (ICE) ጋር ከተገናኙ (If You Encounter ICE | National Immigrant Justice Center)
- መብቶችዎን ይወቁ ( Know Your Rights): በኢሚግሬሽን ከተያዙ ወይም ከታሰሩ ምን ማድረግ አለቦት (What to Do if You Are Arrested or Detained by Immigration | National Immigration Law Center)
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights)፡ ህጋዊ ምንጮች (Legal Resource app | National Korean American Service and Education Consortium)
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights): ከህግ አስከባሪዎች ጋር ስትገናኙ ምን ማድረግ እንደሚገባዎት (What to Do in Interactions with Law Enforcement | CLEAR)
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights): የስደተኞች መብቶች (Immigrants’ Rights | ACLU
ይህ የሰደተኛ ወረቀት ምን ያህል ግዜ ነው የሚያገለግለው?
የስደተኛ ወረቀት መቼም ግዜ ቢሆን አይቃጠልም። “እንዲታደስሎ” ማመልከትም አያስፈልጎትም። መንግስት፤ የስደተኛ መብቶን “ሊገፍ” የሚችለው ገና ወደ አሜሪካን አገር ሲገቡ፤ በህጉ መሰረት እንደተገለጸው በእውነትም ስደተኛ ሳይሆኑ ከቀሩ ብቻና መንግስት ስደተኛ አይደሉም ብሎ ሲወስን ብቻ ነው።
የስደተኛ ወረቀት እያለኝ ከአገር ልባረር እችላለሁን?
ምንም እንኳን በአሜሪካን አገር የስደተኛ ወረቀት አንድ ዓይነት ቋሚ የሆነ ህጋዊ የመኖርያ ወረቀት ቢሆንም፤ አንድ ስደተኛ “በመወገድ ሂደት” (removal proceedings) ውስጥ ከገባ በኋላ፣ ከአገር ሊባረርባቸው የሚያስችሉ አንዳንድ ምክንያቶች አሉ። “የመወገድ ሂደት” ሲባል ከአገር የመባረር ሌላው ስም ሲሆን የኢሚግሬሽን ዳኛ ከአገር ይባረሩ ወይም አሜሪካን አገር ውስጥ ይቆዩ ብሎ ውሳኔ የሚሰጥበትን ጉዳይ የሚያካትት ነው።
ለምሳሌ፤ በ”መወገድ ሂደት” ውስጥ ሊገቡ የሚችሉት አንድ ዓይነት ወንጄል ፈጽመዋል ተብለው ሲወነጀሉ ወይም መንግስት የውሸት ዶኩመንቶችን አቅርበዋል ብሎ ሲከሶት ነው። በአንድ ዓይነት ወንጄል ተከሰው የተፈረደቦት ስደተኛ ከሆኑ፤ ምክር ለማግኘት አንድ ብቁ የሆነ የኢሚግሬሽን ጠበቃ ፈልገው ያግኙ።
የስደተኛ ወረቀት መኖር ጥቅሙ ምንድነው?
የስደተኛ ወረቀት ያላቸው ሰዎች አሜሪካን አገር ውስጥ ያሉት በህጋዊ መንገድ መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋቸዋል።
ህዝባዊ ጠቀሜታዎች
ህዝባዊ ጠቀሜታዎች ሲባሉ ብቁ ለሆኑ ሰዎችና ቤተሰቦች በመንግስት የሚደረጉ የእርዳታ ፕሮግራሞች ናቸው። ስደተኛ ከሆኑ አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑ ህዝባዊ ጠቀሜታዎች ለምሳሌ የጤና ጥበቃና የትምህርት አገልግሎት የመሳሰሉ እርዳታ የማግኘት ዕድል አሎት። በተጨማሪም በአሜሪካን አገር ውስጥ የት አካባቢ እንደሚኖሩ ግምት ውስጥ ገብቶ፤ የምግብ እና የመኖርያ ቤት እርዳታም ሊያገኙ ይችላሉ። አብዛኛዎቹ ህዝባዊ ጠቀሜታዎች በገቢ መጠን የሚወሰኑ ናቸው። ይህም ማለት እርዳታውን ለማግኘት ብቁነትዎ የሚሞረከዘው ባሎት የገቢ መጠን ወይም ገንዘባዊ ሁኔታና የቤተሰቦ ቁጥር ወይም ብዛት ላይ ነው።
ባለፈው ሃምሌ ወር 2025 በተላለፈው ህግ መሰረት ግን ስደተኞች በሚያገኟቸው አንዳንድ እርዳታዎች ላይ ለውጥ ተደርጓል። ስለህዝባዊ ጠቀሜታዎች በበለጠ ለማወቅ እዚህ ይመልከቱ ።
ቋሚ የመኖርያ ወረቀትና ዜግነት
