የይዘት ማውጫ
አስፈላጊ ማስታወሻ፡ ገና ግሪን ካርዳቸውን (green cards) ያላገኙ በአሜሪካን አገር የሚገኙ ስደተኞች፤ በወጣው አዲስ መመርያ መሰረት፤ በመያዝና በመታሰር አደጋ ላይ ይገኛሉ። የስደተኛ ወረቀት ይዘው በአሜሪካን አገር ውስጥ የምትገኙ ስደተኛ ከሆኑ፤ ምናልባት የ የአይስ (ICE) ወታደሮች ወደ ቤትዎ ከመጡ ምን ማድረግ እንደሚያስፈልጎት ለማወቅ እባኮን ይህንን የኛን መመርያ ይመልከቱ። ወደ ቤትዎ የመጡት ወታደሮች በዳኛ የተፈረመ የፍርድ ቤት ወረቀት ወይም መጥርያ (judicial warrant) ከሌላቸው በሮን መክፈት እንደሌለቦት ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው።
ህዳር (November) 21 ቀን 2025፤ የአሜሪካን መንግስት ከጥር (January) 21ቀን 2021 ጀምሮ እስከ የካቲቲ (February) 20 ቀን 2025 ድረስ ባለው ግዜ ውስጥ ወደ አሜሪካን አገር የገቡ ስደተኞችን ጉዳይ እንደገና የሚያጠና መሆኑን አውጇል። ይህ ዝርዝርም በአሁኑ ግዜ ግሪን ካርድ (green card) ያላቸውንና ግሪን ካርድ ለማግኘት ገና ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉትን ስደተኞችን ይመለከታል። በየካቲት (February) 18 ቀን 2026፤ ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) ግሪን ካርድ (green card) ያላገኙ በተለይም ግሪን ካርድ ለማግኘት ገና ቃለመጠይቅ ያላደርጉ ስደተኞችን በኢሚግሬሽን እስር ቤቶች እንደሚያስር የሚገልጽ አዲስ መመርያ አውጇል።
ይህንን የስደተኞችን ማሰር አዲስ ትእዛዝ በተመለከተ የበለጠ ማስረጃ ለማግኘት እዚህ ይመልከቱ።
ይህ ጽሁፍ ሰኔ (June) 9 ቀን 2026 ታደስ
አጭር መግለጫ
በአሜሪካን አገር ውስጥ የምትገኙ ስደተኛ ከሆኑ፤ ምን ማድረግ እንደሚፈቀድሎ፣ የያዙት ወረቀት ምን ማለት እንደሆነና ራስዎን እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ጥያቄ ሊኖሮት ይችላል። ይህ ጽሁፍ የሚከተሉትን ያብራራል፡
- በአሜሪካን አገር “የስደተኛ ወረቀት” መያዝ ምን ማለት እንደሆነ
- የሆነ ሰው ሲጠይቆት ሁኔታዎን ማረጋገጥ እንዴት እንደሚችሉ
- ያሎት ወረቀት ለምን ያህል ግዜ እንደሚያገለግል
- ከአገር ሊባረሩ ይችላሉን
- ለምን ዓይነት ጠቀሜታዎች ነው ብቁ መሆን የሚችሉት
- ቤተሰቦን ማስመጣት ይችላሉን
- ከአገር ውጭ ለመጓዝ ይፈቀድሎታልን
በአሜሪካን አገር “የስደተኛ ወረቀት” መኖር ማለት ምን ማለት ነው?
