የይዘት ማውጫ
አጭር መግለጫ
ይህ መመርያ፤ የዩ-ኤን-ኤች-ሲ–አር (UNHCR) የስደተኛነት ሁኔታን የመወሰን ሂደት በአጭሩ የሚገልጽ ነው።
የስደተኛነት ሁኔታን መወሰን ሲባል ምን ማለት ነው?
የስደተኛነትን ሁኔታ መወሰን ማለት አንድ ሰው ስደተኛ የመሆኑና ያለመሆኑን ጉዳይ የመወሰን ሂደት ነው። አብዛኛውን ግዜ የስደተኛ መብት እንዲሰጣቸው የሚያመለክቱ ሰዎች ጥገኛነት የሚጠይቁ ሰዎች በመባል ይታወቃሉ። ስደተኛ የሚባሉት የሚከተሉትን በሙሉ የሚያሟሉ ከሆነ ነው። ፤
- የሚገኙት ከአገሮ ውጭ ከሆነ
- ወደ አገሮ ከተመለሱ ጉዳት ይደርስብናል ብለው ፍራቻ ሲኖሮት
- ፍራቻዎ “በደንብ የተመሰረተ” ሲሆን
- ከባድ ጉዳት ይደርስብኛል ብለው የሚፈሩት በሚከተሉት ምክንያቶች ሲሆን፤
- በዘርዎ
- በሃይማኖትዎ
- በብሄሮ
- በፖለቲካ አስተያየትዎ
- በአንድ ማህበራዊ ቡድን አባል በመሆንዎ
- በአገሮ ውስጥ ባለው መንግስት ጉዳት ይደርስቦታል ወይም በአገሮ ውስጥ ያለው መንግስት በሌሎች ሊደርስቦ ከሚችል ጉዳት ሊጠብቆት ወይም ሊከላከልልዎት የማይፈልግ ወይም የማይችል ከሆነ
- በአገሮ ውስጥ ደህንነትዎ ሊጠበቅበት ወደሚችል ቦታ መንቀሳቀስ የማይችሉ ከሆነ
- በተፈጸመ ከባድ ወንጄል ምክንያት ከስደተኛነት ሊገለሉ አይችሉም።
ይህ መስፈርት የወጣው በ1951 በተካሄደው የስደተኛነት ስብስባ (1951 Refugee Convention) ላይ ነው።.
በአያሌ አገሮች፤ አንድ ሰው ስደተኛ ነው ወይስ አይደለም ብሎ የሚወስነው መንግስት ነው። በመንግስት የሚተዳደር አንድ ስርዓት አብዛኛውን ግዜ የጥገኛነት ስርዓት በመባል ይታወቃል። በደርዘን በሚቆጠሩ አገሮች፤ አንድ ሰው ስደተኛ ነው አይደልም ብሎ የሚወስነው ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ነው። ይህ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) አር-ኤስ-ዲ (RSD) የሚያካሂደው የማጣርያ ሂደት ሁሌም በነጻ ነው። ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR)፤ አር-ኤስ-ዲ (RSD)ን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ እዚህ ላይ ይመልከቱ።
በምኖርበት አገር ውስጥ ያለው የስደተኞች የማጣርያ ሂደት (RSD) ምን ይመስላል?
የጥገኛነት ማመልከቻ ማስገባት ከፈለጉ፤ ስደተኛነትን የመወሰን ሁኔታ (RSD) የሚወስነው ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ወይም መንግስት ነው ለሚለው ጥያቄ መጀመርያ መልስ ያግኙ። የአያሌ አገሮች የ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቄዎች ዌብሳይት ውስጥ መረጃ ያገኛሉ
የዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር፣ አር-ኤስ-ዲ (UNHCR RSD) የስደተኞች ማጣርያ ሂደት በተለያዩ አገሮች የተለያየ ሊሆን ይችላል። በአያሌ አገሮች፤ አንድ ሰው መጀመርያ በስልክ ወይም በአካል በዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ጽህፈት ቤት ውስጥ ይመዘገባል። አንዳንዴ፤ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) የጥገኝነት መታወቅያ ካርድና የምዝገባ ቁጥር ወድያዉኑ ይሰጣል። ይህ ግን በምትኖሩበት አገር በዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) የምዝገባ ሂደት ላይ የተመረኮዘ ነው።
ከምዝገባው በኋላ፤ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) የስደተኛነት ማጣርያ (RSD)ቃለመጠይቅ እንድታደርጉ ቀነ-ቀጠሮ ይሰጥ ይሆናል። በዚህ ቃለመጠይቅ የዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ስደተኛ መሆንዎንና አለመሆንዎን ለመወሰን አያሌ ጥያቄዎችን ይጠይቆታል። ኢራፕ (IRAP) ለአር-ኤስ-ዲ ( (RSD) ቃለመጠይቁ እንድትዘጋጁ የሚያግዞትን መረጃ የያዘ መመርያ አለው። ስለ መልሶ መቋቋም ጉዳይም ኢራፕ (IRAP) እዚህ ላይ መረጃ አለው።
በአንዳንድ አገሮች፤ የአንዳንድ ብሔሮች አባሎች በዚህ የግለሰብ የማጣርያ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ አይደረጉም። በአንዳንድ አገሮች፤ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ለእያንዳንዱ ሰው የተናጠል ቃለመጠይቅ ከማድረግ ፈንታ፤ የተወሰነ ብሄር አባል ከሆኑ፤ ካለ ምንም ቃለመጠይቅ በአጠቃላይ የስደተኛነት መብት ይሰጣል።
የስደተኛ ማጣርያ ማመልከቻዬ (RSD) ተቀባይነት ሳያገኝ ከቀረ ከዛ በኋላ ምን ይቀጥላል?
ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR)፤ የስደተኛ ማጣርያ (RSD) ቃለመጠይቅ ካደረጉ በኋላ፤ ጥያቄዎን ካልተቀበለው፤ በሚያውቁትና በሚገባዎት ቋንቋ ደብዳቤ ይልክሎታል። ደብዳቤውም ጥያቄዎ ለምን ተቀባይነትን እንዳላገኘ ምክንያቱን ይዝረዝራል።
ይግባኝ ማለት ይችላሉ። በአብዛኛዎቹ ቦታዎች፤ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR)፤ ይግባኝ ለማለት የ ሰላሳ ቀናት ግዜ ይሰጣል። ይህ ሰላሳ ቀናት እንዳያልፍቦት ይጠንቀቁ። ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) ጥያቄዬን መቀበል ነበረበት በማለት መረጃዎችን በደንብ ማቅረቦን ያረጋግጡ።
ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት ያላገኘ ቢሆንም ወይም አቤቱታ የማስገባት ግዜው ያለፈ ቢሆንም፤ በተወሰኑ ሁኔታዎች፤ ዩ-ኤን-ኤች-ሲ-አር (UNHCR) እንደገና ፋይሎን እንደገና እንዲከፍት መጠየቅ ይችላሉ።
በአንዳንድ አገሮች ውስጥ ነጻ የህግ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ዝርዝር ለማወቅ እዚህ ላይ ይጫኑ፤ አቤቱታዎን በተመለከተ እርዳታ ካስፈለጎት በአገሮ ወስጥ ካለው ድርጅት ወይም ድርጅቶች ጋር ተገናኙ።
ከኢራፕ (IRAP) እርዳታ ከፈለጉ እዚህ መረጃ ላይ ይጫኑ።
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.