ስደተኞች ከግዜ በኋላ ህጋዊና ቋሚ የሆነ የመኖርያ ወረቀት “ግሪን ካርድ” (green card) በመባልም የሚታወቀውን ወረቀት ከዛም በኋላ ዜግነት ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ።
ስራ
በአሜሪካን አገር ስደተኞች በህጋዊ መንገድ ስራ ተቀጥረው መስራት ይችላሉ። የስደተኛ ወረቀት ላላቸው ሁሉ ይህ የስራ ፈቃድ ኦቶማቲክ ነው። ፈቃዱም የሚቃጠል አይደለም። ስራ ለመስራት በኦፊሴል የስራ ፈቃድ ዶኩመንት (employment authorization document) ወይም ኢ ኤ ዲ (EAD) በመባል የሚታወቀው ካርድ የግድ ሊኖሮት አይገባም። ይሁንና ይህ የስራ ፈቃድ በእጅዎ ካለ ለቀጣሪዎችዎ የስራ ፈቃድ እንዳሎትና ለመስራት እንደተፈቀደሎ ለማስረዳት የቀለለ ይሆንሎታል።
አሜሪካን አገር ውስጥ የሚገኙት እንደ ስደተኛ ከሆነ ወደ አሜሪካ ከገቡ በጥቂት ወራት ውስጥ የስራ ፈቃድ ካርድ ይደርሶታል። የስራ ፈቃድ ካርዶን ፍጹም ካልገኙ ግን መተክያ እንዲሰጦት ማመልከት ይችላሉ።
ግሪን ካርድ (green card) ምን ማለት ነው፣ መቼ ነው ግሪን ካርድ ለማግኘት ማመልከት የምችለው?
“ ግሪን ካርድ” (green card) ለህጋዊና ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ (ኤል ፒ አር LPR) ወይም በአሜሪካን አገር ውስጥ በቋሚነት መኖር ለሚያስችል መብት የተሰጠ ሌላው መጠርያ ስም ነው። የአሜሪካ ህግ፣ ስደተኞች አንዴ አሜሪካን አገር ”በአካል ከገቡ” እና ከገቡበት ዕለት ጀምሮ የሚቆጠር ከአንድ ዓመት በኋላ፤ ቋሚ የሆነ የመኖርያ ፈቃድ ለማግኘት እንዲያመለክቱ ይጠይቃል።
ከአሜሪካን አገር ውጪ ከተጓዙ፤ በስደተኛ ወረቀት ስለሆነ የገቡት፤ የአንድ ዓመት ግዜው እስኪሞላ ድረስ በተጠየቀው የአንድ ዓመት ግዜ ተጨማሪ ግዜ ይጠይቃል።
አሜሪካን አገር “በአካል ከገቡ” አንድ ዓመት ሊሞላዎት ሲቃረብ፤ ህጋዊና ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ ለማግኘት እንዲያመለክቱ እንመክራለን። ከገቡ አንድ ዓመት ከመሙላቱ በፊት ማመልከት አስፈላጊ ነው። አሜሪካን አገር ከገቡ እስካሁን ድረስ አንድ ዓመት ካለፎት ግን በተቻለ መጠን ቶሎ ብለው አሁኑኑ ማመልከቻዎን ያስገቡ።
የስደተኛ ግሪን ካርድን (green card) በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ እዚህ ይመልከቱ።
በ2026 የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መመርያ፤ አሜሪካን አገር ውስጥ ከአንድ ዓመት በላይ የተቀመጡና ገና የግሪን ካርድ ማመልከቻ ያላስገቡ ስደተኞችንና በተደረገላቸው የግሪን ካርድ የቃለመጠይቅ ቀነ ቀጠሮ ላይ ያልተገኙ ስደተኞችን መያዝና ማሰር እንደሚጀምር አስታውቋል። ይህ መመርያ የግሪን ካርዳቸውን ማመልከቻ አስገብተው ገና ግሪን ካርዳቸውን ያላገኙትን ስደተኞችንም የሚፈታተንና በላያቸው ላይ የእስራት አደጋ የሚጥል ነው። ኢራፕ (IRAP) ይህንን መመርያ በመቃወም ጉዳዩን ፍርድ ቤት አቅርቦታል። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ ገና በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ባለበት ወቅት መንግስት ስደተኞችን መያዝና ማሰር አይችልም ብሎ
ትእዛዙን ሰጥቷል።
አንዳች ለውጥ ከተገኘ ይህንን ገጽ እናድሳለን ግን እስከ ሰኔ (June) 5 ቀን 2026 ድረስ ባለን መረጃ መሰረት በዚህ መመርያ ስደተኞች መያዝና መታሰር አይችሉም። ስለዚህ የፍርድ ቤት ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።
ከአሜሪካን አገር ውጪ መሄድ እችላለሁን?