“የስደተኛ ወረቀት” አንድ ዓይነት የኢሚግሬሽን ሁኔታ ነው።
በአሜሪካን አገር “የስደተኛ ወረቀት” ሲባል አንድ ዓይነት የኢሚግሬሽን ሁኔታ ማለት ነው። “የስደተኛ ወረቀት” ካሎት፤ የአሜሪካን መንግስት፤ በአሜሪካን ህግ መሰረት፤ ስደተኛ ሊያስብሉ የሚያስችሉትን መስፈርቶችን አሟልተዋል ብሎ ሲወስን ነው። በህጉ መሰረት አንድ ሰው “የስደተኛ ወረቀት” አለው ሲባል የሚከተሉትን የሚያሟላ ነው ማለት ነው፡
- ከራሱ አገር ውጪ ሲሆን
- በአገሩ ውስጥ በዘሩ፣ በሃይማኖቱ፣ በብሄራዊ ማንነቱ፣ በፖለቲካ አስተያየቱ ወይም በአንድ ማህበራዊ ቡድን ውስጥ አባል በመሆኑ ምክንያት፤ አንድ ዓይነት ግፍ ወይም ስቃይ የደረስበት ወይም ወደ አገሬ ከተመለስኩ የሆነ ግፍ ይፈጸምብኛል ብሎ የሚፈራና ወደ አገሩ መመለስ የማይችልና የማይፈልግ ከሆነ
- በአጠቃላይ ሌሎች ህጋዊ የሆኑ መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ
የአሜሪካ የስደተኛ ወረቀት በዩ ኤን ኤች ሲ አር (UNHCR) ከሚሰጠው የሰደተኛ ወረቀት ጋር አንድ ዓይነት አይደለም።
እኛ በዚህን ወቅት በመነጋገር ላይ የምንገኘው በአሜርካን አገር ስለሚሰጠው የስደተኛ ወረቀት መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል። አንዳንድ ሰዎች ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ተቋም (UN Refugee Agency (ዩ ኤን ኤች ሲ አር UNHCR) ወይም ከሌላ አገር መንግስት “የስደተኛ ወረቀት” ተብሎ የሚጠራ ወረቀት የሚያገኙ አሉ። በዚህ ጽሁፍ ላይ የተዘረዘረው መረጃ በሙሉ ግን በአሜሪካን መንግስት “የስደተኛ ወረቀት” በሚያገኙ ስደተኞች ላይ ብቻ የሚያተኩር ነው። በዩ ኤን ኤች ሲ አር (UNHCR) ስደተኛ ስለሚያሰኙ መስፈርቶች በበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ የዩ ኤን ኤች ሲ አር (UNHCR) ምንጮቻችንን ይመልከቱ።
የስደተኛ ወረቀት ከጥገኛነት (asylum) ና ለአጭር ግዜ በአሜሪካን አገር እንዲቀመጡ ከሚፈቀድላቸው ሰዎች (parole) ጉዳይ ጋር የተለያየ ነው።
ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈሩና በአሜሪካን አገር ውስጥ ሁነው የኢሚግሬሽን ወረቀት ለማግኘት የሚያመልከቱ ሰዎች የጥገኝነት ወረቀት (አሳይለም asylum) ሊሰጣቸው ይችላል። በአሜሪካን የኢሚግሬሽን የአሰራር ደንብ መሰረትም አሲሊ (asylees) ተብለው ይጠራሉ። ይህ ከስደተኛ ወረቀት ከመኖር ጋር የተለየ ነው።
አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ፔሮል (parole) በሚባል መንገድ ወደ አሜሪካን አገር የሚገቡ አሉ። ፔሮል የሚባለውም ከስደተኛ የተለየ ነው። ፔሮል ማለት አሜሪካን አገር ውስጥ ለመግባትና በግዜያዊነት ለመኖር ፈቃድ የሚሰጣቸው ሰዎች ማለት ነው።
የስደተኛ ፈቃድ እንዳለኝ እንዴት ነው ማወቅ የምችለው? ይህንንም እንዴት ነው ማረጋገጥ የምችለው?
የስደተኛ ወረቀት (refugee status) የሚኖሮት የአሜሪካን መንግስት ባለስልጣን፤ ገና ከአሜሪካን አገር ውጪ እያሉ፤ ስደተኛ ሊያሰኞት የሚችሉ ህጋዊ መስፈርተኞችን በሙሉ ያሟላሉ ብሎ ሲወስንና በአሜሪካ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም (U.S. Refugee Admissions Program (USRAP) በኩል ወደ አሜሪካን አገር የገቡ ሲሆኑ ነው።
ዩ ኤስ አር ኤ ፒ (USRAP) የስደተኞች መልሶ ማቋቋምያ (refugee resettlement) በመባልም ይታወቃል። የስደተኛ ወረቀት ያለው ግለሰብ ባለቤት ወይም ልጅ ከሆኑም የስደተኛ ወረቀት ሊኖሮት ይችላል፤ በግለሰቡም በኩል አንድ ዓይነት የስደተኛ ወረቀት ያገኛሉ።
የስደተኛ ወረቀት እንዳለኝ ለማረጋገጥ ማሳየት ያለብኝ ዶኩመንቶች ምንድናቸው?
አንድ ግለሰብ የስደተኛ ወረቀት እንዳለው ለማረጋገጥ ሊያሳያቸው የሚችሉ በርካታ ዶኩመንቶች አሉ። ለምሳሌ፡
- የአይሮፕላን መሳፈርያ ዶኩመንት ወይም ደብዳቤ (Transportation boarding letter)፡ ስደተኞች ወደ አሜሪካን አገር ሲመጡ አብዛኛውን ግዜ የአይሮፕላን መሳፈርያ ዶኩመንት ወይም ደብዳቤ (Transportation boarding letter) ይዘው ነው የሚመጡት። በስደተኛ ጉዳዮ ላይ “ዋነኛው አመልካች” (principal applicant) እርስዎ ከሆኑ ወይም ከዋነኛው አመልካች ጋር ባንድ ላይ ከገቡ ይህንን ዶኩመንት ይዘዋል ማለት ነው። ይህ ዶኩመንት ፎቶግራፎን፣ ስሞን እና ሌላ የግል መረጃዎን የያዘ ነው።
- ቪ93 (V93) የመሳፈርያ ወረቀት (boarding foil)፡ ከእርሶ በፊት ቀደም ብሎ ወደ አሜሪካን አገር የገባ ስደተኛ ባለቤት ወይም ልጅ ከሆኑና “ ለመቀላቀል ተከተሉ” (follow-to-join) በሚል ፕሮግራም ከሆነ ወደ አሜሪካን አገር በመግባት ላይ ያሉት፤ ስደተኛ መሆንዎን የሚያስረዳ ከፓስፖርቶ ገጽ ጋር የተያየዘ የመሳፈርያ ወረቀት እርሶም ይኖሮታል።
- ኢ ኤ ዲ (EAD)፡ የስራ ፈቃድ ካሎት፤ የስደተኛ ወረቀት እንዳሎት የሚገልጽ በካርዶ ላይ “ምድብ” (category) በሚለው ስር የሚገኘው ኮድ “(a)(3)” የሚል ተጽፎበት ይገኛል።
- አይ-94 (I-94)፡ ወደ አሜሪካን አገር የሚገቡ አብዛኛዎቹ ሰዎች አይ-94 (I-94) ተብሎ የሚጠራ ፎርም ያገኛሉ፡ ይህም መግብያና መውጭያ ካርድ (Arrival/Departure Record) ተብሎም ይጠራል። ይህም ወደ አሜሪካን አገር በህጋዊ መንገድ እንደገቡ ማረጋገጫ ነው። አብዛኛዎቹ ስደተኞች የዚህ ዓይነቱን ፎርም ቅጂ ላያገኙ ይችላሉ፤ በኦንላይን ወደ ሲ ቢ ፒ ዌብሳይት ( CBP website) ከገቡ አብዛኛውን ግዜ የ“አይ-94” (I-94) ፎርም ቅጂ ማግኘት ይችላሉ። የስደተኛ ወረቀት ካሎት በምን ዓይነት መንገድ እንደገቡ ለማስረዳት በ “አይ-94” (I-94) ፎርሞ ላይ “RE” የሚሉ ፊደሎች ፤ ከፊደሎቹም ጎን ቁጥር የታከበለት ለምሳሌ “RE1”ይገኛል።
የኤሌክትሪክ አይ-94 (I-94) ፎርሙን ለማግኘት ችግር ካጋጠሞት ምናልባት በአስተዳደር ስህተት ወይም መረጃ በማስገባት በተፈጠረ ችግር ሊሆን ይችላል። እዚህ ላይ የተዘረዘሩትን ዶኩሜንቶች ማግኘት ካልቻሉ ወይም ያሎት የመኖርያ ፈቃድ ምን ዓይነት መሆኑን በሚመለከት ጥያቄ ቢኖሮት ወይም የመኖርያ ሁኔታዎን እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ ማወቅ ከፈለጉ፤ ከወደታች የተዘረዘሩትን ምንጮች በመጠቀም የኢሚግሬሽን ጠበቃ ለማግኘት ይሞክሩ።
አይስ (ICE) የያዝኩትን የስደተኛ ወረቀት ከተጠራጠረ ምን ማድረግ አለብኝ?