ስደተኞች ከአገር ውጪ መጓዝ ይችላሉ ግን ከአገር ከመውጣትዎ በፊት የስደተኞች የጉዞ ዶኩመንት ( Refugee Travel Document (አር ቲ ዲ RTD) የተባለ ሰነድ ያስፈልጎታል። ምንም እንኳን ከአሜሪካን አገር ውጪ ሆነውም ይህንን አር ቲ ዲ (RTD) የተባለ ዶኩመንት ለማግኘት ማመልከት የሚችሉ ቢሆኑም፤ ሃሳቡ የሚደገፍ አይደለም። ምክንያቱም የሂደቱን ደረጃዎች ሁሉ በሌላ አገር ውስጥ ሁነው አሟልተው ለመጨረስ ሊያዳግት ይችላልና። ይህም ከአሜሪካን አገር ውጭ በዘላቂነት ተቀርቅሮ የመቅረት አደጋን ሊያስከትል ይችላል።
የስደተኞችን የጉዞ ወረቀት ለማግኘት መጀመርያ ፎርም I-131 (Form I-131) የተባለ ፎርም ሞልተው፤ ከሌሎች አስፈላጊ ማረጋገጫዎች ጋር ወደ አሜሪካ የዜግነትና የኢሚግሬሽን አገልግሎት (ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ) (United States Citizenship and Immigration Services (USCIS) ማስገባት አለቦት። ይህ ከተፈቀደሎት፤ አብዛኛውን ግዜ ዶኩመንቱ ለአንድ ዓመት ያገለግላል። ስለዚሁ የስደተኛ የጉዞ ፈቃድ እና ዓለም አቀፍ ጉዞ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እዚህ የኢራፕ (IRAP) ጽሁፍ ላይ ይመልከቱ።
በስደተኛ ጉዳዮ ላይ ዋናው አመልካች (principal applicant) እርስዎ ከሆኑና ወደ አገሮ ተመልሰው ከገቡ የስደተኛ መብትዎ ሊገፈፍ እንደሚችል በደንብ አስታውሱ። ምንም እንኳን ግሪን ካርድ ቢኖሮትም፤ እንዲገቡ የተፈቀደሎት እንደ ስደተኛ ስለሆነ፤ ወደ አገሮ ከተመለሱ ያገኙትን የስደተኛ መብቶን አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል። ይህንን የስደተኛ ወረቀት ወይም መብት ሊያገኙ የቻሉት፤ በአገሮ ውስጥ በላዮ ላይ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ተረድተው ከአገሮ መሸሾን በማስረጃ ስላሳዩ መሆኑን አስታውሱ። አሁን ወደ አገሮ እንደገና ከሄዱ፤ መንግስት መጀመርያውኑም እንደ ስደተኛ ብቁ አልነበሩም ብሎ እንዲያምን ምክንያት ይሰጡታል ማለት ነው። ይህም ወደኋላ ግዜ ወደ አሜሪካ ለመመለስ ሲፈልጉ ወይም ወደፊት የኢሚግሬሽን ጠቀሜታዎችን ለማግኘት በሚያመልክቱበት ግዜ ችግር ሊፈጥርቦት ይችላል።
አሜሪካን አገር ስመጣ ባለቤቴና ልጆቼ ከእኔ ጋር አልነበሩም። አሁን ወደእኔ ሊመጡ ይችላሉን?
ባለቤትዎና ዕድሜያቸው ከ 21 ዓመት በታች የሆኑና ያላገቡ ልጆችዎ ከርሶ ጋር ወደ አሜሪካ ካልመጡ፤ ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ወደእርሶ ጋ እንዲመጡ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ። ይህንን አርእስት በተመለከተ የኢራፕ (IRAP)ን ጽሁፍ እዚህ ተመልከቱ።
ተጨማሪ መረጃዎችና ምንጮች
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.