የኢሚግሬሽን መኮንኖች አይስ (ICE) ወደ ቤትዎ ከመጡ፤ የፍርድ ቤት ወረቀት ካልያዙ በስተቀረ፤ በሮን አይክፈቱላቸው። ቤትዎ ውስጥ ለመግባት መኮንኖቹ (በኢሚግሬሽን ዳኛ ሳይሆን) በክፍለ ሃገር ወይም በፌደራል መንግስት ዳኛ የተፈረመ ወረቀት ማሳየት አለባቸው። ይህም “ የፍርድ ቤት ትእዛዝ” (judicial warrant) ይባላል። ከታች በምሳሌነት የቀረበ ትክክለኛ የሆነ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ይገኛል። ይህን የፍርድቤት ትእዛዝ በበሮ ስር ባለው ክፍተት አስገብተው ወይም በመስኮት እንዲያሳይዎት መኮንኖቹን ይጠይቁ። ይህንን ካላሳይዎት ግን በሮን መክፈት የለቦትም።
መኮንኖቹ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ቢኖራቸውም እንኳን፤ ዝም የማለት፣ ጥያቄ ሲጠይቆት መልስ ያለመስጠት፣ ጠበቃዎን የመጥራት መብት አሎት ።
የስዕል ባለቤት፡ ናሽናል ኢሚግራንት ጃስቲስ ሴንተር (National Immigrant Justice Center )
በምሳሌነት የቀረበ የፍርድ ቤት ትእዛዝ - ይህ ትእዛዝ በፍርድቤት የተሰጠ እና በዳኛ የተፈረመ ሲሆን መኮንኖቹ ቤትዎ ውስጥ እንዲገቡ ፈቃድ የሚሰጥ ነው፡
መኮንኖቹ፡ በኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ማጠናከርያ መስርያ ቤት (Immigration and Customs Enforcement (“ICE”) ባለስልጣኖች የተፈረመ የአይስ ትእዛዝ (ICE warrant) ወይም የአስተዳደር ትእዛዝ (administrative warrant) ሊያሳዮት ይችሉ ይሆናል። ይህ ግን በዳኛ የተፈረመ ስላልሆነ ወታደሮቹ፤ ካለ እርሶ ፈቃድ፤ ወደ ቤትዎ እንዲገቡ ፈቃድ የሚሰጥ አይደለም።
በምሳሌነት የቀረበ የአስተዳደር ትእዛዝ - ይህ ትእዛዝ በዳኛ የተፈረመ ስላልሆነ፤ መኮንኖቹ፤ ካለ እርሶ ፈቃድ፤ ቤትዎ ውስጥ እንዲገቡ የሚፈቅድ አይደለም፡
የስዕሉ ባለቤት፡ ናሽናል ኢሚግራንት ጃስቲስ ሴንተር (National Immigrant Justice Center)
የስዕሉ ባለቤት፡ ናሽናል ኢሚግራንት ጃስቲስ ሴንተር (National Immigrant Justice Center)
የአይስ (ICE) ወታደሮች ህዝብ በተሰበሰበት አደባባይ ስለያዙት የፈቃድ ወረቀት ጥያቄ ሊጠይቆት ከፈለጉ፤ የስደተኛ ወረቀት እንዳሎት ለማረጋገጥ ከወደላይ የተዘረዘሩትን ዶኩመንቶች ማሳየት ይችላሉ፤ ዕድሜዎ ከ18 ዓመት በላይ ከሆነ ከታች የተዘረዘሩትን ዶኩመንቶች ሁሌም ከእርሶ ጋር ይያዙ፡ :
- የአይ-94 (I-94) መግብያና መውጭያ ካርድ (Arrival/Departure record)
- ወደ አይሮፕላን የወጡበት ወረቀት (Transportation Boarding Letter (ወይም boarding foil)
- የስራ ፈቃድ (Employment Authorization Document) ወይም ወርክ ፐርሚት (work permit) ካርድ
- ግሪን ካርድ ( green card) ለማግኘት አመልክተው ከሆነ፤ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያለው የግሪን ካርድ ማመልከቻዎን ማረጋገጫ ( ለምሳሌ I-797C የደረሰኝ ወረቀት (Receipt Notice) ያሳዩ።
እዚህ ላይ ሁሌም ማስታወስ ያለቦት፤ ዶኩመንቶች ሊጠፉ ወይም ሊሰረቁ ስለሚችሉ፤ ዋነኛዎቹን ዶኩመንቶችዎን ከመያዝ ይልቅ ቅጂያቸውን መያዝ እንደሚሻል ነው፡፡ በመኮንኖቹ ከታያዙም ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ጥያቄ ስትጠየቁ፤ ጠበቃዎ ከእርሶ ጋር እስከሌለ ድረስ፤ መልስ አልሰጥም፣ አልፈተሽም የማለት መብት አሎት ።
የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ስለ ኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ጥያቄ ሲጠይቆት ተረጋጉ፣ እርስዎ አሜሪካን አገር ውስጥ ያሉት በህጋዊ መንገድ መሆኑንም ያስታውሱ። ይህ የያዙት የስደተኛ ወረቀት መቼም ቀን አይቃጠልም።
የኢሚግሬሽን ጠበቃ ካሎት፤ አድራሻውንና የስልክ ቁጥሩን ከእርሶ ጋር ይያዙ።
ከኢሚግሬሽን መኮንኖች ጋር የመገናኘት ስጋት ካሎት፤ ሬዲናው (ReadyNow!) የሚል አፕ (app) ወደ የእጅ ስልኮ ማውረድን (download) ግምት ውስጥ ያስገቡ። ይህ አፕ በ ኢሚግሬሽን ጠበቃዎች የተዘጋጀ ሲሆን የአደጋ ግዜ ዕቅድ እንድታወጡና በአይስ (ICE) ከተያዙ ሌሎችን ለማሳወቅ መረጃ ለመስጠት ይረዳል።
የአካል ጉዳተኛ ስደተኛ ከሆኑ ከICE ጋር ሲገናኙ ስለ መብቶችዎ ተጨማሪ መረጃዎችን እዚህ ማግኘት ይችላሉ።
ምናልባት ከኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር ከተገናኙ ተዘጋጅተው ለመቅረብ እንዲችሉ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የሚከተሉትን ጽሁፎችን ማንበብም ይፈልጉ ይሆናል፡
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights): ከአይስ (ICE) ጋር ቢገናኙ (If You Encounter ICE | National Immigrant Justice Center)
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights): በኢሚግሬሽን ቢያዙ ወይም ቢታሰሩ ምንድነው ማድረግ ያለቦት (What to Do if You Are Arrested or Detained by Immigration | National Immigration Law Center)
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights) የህጋዊ ምንጭ አፕ (Legal Resource app | National Korean American Service and Education Consortium)
- መብቶችዎን ይወቁ (Know Your Rights): ከህግ አስከባሪዎች ጋር ሲገናኙ ምን ማደረግ አለቦት (What to Do in Interactions with Law Enforcement | CLEAR)
- መብቶችዎን ይወቁ (Your Rights)፡ የስደተኛ መብቶች ( Immigrants’ Rights | ACLU)
የስደተኛ ወረቀት ምን ያህል ግዜ ነው የሚቆየው?
የስደተኛ ወረቀት መቼም ቀን ቢሆን አይቃጠልም። “ለማሳደስም” ማመልከት አይስፈልጎትም። መንግስት፤ የስደተኛ ወርቀትዎን “እንዳይሰራ የሚያደርገው” ገና ወደ አሜሪካ አገር ሲገቡ (በህጉ አገላለጽ መሰረት) የስደተኛ መስፈርት አላሟሉም ብሎ ሲወስን ብቻ ነው።
የስደተኛ ወረቀት እያለኝ ከአገር ልባረር እችላለሁን?
ምንም እንኳን የስደተኛ ወረቀት በዘላቂነትና በህጋዊ መንገድ በአገር ውስጥ የመኖር ፈቃድ የሚሰጥ ቢሆንም፤ አንድ ስደተኛ “በመባረር ሂደት” ውስጥ ከገባ ወይም በህግ ፊት ከቀረበ በኋላ ከአገር እንዲባረር የሚያስደርጉ አንዳንድ ልዩ ምክንያቶች አሉ። ይህ” የመባረር ሂደት” ማለት ከአገር የመባረር ሂደትን የሚገልጽ ሲሆን ከአገር መባረርን ወይም በአሜሪካን አገር መቆየትን በሚወስን የ ኢሚግሬሽን ዳኛ ፊት ቀርቦ በችሎት (ኦፊሲይላዊ ችሎት) መፈርደን ያመለክታል።
ለምሳሌ፡ አንድ ዓይነት ወንጄል ፈጽመው ሲፈረድቦት በመባረር ሂደት ውስጥ ይገባሉ ወይም መንግስት እውነተኛ ያልሆነ ዶኩመንት አቅርበዋል ብሎ ሲከሶት በመባረር ሂደት ውስጥ ይገባሉ። በሆነ ወንጄል የተከሰሱ ወይም የተወንጀሉ ስደተኛ ከሆኑ ብቁ ከሆነ የኢሚግሬሽን ጠበቃ ጋር በመገናኘት ምክር ይጠይቁ።
የሰደተኛ ወረቀት መኖር ጥቅሙ ምንድነው?
የስደተኛ ወረቀት የተሰጣቸው ሰዎች አሜሪካን አገር ውስጥ ያሉት በህጋዊ መንገድ መሆኑን ማስታወስ እጅግ ጠቃሚ ነው።
የህዝብ ጠቀሜታዎች
ስደተኛ ከሆኑ፤ አስፈላጊ ለሆኑ አገልግሎቶች የሚጠቀሙባቸው አንዳንድ የህዝብ ጠቀሜታዎችን፤ የጤና ጥበቃና የትምህርት አገልግሎቶችን ጭምር፤ ማግኘት ይችላሉ። በተወሰኑ የአሜሪካን አገር ክፍላተ ሃገርም ከምግብና መኖርያ ቤቶች ጋር የተያያዙ ሌሎች ጠቀሜታዎችንም ለማግኘት ይችሉ ይሆናል። አብዛኛዎቹ የሚሰጡ ህዝባዊ ጠቀሜታዎች በሚያገኙት ገቢ ላይና በቤተሰቦ ውስጥ ባለው የሰው ቁጥር የሚለኩ ናቸው። በተጨማሪም ሓምሌ (July) 2025 ላይ ለስደተኞች በሚሰጡ ህዝባዊ ጠቀሜታዎች ላይ አንዳንድ ለውጦች ተደርገዋል። ህዝባዊ ጠቀሜታዎችን በተመለከተ በበለጠ ለመረዳት እዚህ ላይ ይጫኑ።
ዘላቂ የመኖርያ ፈቃድና ዜግነት
በመጨረሻም ስደተኞች ህጋዊና ቀዋሚ የሆነ የመኖርያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ (green card) በመባልም የሚታወቅ) ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ። ከዛ በኋላ ደግሞ ዜግነት ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ ።
ስራ መስራት
አሜሪካን አገር ውስጥ ስደተኞች ስራ መስራት በህግ ይፈቀድላቸዋል። ይህ ፈቃድ የስደተኛ ወረቀት ላላቸው ስደተኞች ኦቶማቲክ ነው፤ ፈቃዱም አይቃጠልም። እንዳውም ስራ ለመስራት በኦፊሴል የስራ መስራት ስልጣን (employment authorization document ወይም ኢ ኤ ዲ EAD) ተብሎ የሚታወቅ የስራ ፈቃድ የግድ ሊኖሮት አስፈላጊ አይደለም። ይሁንና ስራ ለመቀጠር በሚሄዱበት ወቅት፣ የስራ ፈቃድ በእጆ ካሎት፤ የመስራት ፈቃድ እንዳሎት ለቀጣሪዎችዋ በበለጠ ለማስረዳት ይቀሎታል።
አሜሪካን አገር ውስጥ የሚገኙት እንደ ስደተኛ ከሆነ፤ አገር ውስጥ ከገቡ ከጥቂት ወራት በኋላ የስራ ፈቃድ ወረቀትዎ (ኢ ኤ ዲ EAD) ይደርሶታል። የስራ ፈቃዶን (ኢ ኤ ዲ EAD) ፍጹም ካልደረሶት ግን መተክያ እንዲሰጦት ማመልከት ይችላሉ።
ግሪን ካርድ (green card) ምን ማለት ነው? ግሪን ካርድ ለማግኘት መቼ ነው ማመልከት ያለብኝ?
ግሪን ካርድ (green card) ሕጋዊና ዘላቂ ለሆነው የመኖርያ ፈቃድ- ኤል ፒ አር (LPR) የተሰጠ ሌላኛው አገላለጽ ነው። ወይም አሜሪካን አገር ውስጥ በዘላቂነት የመቀመጥ መብት መኖር ማለት ነው። የአሜሪካን ሕግ፤ ስደተኞች፤ በአሜሪካን አገር ውስጥ ከገቡበት ዕለት ጀምሮ የሚቆጠር አንድ ዓመት “በአካል ከተቀመጡ” በኋላ ይህንን ለዘለቄታው የሚያስኖራቸውን የፈቃድ ወረቀት ለማግኘት የግድ ማመልከት አለባቸው ይላል።
አሜሪካን አገር እንደ ስደተኛ ከገባችሁ በኋላ ወደ ውጭ አገር ተጉዛችሁ ከሆነ መሙላት የሚጠበቅባችሁ የአንድ ዓመት ቆይታ ይራዘማል ማለት ነው።
በእኛ አስተያየት፤ በአሜሪካን አገር “በአካል” የቆያችሁበት አንድ ዓመት ሊጠናቀቅ ትንሽ ግዜያት ሲቀረው፤ ሕጋዊና ዘላቂ የሆነውን የመኖርያ ፈቃድ ወረቀት ለማግኘት ማመልከት ብትጀምሩ የተሻለ ነው እንላለን። በአሜሪካን አገር የቆዩበት ግዜ አንድ ዓመት ከመሙላቱ በፊት ማመልከት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። እስከ አሁን አሜሪካን አገር የቆዩት ከአንድ ዓመት በላይ ከሆነ ደግሞ አሁኑኑ በተቀላጠፈ ሁኔታ ማመልከቻ ማስገባት አለቦት።
የአሜሪካን መንግስት፤ በ 2026 አሜሪካን አገር ውስጥ አንድ ዓመት ያደረጉና ግሪን ካርድ ለማግኘት ገና ማመልከቻ ያላስገቡትን ስደተኞች እንዲሁም ግሪን ካርድ ለማግኘት የሚደረገውን ቃለመጠይቅ ገና ያላደረጉ ስደተኞችን የሚይዝና የሚያስር መሆኑን የሚያመለክት አዲስ መመርያ አውጥቷል። ይህ መመርያ፤ ግሪን ካርድ ለማግኘት ማመልከቻቸውን ያስገቡ ግን ገና ግሪን ካርድ ያላገኙ ስደተኞችንም አስጊ ሁኔታ ላይ የሚጥል ነው። ኢራፕ ( IRAP) ይህንን ፖሊሲ በመቃውም በፍርድ ቤት ክስ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም ይህ ጉዳይ ገና ውሳኔ ያላገኘ በመሆኑ፤ ጉዳዩ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ መንግስት ሰው መያዝና ማሰር አይችልም የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። አንዳች ለውጥ ከመጣ፤ ይህንን ገጽ እናድሳለን። እስከ ሰኔ (June) 5 ቀን 2026 ድረስ የሚታወቀው፤ በዚህ መመርያ መሰረት ማንም ስደተኛ መያዝና መታሰር አይችልም።
ከአሜሪካን አገር ውጪ መጓዝ እችላለሁን?
ስደተኞች ከአሜሪካን አገር ውጪ መጓዝ ይችላሉ ግን ወደ ውጭ ከመጓዞ በፊት የስደተኞች የጉዞ ዶኩመንት ( Refugee Travel Document አር ቲ፟ዲ RTD ) ማግኘት አለቦት፡፡ ከአሜሪካን አገር ውጭም ሁነው ይህንን የጉዞ ዶኩመንት ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ፤ ይህ ግን የሚደገፍ አይደለም። ምክንያቱም ውጭ አገር ሁነው ማቅረብ የሚያስፈልጎትን ዶኩመንት ሁሉ ለማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ ለዘለቄታው ሌላ አገር ተቀርቅሮ የመቅረት አደጋ ሊያከትሎቦት ይችላል።
ይህንን የስደተኞች የጉዞ ወረቀት (RTD) ለማግኘት በሚያመለክቱበት ወቅት፤ ፎርም አይ-131 ( Form I-131) የተባለ ፎርም ሞልተው ለዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ ( USCIS) መስጠት አለቦት። ያስገቡት ፎርም ተቀባይነት ካገኘ፤ አብዛኛውን ግዜ እስከ አንድ ዓመት የሚቆይ የጉዞ ፈቃድ (RTD) ይሰጦታል። ስለዚህ የስደተኞች የጉዞ ፈቃድ አር ቲ ዲ (RTD) እና እንደ ስደተኛ ሁኖ ዓለም አቀፍ ጉዞ ስለማድረግ በበለጠ መረጃ ለማግኘት የኢራፕ (IRAP)ን ጽሁፍ እዚህ ላይ ይመልከቱ።
እዚህ ላይ በደንብ ማስታወስ የሚገባዎት ነገር፤ በስደተኛ ጉዳዮ ውስጥ እርሶ ዋናው አመልካች (principal applicant) ከሆኑና እንደ ስደተኛ ሁነው ወደ ወጡበት አገር ተመልሰው ከሄዱ ያገኙትን የስደተኛ ወረቀት ሊያጡ እንደሚችሉ ነው። ግሪን ካርድ (green card) ያሎት ስደተኛ ቢሆኑም ወደ አሜሪካን አገር እንደ ስደተኛ ከሆነ የገቡት፤ ወደ አመለጡበት አገር ተመልሶ መግባት ያሎትን የስደተኛ ወረቀት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ማድረግ ነው። መጀመርያውኑም የስደተኛ ወረቀት ሊያገኙ የቻሉት አገርዎ ውስጥ መቀመጥ ደህንነትዎ ላይ አደጋ የሚያስከትልና ከአገሮ ማምለጥ የግድ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ስላቀረቡ መሆኑን አስታውሱ። አሁን ተመልሰው ወደ አገርዎ ቢሄዱ፣ መንግስት ከመጀመርያውም ቤሆን የስደተኛን መስፈርት እንደማያሟሉ ለማመን በቂ ምክንያት ይኖረዋል ማለት ነው። ይህም ወደ አሜሪካን አገር እንደገና ለመመለስም ሆነ ወደፊት የኢሚግሬሽን ጠቀሜታዎችን ለማግኘት በሚያመለክቱበት ግዜ እንቅፋት/ችግር ይፈጥርቦታል።
ወደ አሜሪካን አገር ስገባ ባለቤቴና ልጆቼ ከእኔ ጋር አልነበሩም። አሁን ከኔ ጋር መቀላቀል ይችላሉን?
ከእርሶ ጋር ወደ አሜሪካን አገር ለመጓዝ ያልቻሉ ባለቤትዎና ዕድሜያቸው ከ 21 ዓመት በታች የሆኑና ባለትዳር ያልሆኑ ልጆችዎ ከእርሶ ጋር እንዲቀላቀሉ፤ አሜሪካን አገር መቀመጥ ከጀመሩበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ማመልከት ይችላሉ። ስለዚህ ጉዳይ የኢራፕን ( IRAP)ን ጽሁፍ እዚህ ላይ ይመልከቱ።
ተጨማሪ መረጃና ምንጮች
- ግሪን ካርዶን (green card) ለማግኘት ገና በመጠባበቅ ላይ ከሆኑና ወደ ውጭ አገር ለመሄድ ከፈለጉ፤ የስደተኛ ጉዞ ዶኩመንት (refugee travel document) ማግኘትዎን ያረጋግጡ። ይህ ዶኩመንት ካሎት ተመልሶ ወደ አሜሪካን አገር መግባት ይፈቀድሎታል።
- አድራሻዎን ከቀየሩ ዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) እንዲያውቅ ያድርጉ። በፖስታ የሚላክሎት የሆነ መልእክት ካመለጦት ጉዳዮን ሊያዘገይ ይችላል።
ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን ለመከታተል የዩ ኤስ ሲ አይ ኤስ (USCIS) የኦንላይን ሂሳብ ይክፈቱ።
የአለም አቀፍ የስደተኞች እርዳታ ፕሮጀክት (IRAP) ለአንዳንድ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ነፃ የህግ እርዳታ ይሰጣል።
- IRAP አንዳንድ ሰዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እና የስደተኛ እና የቪዛ ማመልከቻዎችን እንዲያዘጋጁ ይረዳቸዋል።
- IRAP የየትኛውም መንግስት፣ IOM ወይም UNHCR አካል አይደለም።
- IRAP የስደተኛ ደረጃ ወይም ቪዛ ሊሰጥ ወይም ጉዳዮችን ማፋጠን አይችልም።
- IRAP የገንዘብ ድጋፍ መስጠት፣ መኖሪያ ቤት ማግኘት ወይም መክፈል፣ ወይም ሥራ ማግኘት አይችልም።
- ሁሉም የ IRAP እርዳታ ነፃ ነው። ማንም ሰው ከIRAP ጋር ግንኙነት ያለው ገንዘብ ወይም ሌላ አገልግሎት ሊጠይቅዎት መብት የለውም።
IRAP ሰዎችን በፍላጎታቸው እና ለስደት ሁኔታ ብቁነታቸውን መሰረት አድርጎ ለመርዳት ይወስናል። IRAP በማንኛውም ሌላ ማህበራዊ ወይም ፖለቲካዊ ወይም ሃይማኖታዊ መመዘኛዎች ሰዎችን ለመርዳት አይወስንም።
ይህ ድህረ ገጽ ለአንዳንድ ስደተኞች ስለሚገኙ የህግ ሂደቶች አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። ለግል ማመልከቻዎች እንደ ህጋዊ ምክር አይደለም።
መስፈርቶች ሊለወጡ ይችላሉ። ጥያቄዎን ሲወስኑ ሁል ጊዜ ከመንግስት ወይም ከኤጀንሲው ወቅታዊ መስፈርቶችን ያረጋግጡ።
በስደተኞች ድንገተኛ አደጋ ውስጥ ከሆኑ፣ በሚኖሩበት አገር ያለውን የ UNHCR ቢሮ እንዲያነጋግሩ እንመክራለን።
Comments
0 comments
Please sign in to leave a comment.